በኢትዮጵያ የትምህርት እና የሐይማኖት ስርዐቱ እንዳይሰራ ለምን ተፈለገ?? ለምንስ ጦርነት ተከፈተበት??

0
0 0
Read Time:1 Minute, 10 Second

ይህ ስዕል የተሳለው ጆሴፍ ዲዘሪ በተባለ ሰዓሊ ነው። እንደምትመለከቱት ሰውየው ውድ ሚስቱንና ልጁን ትቶ አባቱን ከመስመጥ አደጋ ለማዳን እየሞከረ ነው። በግልፅ ለማየት እንደሚቻለውም፦ ከአባትየው ይልቅ ሚስቱን፤ ከሚስቱም ይልቅ ልጁ ለእርሱ በጣም ቅርቡ ነበሩ። ነገር ግን ሰውየው እየተንጠራራ ያረጀ አባቱን ለማዳን እየጣረ ነው።

እና ሰዓሊው ምን ለማሳየት ፈልጎ ነው?

በዚህ ስዕል ላይ፦
👶 ህፃን ልጁ፦ ነገን ይወክላል።
🤰 ሚስቱ ደግሞ ህፃን ልጁን (ነገን) የሰጠችው ህይወትን ትወክላለች።
🧙‍♂️ ያረጀ አባትየው ደግሞ ትላትን፣ ትዝታና ታሪክን ይወክላል።

የሰው ልጅ ትላትናን የሙጥኝ ብሎ ህይወቱንና ነገውን ረስቶ በሰቆቃ ውስጥ እንደሚኖር ለመግለፅ ነው የሞከረው። የትላንት ደስታውን፣ ሀዘኑን፣ ስኬት ውድቀቱን፣ ጥጋብ ረሀቡን፣ መከፋት መደሰቱን….. እያሰላሰለና ‘ እንዲህ ቢሆን ኖሮ’ እና ‘እንዲህ ባይሆን ኖሮ’ እያለ ዛሬን ሳይኖራት፤ ነገን ሳይቀበላት ትዝታው ውስጥ ተዘፍቆ፤ ታሪኩ ውስጥ ተደብቆ፤ ‘እንደዛ ነበርኩ’ን እየዘፈነ የትላንቱ እስረኛ ሆኖ ይኖራል።

ትላትና የዛሬ መዳረሻ፤ የነገ መማሪያ እንጂ… የዛሬ ሰንኮፍ መሆን የለበትም። ነገን አሳልፈን እንዳናይ የሚያደርገን መጋረጃም መሆን የለበትም።

ትላትና ታሪክ ነው፤ ነገ ደግም ምን መሆኑን የማይታወቅ በስጦታ ወረቀት ውስጥ ያለ በረከት ነው፤ ህይወት የሚገለጠው ደግሞ በ’ዛሬ’ ፤ ከዛሬም ‘አሁን’ ላይ ነው። የሰው ልጅ በትዝታው ውስጥ የሚሆንበት ጊዜ አለው፤ እሱንም ሲያረጅ ነው። አያቶች ከልጅ ልጆቻቸው ጋር መጫወት የሚፈልጉት ትላትናቸው ስለሚናፍቃቸው ነው። ታሪካቸውን መንገር የሚወዱትም ትላንትናቸው ስለሚያስደስታቸው ነው። ህፃናት ደግሞ እቃ-እቃ ሲጮቱ እንደ ትልቅ ሰው አክት የሚያደርጉት ነጋቸው ስለሚናፍቃቸው ነው። ባልና ሚስት ሆነው፤ ልጆች ኖሯቸው፤ ስለ ስራ እያወሩ ምናምን ብለው የሚጮቱት… ነገን ስለሚናፍቁ ነው።

ለወጣት ደግሞ ‘ዛሬ’ ነው ያለችው። ዛሬ የሚለፋበት፣ ህልሙን የሚያባርርበት፤ መክሊቱ የሚገልጥበት፤ ህይወትን የሚያጣጥምበት፤ ስኬትን የሚያነፈንፍበት ጊዜው ናት። ዛሬ!

ዛሬንና ህይወትን እንኑራት!
⩩⨳⩩⨳⩩⨳⩩⨳⩩⨳⩩⨳⩩⨳⩩⨳⩩⨳⩩⨳⩩⨳⩩⨳⩩⨳⩩
መልካም ቀን! 🌄

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *