1 0
Read Time:1 Minute, 1 Second

እደግመዋለሁ የሞተ ተጎድቷል…!!

“…ዐቢይ አሕመድ ተጎድቷል? አገኘሁ ተሻገር አባ አረቄ ተጎድቷል? ብርሃኑ ጁላ እንዲህ ደምቷል? ጭራሽ የማርሻልነት ማዕረግ አይደል እንዴ ያገኘው? እነ ጻድቃን፣ ጌታቸው ረዳ እና እነ ደብረ ጽዮን ተጎድተዋል? አልተጎዱም። በጫ ደበሌ ይሄን ሁሉ ወታደር አስፈጅቶ አሁን የት ነው ያለው? ኦሮሞነቱ አምባሳደርነት አይደል ያሸለመው?

“…ይሄ ቁስለኛ ወታደር ትክክል ነበረ። ሃገሬ ተደፈረች ብሎ መሄዱ፣ መቁሰል፣ መማረክ፣ መሞቱም ስህተት አልነበረም። ይሄ ሁሉ እልቂት፣ ይሄ ሁሉ ስቃይ፣ ይሄ ሁሉ ሰቆቃ ሳይመጣ በፊት ግን እንደ ትናንቱ የመቀሌ የሃሰት አርቴፍሻል ፍቅር መፍጠር አይቻልም ነበር? እና ዛሬ ላይ የትናንቱን ስህተት ይሄን ሁሉ ስቃይ የፈጠሩ፣ ያስፈጠሩ፣ ከዚህም፣ ከዚያም ወገን በፍትሕ ሳይዳኙ ሰላም ብሎ ነገር የማይታሰብ ነው።

“…እደግመዋለሁ ትናንትም ጦርነት ስታውጁም ሆነ ዛሬ ስትታረቁ እናንተ ብቻ በጦርነቱም ጊዜ ልክ፣ በሰላሙም ጊዜ ልክ የምትሆኑበት ምክንያት የለም። በጦርነት ወቅት ስለሰላም ሲዘምሩ የነበሩትን ስታሸማቅቁ ኖራችሁ፣ ስታላግጡበት፣ ሰታዋርዱት፣ ስትሰድቡት ከርማችሁ አሁን ባሻችሁ ሰዓት ያለምንም ተጠያቂነት ሰላም፣ ሰላም እያልክ እኔን ፍትሕ ጠያቂውን እንደ ጦርነቱ ጊዜ ልታሸማቅቀኝ ብትሞክር አልሰማህም። ደሀ አስጨርሰህ ሃገር አስወድመህ ዛሬም ትክክል ነኝ ብለህ ብትሰብከኝ አልሰማህም።

“…ድፍረታቸው እኮ ገራሚ ነው። ደመቀ መኮንን 30 ዓመት ሙሉ ምክትል ሚኒስትር ሆኖ ለሚኖረው፣ ዳግማዊት ሞገስ 30 ዓመት ሙሉ ዳሌዋንም ጫንቃዋንም እንደሐረርጌ ሰንጋ ለምታደልበው፣ ብርሃኑ ጁላና ባጫ ደበሌ በደርግም፣ በወያኔም፣ በብልጽግናም ዘመን 10 ጊዜ ለወያኔ ይገረዳሉና ደሀው ማለቅ አለበት እንዴ? እውነተኛ ሰላም ከፍትሕ ጋር ብቻ።

እደግመዋለሁ የሞተ ተጎዳ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *