ክቡር አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ ፓሪስ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና ማህበረሰቡን በማመስገን ተሰናበቱ።

Read Time:23 Second

በፈረንሳይ፣ ስፔን፣ፖርቹጋል ፣ ሞናኮ እንዲሁም UNSECO #የኢትዮጵያ አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ የስራ ጊዜያቸውን እንዳጠናቀቁ አሳውቀዋል።
አምባሳደር ሄኖክ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰራጩት ፅሁፍ ፤ በፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ፖርቹጋል፣ ሞናኮ እና UNSECO በአምባሳደርነት ሀገራቸውን ያገለገሉበት የስራ ጊዜ ማብቃቱን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያን በውጪ ሀገር ከወከል የበለጠ ትልቅ ነገር እንደሌለ የገለፁት አምባሳደር ሄኖክ ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሀገራቸውን የማገልገል እድል ስላመቻቹላቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ ፓሪስ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና ማህበረሰቡን አመስግነዋል ፤ ሰላምና ብልፅግናን ለኢትዮጵያ ተመኝተዋል።