1 0
Read Time:1 Minute, 10 Second

ማህበራት ሲመሰረቱ እራሳቸውን በገንዘብ/በገቢ መደጎማቸው የተለመደ ነው። እናም የሀገር ፍቅር ማኅበር የገቢ ችግሩን ለሟሟላት ያልፈነቀለው ፣ ያልሞከረው ጉዳይ አልነበረም።
በ1940’ዎቹ መባቻ ላይ ግን አንድ እድል ገጠመው። እርሱም አዲስ አበባ ውስጥ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ጠንቋዮች አቤቱታ ማቅረብ ጀመሩ።

ጥያቄአቸውም ጥንቁልና ሥራ ሆኖ ሳለ መንግስት ስለምን ትኩረት አልሰጠውም የሚል ነበር። ይነገር ጌታቸው ደሞ ጠመንጃና ሙዚቃ በሚለው መጸሐፉ ላይ እንዲህ አሰፈረው ጉዳዩን…ገጽ 53

“በወቅቱ ጥንቆላ ሥራ መሆኑን የተረዱ አንዳንድ ነዋሪዎች ጠንቋይ በመሆን የገቢ ምንጭ ለማግኘት ይሯሯጡ ነበር”። መንግስትም ሁኔታውን አየና የሥራ ፈቃድ አውጥተው እንዲንቀሳቀሱ አሳሰበ።

ይህን የፈቃድ የመስጠት አላፊነት ደግሞ ለሀገር ፍቅር ማኅበር የሰጠ። አስተዳደሩም ፍቃዱን ለመውሰድ 10 ብር እንደሚያስፈልግ በመደንገግ ወደ ሥራው ገቡ። በዚህ በፊት የኢትዮጵያ ሕዝብ ያገር ፍቅር ማኅበርን የጥበብ ሰዎች የደሞዝ ክፍያ ለማሳደግ ከተሞከሩት ሙከራዎች ሁሉም ይህ የላቀው ሆኖ ተገኘ።

በየዓመቱም ጠንቋዮች ፍቃዳቸውን ለማሳደስ ሲመጡ የሚገኘው ገቢ ከፍ አለ። ነገር ግን በከተማው ውስጥ አዝማሪዎች ስለበዙ ያ ደሞ ወደ ሀገር ፍቅር የሚመጣውን ሰው ስለሚቀንስ ያለ ፍቃድ እንዳይሰሩ ድንጋጌ አወጣ።

ሀገር ፍቅር ይሄን ይሄን የመሰለውን ድንጋጌ ቢያወጣም ገቢው በማነሱና ለጥበብ ቤተሰቦች ገቢያቸውን ከፍ ማድረግ ቢያቅተው ፤ ቁማር ቤትም ሆኖ ነበር። ከቁማር ጨዋታው የሚገኘው ገቢም ከፊሉ ለገንዘብ ሚኒስቴር ፣ የተቀረው ለማኅበሩ የሚበረከት ሆነ። አቶ መኮንን ሀብተወልድ በመሞታቸው ይህ ሥራ ቢስተጓጎልም …

በ1950’ዎቹ በትንሿ አዳራሽ የሙዚቃም ሆነ የቴአትር ትርኢት ሲቀርብ የአለባበስ ሁኔታ ጥብቅ በመሆኑ ፤ ከረቫት ሳያደርጉ ለሚመጡ ከረቫት ማከራየት መፍትሔ ተደረገ።

ያም ቢሆን ማኅበሩ እጅ እያጠረው በመምጣቱ 33 ያህል አባላቱን በገቢ ምክንያት አሰናበተ። እንዲህ እንዲህ እያለ እዚህ ደርሷል ….

ጠመንጃና ሙዚቃ መጸሐፍ ላይ ብዙ ነገሮች በዝርዝር ስላለላችሁ መጸሐፉን ገዝታችሁ አንብቡ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *