መስከረም አበራ ዛሬ ከሰዓት በኋላ አዲስ አበባ ውስጥ በሜክሲኮ የፌደራል ወንጀል ምርመራ መታሰሯን ተገለጠ።

Read Time:31 Second
ከዚህ ቀደም ታስራ ከእስር የተፈታችው መስከረም አበራ ዛሬ ከሰዓት በኋላ አዲስ አበባ ውስጥ በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋሏን ባለቤቷ መናገሩን ቢቢሲ ዘግቧል።
የመስከረም አበራ ባለቤት አቶ ፍጹም ገ/ሚካኤል እንደተናግረው ፤ ከሰዓት 10፡30 አካባቢ ” ሃያ ሁለት / 22 ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አብረው ሳሉ ሲቪል እና የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች መጥተው መስከረምን ይዘው ሄደዋል።

መስከረም የግለሰቦቹን ማንነት ስትጠይቅ የፌደራል ፖሊስ አባላት መሆናቸውን ከገለጹ በኋላ ሜክሲኮ ወደሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ መሥሪያ ቤት ይዘዋት እንደሚሄዱ ተናግረው በመኪና እንደወሰዷት ባለቤቷ ፍጹም ገ/ሚካኤል አስረድቷል።
ፍጹም እንደሚለው ባለቤቱ ታስራ ወደምትገኝበት ሜክሲኮ የፌደራል ወንጀል ምርመራ አቀንቶ መስከረምን ማግኘቱንና በምን ወንጀል ተጠርጥራ በቁጥጥር ስር እንደዋለች እንደማታውቅ ተናግረዋል።