በአዲስ አበባ ከተማ ሥር የሚገኙ ዕድሮች ሕጋዊ ግብር ከፍዮች እንዲሆኑ አስገዳጅ መመሪያ ትግባራዊ ሊሆን ነው።

0

Gonder, Ethiopia - January 19, 2012: group of unidentified people dressed in traditional attire during the Timkat holiday, the important Ethiopian Orthodox celebration of Epiphany.

0 0
Read Time:1 Minute, 7 Second

ዕድሮች ሕጋዊ እንዲሆኑ ምዝገባ ማድረግ የሚያስችል አዋጅ ቢኖርም አስገዳጅ መመርያ ባለመዘጋጀቱ፣ ምዝገባ እንዲያደርጉ የሚያስችል መመርያ ነው ብለዋል፡፡

‹‹የዕድሮችና የዕድር ምክር ቤቶች የምዝገባና ዕውቅና አሰጣጥ›› የተሰኘው መመርያ፣ ዕድሮች በተለመደው ባህላዊ አሠራር ከቀብር ባሻገር ወደ ልማት መግባት እንዲችሉ፣ ዕድሮችና የዕድር ምክር ቤቶች ሕጋዊ ሆነው እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ የተዘጋጀ መሆኑን ያብራራል፡፡

በመመርያው መሠረት የሚመዘገቡበትና ዕውቅና የሚያገኙበት ሥርዓት በወረዳና በክፍለ ከተማ ሲሆን፣ በአንድ ወረዳ ወይም በአንድ ክፍለ ከተማ ከአንድ በላይ የዕድር ምክር ቤት ማቋቋም እንደማይቻል መመርያው ይደነግጋል፡፡

በእያንዳንዱ የዕድር ምክር ቤት የሥራ አመራር አባላት ቁጥር ከ12 በላይ መብለጥ እንደሌለበት ተቀምጧል፡፡

መመርያው ተፈጻሚ የሚሆነው በአዲስ አበባ ከተማ ሥር በሚገኙ ዕድሮችና የዕድር ምክር ቤቶች ላይ ሲሆን፣ የማስፈጸም ሥራውን የሚያከናውነው ቢሮው የምዝገባ ሥርዓት መዘርጋት፣ ችግሮችን መፍታት፣ መረጃዎችን መሰብሰብ፣ የፋይናንስ አስተዳደር አደረጃጀትን ማጠናከርና ማገዝ፣ እንዲሁም ወደ ልማት የሚገቡበት መንገድ የማመቻቸት ሥራዎች እንደሚጠበቅበት በመመርያው ተገልጿል፡፡.

የዕድር ምክር ቤቶች የምዝገባ መሥፈርትን በተመለከተ ማሟላት የሚጠበቅበት ማስረጃዎች መካከል የዕድር ምክር ቤት አባላት ስምና አድራሻ፣ የተመዘገበ ሀብት፣ የሥራ አመራር ኮሚቴ አባላት የተደራጀ ፕሮፋይል፣ በዕድር አባላቱ ጠቅላላ ጉባዔ የፀደቀ የኦዲት ሪፖርት ማቅረብ ይጠቀሳሉ፡፡ ቢሮው ከዕድሮች የቀረበለትን ማመልከቻ መርምሮ ሲያረጋግጥ የአገልግሎት ክፍያ እንዲፈጸም በማድረግ፣ በሁለት ቀናት ውስጥ ምዝገባውን በማጠናቀቅ የምዝገባ ማረጋገጫ የምስክርነት ወረቀት ይሰጣል ሲል መመርያው ይገልጻል፡፡

የዕድሩ ወይም የዕድር ምክር ቤቱ የምዝገባ ፈቃድ ከሚሰረዝባቸው ምክንያቶች አንደኛ ከአባላት ሁለት ሦስተኛ በሆነ ድምፅ እንዲሰረዝ ጥያቄ በሚቀርብበት ጊዜ፣ ሁለተኛ ዕድሩ የምዝገባ ፈቃዱን ከተሰጠበት ዓላማ ውጪ መገልገሉ በቢሮው ሲረጋገጥ፣ ሦስተኛ ሐሰተኛ ሰነድ በማቅረብ የተመዘገበ መሆኑ በቢሮው ሲረጋገጥ ሊሰርዝ እንደሚችል በመመርያው ተደንግጓል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *