በኢትዮጵያ ታሪክ የማይነገርህን እንካ!!
Read Time:35 Second
(በኢትዮጵያ ታሪክ የማይነገርህን እንካ)
ጃንሆይ በድሬደዋ ከተማ ታዋቂውን እና በእስልምና አስተምሮ እጅግ እውቀት ከነበራቸው የአፍሪካ ሊቅ አንዱ የነበሩትን ሼክ ኡመር አዛሪን በድሬደዋ እቤታቸው በመገኘት ሲጎበኟቸው። በነገራችን ላይ ጃንሆይ ቁድስ ቁርዓንን በጥንቃቄ ኮሚቴ አዋቅረው፣ በራሳቸው ወጪ ወደ አማርኛ አስተርጉመውታል።
በዚህ ምስል ሁለት ነገርን ውሰድ፣
አንድ
ጃንሆይ ድሬደዋ ማረፊያ ቤተመንግስት አላቸው። ሼሁን ቤተመንግስት መጥራት ይችሉ ነበረ። ደሳሳ ቤታቸው ሄዱ። በፍቅር ሰላም አሏቸው። (ምስሉ ይናገራል)
ሁለት
ሼሁ ጃንሆይ ሲመጡ ከወንበራቸው ወርደው ሰሌን ላይ በመቀመጥ ንጉሱን አከበሯቸው።
ይህም የእኛ ታሪክ ነው።
(የጭቆና ታሪክ ብቻ እየመዘዙ ትውልድን ያበላሹ ብዙ ናቸው። የጭቆና ታሪክ እንኳ ድሮ አሁንም አለ። መሰልጠን ትናንተን ለመማሪያ በመተው ነጋችንን ማሳመር ነበረ)
ይህ ሀሳብ ገዢ ነው። ከዚህ ሀሳብ ጋር የሚቃረን መውደቁ አይቀርም። የጊዜ እንጂ የሰው ንጉስ የለውም‼
Source ✍? Muktarovich Ousmanova