1 0
Read Time:1 Minute, 0 Second

ከኢያሱ ኤፍሬም ገ/ሐና ፡ ለንደን ጥር 22 2015 ፡ 2023 ጃንዩወሪ 30, ሰኞ

2013 ለ25 ሺ የላይቤሪያ ተማሪዎች የተሰጠውን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የፈተና አንዳቸውም ባለማለፉቸው የተደናገጡት የላይቤሪያ የትምህርት ሚኒስትሯ የፈተና ውጤትን “የጅምላ ፍጅት” ብለውታል፡፡ በኢትይጵያ የተፈፀመውን ምን እንበለው? የትውልድ ፍጅት? ቢንስ ነው፡፡

https://youtube.com/watch?v=dDQ7FRUr6qg%3Fstart%3D17

ጥሎብን የተማረ እንወዳለን የተማራ እናከብራልን በተማራ እንመካለን፡፡ ስለ ትምህርት ያለን ግምት ክብር እና ስፍራ ከፍተኛ ነው ፡፡ እንግሊዞች ከዋሻ ሳይውጡ እኛ ፊደል ቀርፀን መማር ማስተማር ጅምረናል፡ አክሱም የገነባነው በሊሂቃን የሂሳብ ( ጂኦሜትሪ/ የመአዘን) ጥናት እና ስሌት ነው፡፡ ስነቁሳዊ ህግጋትን (የፊዚክስ) ቀመርን ተጠቅመን ነው ላሊበላ የጂኦሜትሪ ውጤት ነው፡ ጠላ ስትተምቅ ፡ ጠጅ ስትጥል ፡ አረቄ ስታወጣ የስነ ቅመም ህግ ( ኬሚስትሪ) አውቀህ ነው፡፡ ከዘሮች ሁሉ ጤፍን ለይተህ ስታበቅል እና ምግብ ስታደርገው የስነሕይወት እውቀትን ተጠቅመህ ነው፡፡ ቀለምም በትጥብጠህ ፡ ቆዳ አለስልሰህ መፅሃፍትን ስትከትብ እውቀት ላይ ተመስርተህ ነው ፡፡ ይህን ያልኩት ለጉራ ለወሬ አይደለም እኛ ከእውቀት ጋራ ያለንን ዝምድና ቁርኝት እና ውህደት የሺ አመታት ታሪክ እንዳለው ለማሳየት ነው፡ ፡ እኛ እና እውቀት ፡ እውቀት እና እኛ ያለንን ዝምድና በይበልጥ ለማወቅ በኢትዮጵያዊን እውቀት ዙሪያ 25 መፅሀፍትን የከተበውን የውንድማችንን የመጋቢ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደስን ስራዎች መመልከቱ ከበቂ በላይ ምስከር ነው፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *