በሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውሰጥ ሁለት ወጣቶች በመንግሰት ሃይሎች ተረሸኑ።

0
0 0
Read Time:1 Minute, 59 Second

በዐራት ወጣቶች ላይም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል

ቅዳሜ ጥር 27 ቀን 2015 በሻሸመኔ ከተማ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን፤በኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ በሕገ ወጥ መንገድ የተሾሙት ኤጲስ ቆጶሳት ወደ ሻሸመኔ ይመጣሉመባሉን ተከትሎ፤ ጠዋት ኹለት ሰዓት ላይ ሥርዓተ ቅዳሴ እንደተፈጸመ ሕዝቡን ለመጥራት በከተማዋ ያሉ አድባራት ደወል ደውለዋል።

ይህንን ጥሪ ሰምቶ ሁሉም ምእመን ወደ ወደ ሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ያቀና ሲሆን፤ ምእመኑ የቤተ ክርስቲያኑ በር በመዘጋቱ ከውጪ ቆሞ እንደነበር ተገልጿል።

በእንዲህ ሁኔታ ውስጥ እያለ የከተማው ፖሊስ በሰላማዊ ሕዝቡ ላይ ተኩስ መክፈቱ የተነገረ ሲሆን፤እስካሁን ድረስ ሀ‍ኡለት ኦርቶዶክሳዊያን ወጣቶች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ በአራት ወጣቶች ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ዘግቧል።

ከጠዋት አንስቶ የአብያተ ክርስቲያናቱ በር በጸጥታ ኃይሎች ቢዘጋም ሕዝቡ አጥሩን እየገነጠለ ወደ ቤተ ክርስቲያኗ ቅጽር ጊቢ መግባቱም ተገልጿል።

አብያተ ክርስቲያኗ ውስጥ ያሉት ምእመናን እስካሁን ድረስ በቅጽር ግቢ ውስጥ እንዳሉ የተገለጸ ሲሆን፤ ነገር ግን አሁን ላይ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጣውን የጸጥታ ኃይል አባላት በዱላ እያባረሩ እንደሚገኙም ነው የተነገረው።

የከተማዋ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አካላት ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ውጪ ላሉት የከተማዋ ነዋሪዎች ነጠላ በማደል ሻሸመኔ ስታዲዮም ተገኝተው ሕገ ወጡን ቡድን እንዲቀበሉ እያስተባበሩ እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን፤ በመኪና ከተማውን እየዞሩ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ እንደሚገኙም ተነግሯል።

በአሁኑ ሰዓትም የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ከሻሸመኔ እስከ አርሲ ነገሌ ድረስ ያለውን ቦታ መቆጣጠሩን ተ.ሚ.ማ በዘገባው አመላክቷል።

በሌላ በኩል በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በጭሮ ከተማ በሕገ ወጥ መንገድ የተሾሙት ኤጲስ ቆጶሳት ዛሬ ጥር 27 ቀን 2015፤ እንደሚመጡ መረጃ ስለደረሳቸው የጭሮ ከተማ ሕዝበ ክርስቲያን በከተማው የሚገኙትን 4 አብያተ ክርስቲያናት በንቃት እየጠበቀ እንደሚገኝ ተነግሯል።

ትናንት ሌሊት ሊቀ ጳጳሷ የታሠሩባትና መቆየት አይችሉም ተብለው ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ የተደረጉባት በአርሲ ሀገረ ስብከቷ መናገሻ አሰላ ላይም፤ ኦርቶዶክሳውያን እየታሠሩ መሆኑንና በቤተ ክርስቲያን ቅጥር ያሉትም እንዲወጡ እየተነገራቸውና ያ የማይሆን ከሆነ የኃይል እርምጃ እንደሚወሰድባቸው እንደተዛተባቸው እንደሚገኝም ተገልጿል።

በተጨማሪም በአሁኑ ሰዓት አሰበ ተፈሪ ልደታ ማርያም ቤተክርስቲያን ደወል በመደወል ምዕመኑን ወደ ቤተክርስቲያን መጥራቷን ለማወቅ ተችሏል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በቀድሞ ስማቸው 1ኛ. አባ ሳዊሮስ ፣ 2ኛ. አባ ኤዎስጣቴዎስ ፣ 3ኛ. አባ ዜና ማርቆስ ፤ እንዲሁም ኤጲስቆጶሳት ተብለው ተሹመዋል ተብሎ መግለጫ የተሰጠባቸው 25 ግለሰቦችን ጨምሮ፤ በፌዴራል ፖሊስ፣ በኦሮሚያ ክልል መንግስት እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ላይ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ መሰረታዊ መብቶች እና ነፃነቶች ምድብ ችሎት ክስ ለመመስረት ጥያቄ ያቀረበች ሲሆን፤ ክስ የመመስረት ሂደት ጊዜ ስለሚፈልግም ጊዜያዊ እግድ እንዲሰጥ ጥያቄ ማቅርቧን መግለጿ ይታወሳል።

__

ሻሸመኔ አሁን…! “…በፎቶው ላይ በምታዩት ከንቲባ በኦቦ ያከኔ ትእዛዝ በአሁን ሰዓት ፖሊሶቹ ኃይል እንዲጠቀሙ በመታዘዛቸው በአሁን ሰዓት በጭስ ቦንብና በስናይፐር በከባድ መሳሪያም የታገዘ ጭፍጨፋ ተጀምሯል። እስከአሁን 3 ልጆች ተመተዋል። ይሙቱ ይዳኑ አልታወቀም። “…የከተማው ከንቲባ የአቶ ያከነ ስልክ ይሄ ነው። +251 916827121

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *