የመንግስት አካላት ሕግ ሲጣስ የሕግ አፍራሾች ተባባሪ ሆነው በመገኘታቸው እጅግ አሳፋሪ እና አንገት የሚያስደፋ ድርጊት ነው ብላለች
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፤ መንግስት ” በሃይማኖት መካከል ጣልቃ አልገባም “/” ገለልተኛ ነኝ ” የሚሉ ንግግሮችን እና ሃሳቦችን ቢያራምድም መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን ከዚህ ፍፁም ተቃራኒ መሆኑን እየገለፀች ትገኛለች።
ቤተክርስቲያን ህገወጥ ናቸው ብላ ያወገዘቻቸው አካላት የመንግስትን የፀጥታ አካላትን ሽፋን እያገኙ፤ የቤተክርስቲያን ስርዓትም በከፍተኛ ሁኔታ እየተጣሰ መሆኑን ገልፃለች።
ቅዱስ ሲኖዶስ፤ በተለያዩ ክልሎች እና የፌዴራል መንግሥት በሚመራቸው ቦታዎች ውስጥ በሚገኙ የቤተ ክርስቲያኗ አህጉረ ስብከት የሆኑትን ሥርዓተ አምልኮዋን የምትፈጽምባቸው በየመዋቅሩ የሚገኙ አስተዳደር ቢሮዎችን ከሕግ አግባብ ውጭ የቤተ ክርስቲያኗ እምነት ተከታይ ያልሆኑ ግለሰቦችን በማካተት በመንግሥት ልዩ ኃይል ድጋፍ በመውረር እና በመስበር የሕግ አግባብነት በሌላቸው እንዲሁም መብት እና ጥቅም ሳይኖራቸው በማሸግ ቤተ ክርስቲያን ላይ ወረራ እየተፈጸመባት ይገኛል ብሏል።
በሻሸመኔ የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ የሰው ህይወት ጠፍቷል፣ ጉዳት ደርሷል።
በጭሮ/ ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የጸጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ ወደ ምእመናን መወርወራቸውና ተኩስ ከፍተው እንደበር ቤተክርስቲያና ገልጻለች።
ዛሬ በጭሮ ምእመናን ከጠዋት ጀምረው ቤተ ክርስቲያኗን ሲጠብቁ የነበረ ሲሆን የዞኑ የጸጥታ ኃይል “በሁለታችሁ አንገባም” በማለት ገለልተኛ ለመሆን ሞክሮ ውሏል። ነገር ግን ምሽት ላይ ከክልል የመጣ ትእዛዝ ነው በሚል የክልሉ ልዩ ኃይልን ጨምሮ ተኩስ በመክፈት አስለቃሽ ጭስ ወደ ምእምናን መወርወሩ ተገልጿል።
ቤተክርስቲያኗ ፤ የመንግስት አካላት ሕግ ሲጣስ የሕግ አፍራሾች ተባባሪ ሆነው በመገኘታቸው እጅግ አሳፋሪ እና አንገት የሚያስደፋ ድርጊት ነው ብላለች።