”ለህክምና ከአገር እንዳልወጣ መከልክሌን ይመለከታል” ብር ጋዴየር ጄነራል ተፈራ ማሞ

0
1 0
Read Time:2 Minute, 29 Second

“ኢትዮጵያ አገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ፤ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!”

ጉዳዩ፡-

ለህክምና ከአገር እንዳልወጣ መከልክሌን ይመለከታል እኔ ብር ጋዴየር ጄነራል ተፈራ ማሞ ጨርቆስ በኢሕአዴግ ትግል ከተራ ታጋይነት ጀምሮ እስከ ከፍለ ጦር ድረስ በመምራት ለድል አብቅቻለሁ!

በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትም የክ/ጦር አዛዥ ሆኞ በወጊያው ለተገኘ ው የበላይነት ክቡድ አስተዋጽኦ ማድረጌ በመንግሥት ታምኖበት የሜዲላያና የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶልኛል፡፡

ከ1997ቱ ምርጫ በኋላም በመከላከያ ሠራዊቱና በሌሎች ተቋማት የሚያገለግሉ የዐማራ ተወላጆች ታድነው መታሰራቸውና ከሥራ መባረራቸውን ተከትሎ፣ ከጓዶቼ ጋር ሥርዐቱን ለመቀየር ያደረግነው ሙከራ ከሽፎ ከዘጠኝ ዓመት በላይ በአስከፊ እስር ማቅቄያለሁ፡፡

ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ትግራይ በነበረው የኢትዮጵያ መከላ ከያ ሠራዊት የተከፈተበትን ጥቃት ተከትሎ፣ እንደ አገር የተላለፈውን ጥሪ ተቀብዬ የዐማራ ልዩ ኃይልን በዋና አዛዥነት እየመራሁ እና ከመከላከያ ኃላፊዎች ጋር እየተናበብን አገሪቷን ገጥሟት ከነበረው ከባድ አደጋ ታድጌያለሁ፡፡

ክቡራትና ክቡራን፡- ይህንን መግለጫ እንድሰጥ የተገደድኩበትን ምክንያት በተጋድሎ ታሪኬ የጀመርኩት፣ እኔ ለአገሬ ታማኝ ወታደር እንጂ፤ አጥፊዋ ወይም ክፉ ከሚያስቡባት ጋር የመዋል ልማድ እንደሌለኝ ለማስገንዘብ ነው፡፡

ከዚህ ቀጥሎ ፍትሕ የተነፈኩበትን ጉዳይ አብራራለሁ፡፡በትግሉ ዘመን በደረሰብኝ የፈንጂ አደጋ ከስምንት ያላነሱ ፍንጥርጣሪዎች በቀኝ እግሬ ውስጥ ተሰግስገው ይገኛሉ፡፡እነዚህ ፍንጥርጣሪዎች በተለይ ዕድሜዬ እየገፋ ከመሄዱ ጋ ተያይዞ ነው መሰለኝ ወደ አደ ገኛ ደረጃ መድረሳቸውንና ወደ ካንሰር የመቀየር እድል እንዳላቸው በመረጋገጡ፣ የባሕር ዳር ሪፈራል ሆስፒታል የሐኪሞች ቦርድ በ አስቸኳያ ውጭ አገር ሄጄ እንድታከም ወስኗል፡፡

በዚህም መሰረት፣ በእስራኤል የሚኖሩ አገር ወዳድ የዐማራ ተወላጆች ህክምናውን አመቻችተውልኝ ጥቅምት 30/2015 ዓ.ም ቦሌ አየር መንገድ ከደረስኩ በኋላ፣በደህንነት ሠራተኞች እንዳልጓዝ ተከልክዬ ተመልሻለሁ፡፡

ጉዳዩን ወደ ፌደራል ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ መሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶች ችሎት ወስጄ፣ ግራ-ቀኙን ለአንድ ወር ያህል ካከራከረ በኋላ ሚያዚያ 25/2015 ዓ.ም መከልከሌ ሕገ-ወጥ እንደሆነ ጠቅሶ፣ ከአገር ወጥቼ እንድታከም ተወስኗል፡፡ የውሳኔው ግልባጭም ለኢሚግሬሽንና ለብሔራዊ መረጃ ተልኳል፡፡ነገር ግን፣ በዛሬው ዕለት ግንቦት 7 2015 ዓ.ም ከኢሚግሬሽን ከአገር እንዳልወጣ መታገዴ ተነግሮኛል፡፡

ምክንያቱ ምን እንደሆነ ሳጣራ፣ የፌደራል ፖሊስ ባለፈው ዓመት በ“ፍትሕ መጽሔት” የሰጠሁትን ቃለ-መጠይቅ ጠቅሶ በሁከትና ብጥብጥ እንደሚፈልገኝ ሚያዚያ 30/2015 ዓ.ም የጻፈውን አቤቱታ የተመለከተው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ አራዳ ፍርድ ቤት ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የዛኑ ቀን የእግድ ትዕዛዝ በማስተላለፉ እንደሆነ ነገሩኝ፡፡

መቼም አንድ ዓመት ባለፈው ቃለ-መጠይቅ ከአገር ወጥቼ እንዳ ልታከም የተከለከልኩት ፈልጌና መርጬ ባልተወለድኩበት ብሔር መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህም በዚህች አገ ር ላይ ዐማራ መሆን አደጋ እንደሚያስከትል በስፋት ተመልክተናል ፡፡በእኔም የደረሰው ይህ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም “ዐማራ ለምን ይፈናቀ ላል? በማንነቱ ለምን ይጠቃል?” ብለው በዐደባባይ የተሟገቱት ፕሮፌሰር አስራት ወ/ደየስን አገዛዙ ህክምና በመከልክል ሕይወ ታቸው እንዲያልፍ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

በወቅቱ የዐማራ ክልል ገዥ ፓርቲ የነበረው ብአዴንም የወንጀሉ ተባባሪ እንደሆነ አንዘነጋውም፡፡ጥያቄው፣ አሁንስ በሥልጣን ላይ ያለው የዐማራ ብልጽግና በዚህ ጉዳይ አቋሙ ምንድን ነው?

“እወክለዋሁ” የሚለው ማኀበረሰብ አንድ በአንድ እየታደነ እንዲ ጠፋ ተስማምቷል ወይስ “እጃችሁን ከሕዝቤ ላይ አንሱ?” የማለት ዐቅም የለውም? የሚል ነው፡፡ ፍርዱን ለታሪክና ለሕዝብ ብተወ ውም፤ ፍትሕን ለማግኘት በሕጋዊ መንገድ የማደርገውን ጥረት እቀጥልበታለሁ፡፡

በመጨረሻም፣ ዘመኔን ሙሉ ደረቱን ለጥይት ሰጥቶ ሕዝብንና አገርን በሚያገለግል ሙያ ላይ ያሳለፍኩ ብሆንም፤ ባለቅኔው

ዮፍታዬ ንጉሤ፡- “ኢትዮጵያ አገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!” ያሉበትን ዐውድ በሚያስታውስ መልኩ፣ ሆን ተብሎ ህክምና በመከልከል ህይወቴ እንዲያልፍ የሚደረገው አሻጥር ያሳዝነኝ ይሆናል እንጂ፤ ለሕዝቤ ያለኝን ውዴታና ግዴታ ስንጥር ታህል እንደማይሸርፈው ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡


ከሰላምታ ጋር!
ብ/ጄ ተፈራ ማሞ
ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣
ለዐማራ ሕዝብ፣
ለሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣
ለሚዲያዎች፣
ለማኀበረሰብ አንቂዎች፣

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *