ከሁለት ዓመት በፊት ያስተላለግኩት መልዕክት

0
1 0
Read Time:1 Minute, 59 Second

ዶክተር በቀለ
,…………………

በግፍ ሰዉ መግደል፤ ማሰርና ማፈናቀል ይቁም

1ኛ/ የንፁሐን ዜጎች አብሮ መቆምና ለፍትሕ መታገል ታሪክ

በቀደሙት ዘመናት ንፁሐን ዜጎች በዘር በጎሣ ሳንለያይ የአማራ፤ ኦሮሞ፤ ትግራይ፤ ጉራጌ፤ ወዘተ ልጆች ጎን ለጎን ቆመን ነበር ለዲሞክራሲና ለሰላም የታገልነዉ፤ ከፍተኛ የህይወት መስዋእትነትም የተከፈለወ። ዛሬ ያ መንፈስ እርቆን ነው ከባድ ችግር ዉስጥ የገባነዉ። መማር ይኖርብናል።

2ኛ/ በትግራይ የተቀጣጠለዉ ጦርነት ቶሎ እልባት ማግኘት አለበት

ግፍ የፈፀሙት የህወሃት መሪዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ መሞከሩ መልካም እርምጃ ነበር። ነገር ግን የንፁሐን ዜጎች ህይወት መጥፋት፤ መፈናቀልና ንብረት መዉደም እጅጉን ያሳዝነናል። ስለዚህ የተፈናቀሉት ወገኖች ቶሎ እንዲመለሱና እንዲቋቋሙ፤ ንብረታቸዉ ለወደመባቸዉ ወገኖች ተገቢዉ ካሣ እንዲከፈላቸዉና ሰላም እንዲወርድ በቅንነት ላሳስብ እወዳለሁ።

3ኛ/ በሌሎቹ የአገራችን ክፍሎች የሚካሄዱ የዘር ማጥፋት ወንጄሎች ቶሎ መቆም አለባቸዉ

በተለይ በኦሮሞና ቤኒሻንጉል ክፍሎች የሚካሄዱ የዘር ጭፍጨፋዎች እጅግ ዘግናኞችና ማፈሪያዎቻችን ናቸዉ። ዛሬ ባለንበት 21ኛዉ ክፍለ ዘመን ከቶ የሚጠበቅ ነገር አይደለም። መንግሥት እነዚህን ቶሎ ማስቆም ይጠበቅበታል። ዋና ኃላፊነቱ ነዉና። ስንት ሰዉ እስከሚሞት ወይም እስከሚቀር ድረስ ነዉ የሚጠበቀዉ? ወገን እያለቀ ነዉ። በመቶ ሺዎች እየተፈናቀለ ነዉ። ይሄን ለማቀጣጠልና ለማባባስ የተሰለፉ ጽንፈኞችም ብዙ ናቸዉ።

ከዚያም በመሻገር በደቡብ ኮንሶ፤ በሰሜን ምሥራቅ በሶማሌ፤ በአፋር፤ ወዘተ የሚሰሙት ወንጀሎች እጅግ አሰቃቂና ዘግናኞች ናቸዉ። መላዉ አገር እየተቃጠለ ይገኛል። ምንድን ነዉ የምንጠብቀዉ? ‘ተዉ ስማኝ ሀገሬ፤ ተቃጥሏል መሰለኝ ሸተተኝ ሀገሬ’ ይባል ነበር።

4ኛ/ በግፍ የታሰሩ የፖሊቲካ መሪዎችና አባላት ቶሎ ይለቀቁ።

ባንድ በኩል ለአገራዊ ምርጫ ዝግጅት ሲደረግ በሉላ በኩል ደግሞ እነ እስክንድር ነጋ ወደ ወህኒ ቤት መወርወራቸዉ እጅግ በጣም ያሳዝነናል፤ ያሳስበናል። በርግጥ ወንጀል ያለባቸዉ ግለሰቦች በሕግ መጠየቅ ይኖርባቸዋል። ብዙ ሰዉ እንደሚመሰክረዉ ግን እነ እስክንድር ከወንጀል ነፃ የሆኑና ለፍትና ለዲሞክራሲ በሰላም መንገድ የሚታገሉ ዜጎች እንደሆኑ ነዉ። ከአሁን ወዲያ ሳናጣራ አናስርም ተብሎ ቃል የተገባዉ በተግባር እንዲታይ ይፈለጋል። ልክ እንደእነ ልደቱና ይልቃል ጌትነት፤ እነ እስክንድርም ቶሎ እንዲለቀቁ ለመንግሥት ጥሪዬን ላስተላልፍ እወዳለሁ።

5ኛ/ ለአገራዊ ምርጫ አሁን ዝግጁዎች አይደለንም።

እላይ ባጭሩ የተመለከቱት ችግሮች አገራችንን እያመሱና እያተራመሱ ናቸዉ። በአገሪቷ ክፍሎች በነፃ መንቀሳቀስ የሚቻልበት ሁናቴ የለም። በሰሜንና ምዕራብ በኩል ጦርነት ላይ እንገኛለን። በተቀሩት ክፍሎች ጭፍጨፋዎች እየተካሁዱ ይገኛሉ። ነፃ ተቋማት ገና በደንብ አልተገነቡም። ሕገ መንግሥቱ ራሱ መሻሻል ይኖርበታል። ወደ ወህኒ ቤት የተወረወሩት የፖሊቲካ መሪዎች ጉዳይ አጠያያቂ ነዉ። እነዚህ ሁሉ እስከሚስተካከሉ ድረስ ስለነፃ ምርጫ ማሰብ የሚቻል አይመስለኝምና እንዲተላለፍ እጠይቃለሁ።

6ኛ/ የዉጪ ጠላቶቻችንን በተመለከተ

የዉጪ ጠላቶች ድንበር ለመቀራመት፤ ግድባችንን እንዳንገነባና ከፋፍለዉ ሊገዙን የሚችሉት ስንከፋፈል ብቻ ነዉ። አንድ ላይ በነበርንባቸዉ አያሌ ዘመናት አልቻሉንም፤ እግዚአብሔርም ከኛ ጋር ነበር። ዛሬ ግን ‘ባለቤቱ ያቀለለዉን አሞሌ ባለ ዕዳ አይቀበለዉም’ እንደተባለዉ ንቀዉናል። አሁን አገራዊ ሰላም እንድናወርድ፤ ህዝብ እንድናረጋጋ፤ አንድነታችንን እንድናጠናክርና ድንበራችንንና ሉዓላዊነታችንን እንድናስከብር አደራ እላለሁ።

ለክርስቲያን ወገኖቻችን፤ እንኳን ለጌታችን፤ ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶች ገና አደረሳችሁ፤ መጪዉም ዘመን የእርቀ ሰላምና የደህንነት፤ የተስፋና የአንድነት እንዲሆንልን እመኛለሁ፤ እፀልያለሁ። ይቅር ይበለን፤ አሜን።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *