ተሰፋዩ ታደሰን ያባረረው ኢዜማ ብርሃኑ ነጋን ለምን ከፓርቲው አባልነት አልሰረዘም?

0
0 0
Read Time:49 Second

ኢዜማ የፓርቲዉ አባል የሆኑት ተስፋዬ ታደሰ ከመንግስት ሹመት በመቀበላቸዉ ከፓርቲው አባልነት መሰረዛቸውን አስታወቀ

ሰኞ ጥር 22 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የኢዜማ የምርጫ ክልል 15 አባልና የቀድሞ የኢዜማ የአዲስ አበባ ዞን ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ሰብሳቢ እንዲሁም በአዲስ አበባ የጋራ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት የኢዜማ ተወካይ የነበሩት ተስፋዬ ታደሰ ፓርቲው የጣለባቸውን ሀላፊነትና የፈጠረላቸውን መልካም እድል ለግል ጥቅም በማዋል ከፓርቲው አመራር እውቅናና ፈቃድ ውጭ የቦሌ ክፍለ ከተማ የህዳሴው ግድብ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ሀላፊ ሆነው ከገዢው ፓርቲ ሹመት ተቀብለዋል ሲል ፓርቲዉ አስታውቋል።

የፓርቲው ሥራ አሰፈፃሚ የቀረበላቸውን የሹመት ጥያቄ እንዳይቀበሉ ያስቀመጠላቸውን ግልፅ ትዕዛዝ በመተላለፍ በድርጊታቸው በመፅናታቸው ጉዳዩ በፓርቲው ብሔራዊ ህግና ደንብ ተርጓሚና አስፈፃሚ ኮሚቴ ሲታይ መቆየቱንም የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ – ኢዜማ ገልጿል፡፡

የዲሲፒሊን ኮሚቴው ተስፋዬ ታደሰ የተሰጣቸውን ሹመት በመልቀቅ ለፓርቲው በ 15 ቀናት ውስጥ ሪፖርት እንዲያደርጉ፤ ካልሆነ ግን ከአባልነታቸው እንዲሰረዙ ብሎ በቀን ታህሳስ 22/2015 ባሳለፈው ውሳኔ ተጨማሪ እድል ሊሠጣቸው ቢሞከርም ሊጠቀሙበት ባለመፍቀዳቸው ከአባልነታቸው ሰርዣቸዋለሁ ብሏል።

በዚህም መሠረት ከዛሬ ጥር 22/2015 አንስቶ ተስፋዬ ታደሰ ከኢዜማ ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌላቸው እና የሚያከናውኑት ማንኛውም ተግባር ኢዜማን እንደማይወክል ፓርቲዉ አስታዉቋል።

__

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *