ዶ/ር ዳንኤል የሚዲያ ባለሙያዎችን ማዋከቡ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ገለፁ።

0
2 0
Read Time:1 Minute, 5 Second

የሚዲያ ባለሙያዎችን ማዋከቡ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ

የሚዲያ ባለሙያዎችን ማዋከቡ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር / ዳንኤል በቀለ ገለጹ፡፡

/ ዳንኤል ይህን ያሉት በትናንትናው ዕለት በዓለም አቀፍ ደረጃ 31ኛው የተከበረውን የፕሬስ ነጻነት አስመለክቶ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ባዘጋጀው መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

በኢትዮጵያ የሚዲያ ነጻነት በአሁኑ ወቅት አደጋ ውስጥ መግባቱን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ፤ በአሁኑ ወቅት ቢያንስ ስምንት ጋዜጠኞች በእስር ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ በእስር ላይ ከሚገኙት ጋዜጠኞች በተጨማሪ በመንግሥት በመሳደድ ላይ ያሉ ጋዜጠኞች ስለመኖራቸውም ጠቁመዋል፡፡

የሚዲያ ነጻነት ለሰብዓዊ መብቶች መከበር መሰረት መሆኑን ያስታወሱት ኮሚሽነሩ፤ ከአራት ዓመት በፊት የታየው የነጻነት ዝንባሌ በሂደት አደገኛ ወደሆነ ሁኔታ መለወጡን ጠቁመዋል፡፡ በወቅቱ የታየውን የሚዲያ ነጻነት ዝንባሌ ተከትሎ የተሻሻለው የሚዲያ አዋጅ ትልቅ ለውጥ የታየበት ቢሆንም፤ አፈጻጸሙ ላይ በርካታ ከፍተቶች መታየታቸውን ተናግረዋል፡፡

በሕጉ አፈጻጸም ላይ ከታዩ ከፍተቶች መካከል ጋዜጠኞች በአዋጁ ላይ የተሰጣቸውን መብት በግልጽ የሚጥሱ እስሮችና ተገቢ ያልሆነ ወከባ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን በአዋጁ ላይ በሚዲያ ላይ በቀረበ ይዘት የተፈጸመ ወንጀል ሲኖር፤ ከእስር በፊት ክስ መቅረብ ያለበት ቢሆንም አሁን እየታየ ያለው ከዚያ በተቃራኒ መሆኑን ዳንኤል ገልጸዋል፡፡

ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ከሚዲያ ነጻነት የሚቀዳ ሲሆን፤ ከሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ የሚመዘንበት ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡ የሚዲያ ሕግ ጥሩ ቢሆንም፤ አፈጻጻሙ ላይ በርካታ ክፍትቶች ታይተውበታል።

“ቅድመ ክስ እስር በሕጉ ቢከለከልም መንግሥት ይህን ሕግ በተደጋጋሚ ጥሶታል” ያሉት ዳንኤል፣ ችግሩን አሁንም ተባብሶ መቀጠሉ አሳሳቢ ከመሆኑ ባሻገር ችግሩን ለመቀልበስ ብዙ ሥራ እንደሚጠይቅም አመላክተዋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *