የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከ50 % በላይ አምጠወተው ያለፉት 3 በመቶ ናተቸው ሌላው ተፈተነ እነጂ አላለፈም።

0
1 0
Read Time:1 Minute, 7 Second

12 ክፍል ብሔራዊ ፈተናን 50 % በላይ ያመጡት ከተፈታኞች ውስጥ 3.3 በመቶ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ፈተናውን በትክክል ከወሰዱት 896,520 ተማሪዎች ውስጥ ከግማሽ በላይ ያመጡት፤ 29,909 መሆኑን ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በትላንትናው ዕለት ይፋ የተደረገውን 12 ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በሰጡት መግለጫ ምን ምን ጉዳዮችን አነሱ ?

– በ2014 የትምህርት ዘመን ለፈተና የተመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በጠቅላላ 985 ሺህ 354 ተማሪዎች ሲሆኑ ለፈተና የቀረቡት 92 ነጥብ 2 % 908 ሺህ 256 ተማሪዎቹ ሲሆኑ 77 ሺህ 98 ተማሪዎች ፈተና አልወሰዱም።

– በደንብ ጥሰት ፣ለመኮራረጅ በመፈለግ እና በሌሎች ምክንያቶች 50 ሺህ 170 ተማሪዎች ሳይፈተኑ ቀርተዋል።

– በ2014 የትምህርት ዘመን 899 ሺህ 520 ተማሪዎች ተፈትነዋል ።

– በፆታ ማዕከልነት የአማካይ ውጤት በወንዶች 30 ነጥብ 2 እንዲሁም ሴቶች 28 ነጥብ 09 % አማካይ ውጤት አስመዝግበዋል።

– በትምህርት ዘርፍ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከማህበራዊ ሳይንስ በተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን የተፈጥሮ ሳይንስ 31 ነጥብ 63 ከመቶ እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ 27 ነጥብ 79 ከመቶ በአማካኝ አስመዝግበዋል።

– በክልል ደረጃ ይህየ ነው የሚባል የውጤት ልዩነት የሌለ ሲሆን አዲስ አበባ ፣ ሐረሪ እና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የተሻለ ውጤት አስመዝግበዋል።

– ከተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወንድ ከ 700፤ 666 ያስመዘገበ ሲሆን 650 ሴት ተማሪ አስመዝግባለች ።

– በማህበራዊ ሳይንስ ከ600 ወንድ 524 አስመዝግቧል።

– ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር እውቅና እና ሽልማት ይሰጣቸዋል።

Source: https://moe.gov.et/storage/Books/ESAA%202021-22%20Final%20(2).pdf

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *