የመኖሪያ ኪራይ ቤት እና የንግድ ቤቶች ኪራይ አዲስ በወጣው የግብር ክፍያ የተነሳ በተከራዮች ላይ 60 በመቶ የዋጋ ጭማሬ አስከተለ።

0
0 0
Read Time:40 Second

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፤ ” ከጣሪያ እና ግድግዳ ግብር ” ጋር በተያያዘ አንዳንድ አከራዮች በተከራዮች ላይ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ መሆኑን በክትትል ደርሼበታለሁ አለ።

የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም  ባደረገው ውይይት ማንኛውም አከራይ የቤት ኪራይ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መጨመር የማይቻል መሆኑን መወሰኑ ያስታወሰው አስተዳደሩ፤ ማንኛውም አከራይ የቤት ኪራይ እስከ ሰኔ 30 /2015 ዓ.ም ድረስ መጨመርም ሆነ ተከራይ ማስወጣት የማይቻል መሆኑን አሳውቋል።

ከጣራ እና ግድግዳ ግብር ጋር በተያያዘ አከራዮችከፍተኛ ግብር ተጥሎብናልበማለት በተከራዮቻቸው ላይ ከፍተኛ የኪራይ ጭማሪ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

ለአብነት አንድ የንግድ ተቋም ፤ የተጣለብኝን ከፍተኛ ግብር አሁን ባለው ኪራይ መሸፈን ስለማልችል ብሎ በተከራዮች ላይ  60% ጭማሪ እንደሚደረግ በመግለፅ ዝግጁ እንዲሆኑ አሳስቧል።

ሌሎች በተመሳሳይ ” ከፍተኛ ግብር ተጣለብን ” በማለት ተከራዮቻቸው ላይ የኪራይ ገንዝብ እየጨመሩ እንደሆነና ይህን የማያደርጉትንም እንደሚያስወጡ እየገለፁ እንደሚገኙ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ አ/አ ቤተሰቦች ተጠቁሟል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *