የኢትዮጵያን አየር ክልል ጥሶ የገባ አውሮፕላን ትናንት ሌሊት 4 ሰዓት ላይ በአየር ሃይል ተመትቶ መውደቁ ተገለጸ

0
0 0
Read Time:1 Minute, 18 Second

ለህወሓት ቡድን የጦር መሳሪያ በመጫን በሱዳን አልፎ የኢትዮጵያን አየር ክልል ጥሶ የገባ አውሮፕላን ትናንት ሌሊት 4 ሰዓት ላይ በአየር ሃይል ተመትቶ መውደቁ ተገለጸ

ትናንት ሌሊት 4 ሰዓት ላይ የኢትዮጵያን መዳከም የሚፈልጉ፤ ለዚሁም ለዘመናት የሚንቀሳቀሱና ህወሃትን በመደገፍ ላይ የሚገኙ ታሪካዊ ጠላቶች ንብረት እንደሆነ የሚታመን አውሮፕላን ለሽብር ቡድኑ የጦር መሳሪያ ጭኖ በሱዳን አልፎ የኢትዮጵያን አየር ክልል ጥሶ ሲገባ በጀግናው አየር ሃይል ተመትቶ መውደቁ ተገልጿል።

ሠራዊቱ የአገሩን ሉዓላዊነት ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ በላቀ ኹኔታ ዝግጁ መሆኑም ተገልጿል።

በአገር መከላከያ ሠራዊት የመከላከያ ህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊ ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ላለፉት በርካታ ወራት ከፍኛ ወታደራዊ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው አሸባሪው ህወሃት ካለፉት ኹለት ሳምንታት ጀምሮ ኃይሉን ለውጊያ ሲያስጠጋ ነበር።

በየጊዜውም ተኩስ እየከፈተ የአገር መከላከያን ሲተነኩስ መቆየቱንም ነው ያነሱት።

ቡድኑ መንግስት የዘረጋውን የሰላም አማራጭ ከቁብ ሳይቆጥርና የሰላም ሂደቱ ቴክኒካሊ ፈርሷል ብሎ መግለጫ ባወጣ ማግስት ነሐሴ 17 ቀን 2014 ሌሊት 11 ሰዓት ላይ በቆቦ ግራና ቀኝ ባሉ አካባቢዎች፣ በዞብል ተራራ፣ በቢሶበርና በወትወት ውጊያ መክፈቱን ገልጸዋል።

በዚህም የተኩስ አቁም ሥምምነቱን ማፍረሱን ጠቅሰው፤ የሽብር ቡድኑ እየላከ ያለው ጀሌ በአገር መከላከያ ሠራዊትና በጸጥታ ሃይልች እየተለበለበ ነው ብለዋል።

ሜጀር ጀኔራሉ አክለውም፤ በሱዳን አድርጎ የአየር ክልላችንን ጥሶ በሁመራ ሰሜናዊ ክፍል በኩል ወደ ትግራይ ሊያልፍ የነበረና ለሽብር ቡድኑ የጦር መሳሪያ ሊያቀበል የነበረ የማንንቱ ያልታወቀ አውፕላንም በጀግናው አየር ሃይል ሌሊት አራት ሰዓት ላይ ተመትቶ መውደቁን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስደፈር የሽብር ቡድኑን እየጋለቡ ያሉ ሃይሎች ቢኖሩም የአገር መከላከያ ሠራዊትና ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ለማስክበር በተጠንቀቅ ላይ መሆናቸውን ጠቅሰዋል

በቀጣይም የሽብር ቡድን አገር የማፍረስ ህልሙን ትቶ ወደ ሰላማዊ መፍትሔ ካልመጣ እስከመጨረሻው እርምጃ ለመውሰዱ ሙሉ ዝግጅተ መደረጉን ጠቅሰዋል።

አሁን የመከላከል እርምጃ እየተወሰደ ሲሆን፤ በቀጣይም የማጥቃት እርምጃዎች እንደሚኖሩ ነው ሜጀር ጀኔራሉ የጠቀሱት።

Source: Abbay Media

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *