0 0
Read Time:5 Minute, 59 Second


ልዑል ራስ መኮንን፤

ለዑል ራስ መኮንን ወልደሚካል ጉዲሳ የተወለዱት አንኮበር ነው። አንኮበር ከቀደምት የአክሱም እና የላስታ ቀጥሎም ከጎንደር ነገሥታት በአንድ በኩል ብቻ ትውልድ ካላቸው ውስጥ በመካከለኛው የሀገራችን ክፍል በተለይም በዘመነ መሣፍንት ጊዜ ጀመሮ ከታውቁት ከሸዋው ንጉሥ ሣህለሥላሴ ተወላጅነት ያላቸው ናቸው።

የሸዋው ንጉሥ ሣህለሥላሴ በአንኮበር ከተማ መናገሻቸውን አድርገው ሲኖሩ ሦስት በውል የታውቁ ልጆችን ወልደዋል፤ ኃይለመለኮት ሣህለሥላሴ የዳግማዊ ምኒልክ አባት፣ ራስ ዳርጌ ሣህለሥላሴ የለዑል ራስ ኃይሉ ዳርጌ አባት፣ ራስ ኃይሉ የራስ ካሣ አባት፣ ልዕልት ትላኝወርቅ ሣህለሥላሴ የልዑል ራስ መኮንን ወልደሚካኤል ጉዲሳ እናት ሲሆኑ፤ ልዑል ራስ መኮንን ለዳግማዊ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት የአክስታቸው ልጅ ናቸው።

Ras Mekonnen


የሸዋ አማራ ነገሥታት ከሸዋ አብቹ ሥልጡን ክርስቲያን ኦሮሞዎች ጋር ጋብቻ አላቸው። እንደሚታወቀው እመት እጅጋየሁ የዳግማዊ ምንሊክ እናት ኦሮሞ ናቸው። ራስ መኮንን በአባታቸው በኩል የሸዋ አብቹ ኦሮሞ ናቸው።

ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል የራስ ተፈሪ መኮንን በኋላ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴን እናት ከማግባታቸው በፊት ሌላ ሚስት አግብተው ይልማ መኮንን የሚባል ልጅ ወልደዋል፤ ቀጥሎ ያገቧቸው ሚስታቸው የጅማው አባ ጅፋር አሊን ልጅ የሺእመቤት አሊን ነው። የሺመቤት አሊ ከእስልምና ቤተሰብ የተገኙ ሲሆን፤ ከልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ ተፈሪ መኮንን በኋላ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴን ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያን ወልደው በወጣትነት እድሚያቸው በወሊድ ምክንያት ሕይወታቸው ያለፈ ናቸው።

እንግዲህ የሸዋ ነገሥታት ከንጉሥ ከሣህለሥላሴ ጀምሮ በልጃቸው በንጉሥ ኃይለመልኮት ተሻግሮ በዳግማዊ ምኒልክ ቀጥሎ እስከ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ድረስ የዘለቀው የሸዋ ዘመም የነጋሲነት ትውልድ በወቅቱ ሥልጡን ከሚባሉት ክርስቲያን የሸዋ ኦሮሞ ተወላጆች እንዲሁም ከእስልምና ሃይማኖት ነበራቸው የጀማ ኦሮሞዎች ጋር ጋብቻ ያላቸው መሆናቸውን እንረዳለን ።

ልዑል ራስ መኮንን በዳግማዊ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት የሐረር ጠቅላይ ግዛት አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመው ሲያስተዳደሩ ከእመት የሺመቤት አሊ ራስ ተፈሪ መኮንን ወይም ቀዳማዊ ኃይለሥላሴን እዚያው ሐረር ልዩ ስሙ ኤጀርሳ ጎሮ በሚባል ቦታ ተወለዱ። ቀዳማዊ ኃይልሥላሴ እትብታቸው የተቀበረው ሐረር የትውልድ ሀራቸው ነው። ሐረር ወስጥ ቀድመው የሠፈሩት አደሬዎችና ሐራሪዎች በኃላም ቆቱዎችና ብሌኖች እንጅ ኦሮሞዎች አይደሉም።

ሐረር በቀደምት እረጀም ዘመናት ካስቆጠሩት የሀገራችን ጥንታዊ ታሪክ ጠገብ ከተሞች መካከል ወደ አንድ ሺህ ዘመን የሚጠጋ ታሪክ ያላት ናት። ሐረር በበርበራ ወደብ አማካኝነት የጥንት የንግድ በርና ማዕከል በመሆን ረጅም ዘመናት ያስቆጠረ የታሪክ ትውስታ ያላት ሲሆን በጥንት ዘመን ፑንት ከቀኝ ግዛት በኋል “ሱማሌያ” ተብሎ በሚጠራው የአፍሪካ ቀንድ ጫፍ አጎራባች ስትሆን የመሬቱ ነባር ባለቤቶች ሐራሪና አደሬዎች፣ ብሌኖችና ቆቱዎች እንጅ ኦሮሞዎች አይደሉም።

የልዑል ራስ መኮንን የሐረር ጠቅላይ ግዛት ሆኖ መሾም ከጊዜ በኋላ በበርበራ በኩል ይደረግ የነበረው የሀገራችን የባህር በርና ንግድ ወደ ሰሜን ባህረ ነጋሽ ከጣሊያን ወረራ በኋላ የዛረው “ኤርትራ”፤ አዶሊስ ምጽዋና አሰብ ሲደራ፤ እየተዳከመ የመጣው የምሥራቁ ፈርጥ የሐረር ዝና እንደገና ያንሠራራበትና የማዕከላዊ መንግሥት ተቋማት የተከፍቱበት፣ ሆስፕታልና አቢያተ ክርስቲያናት የታነጹበት ሰላማዊ እንግዳ ተቀባይ የፍቅር ሕዝብ የሆነው የሐራሪ፣ የአደሬና የብሌንና የቆቱ ሕዝቦች ጀሮና ጌጥ ሰምና ወርቅ ሆነው የሚኖሩበት ተናፋቂና የፍቅር ሰላማዊ የሀገራችን ክፍል ሆኖ ቆይቷል።

ሐረርን ልዑል ራስ መኮንን ብቻ ሳይሆኑ የመጀመሪያው ልጃቸው ደጃዝማች ይልማ መኮንንም የሐረር ጠቅላይ ጋዥ አስተዳደሪ ሆነው ተሹመው ሀገሩን አቅንተዋል። ቀጥሎም ራስ ተፈሪ መኮንን ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ተብለው እስከሚነግሡ ድረስ የዚሁ የሐረር ጠቅላይ ግዛት አስተዳዳሪ በመሆን ሐረርን በሰላማዊ በተረጋጋ መንገድና በፍቅር በስምምነት አስተዳድረዋል። ቀጥሎም የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ልጅ ልዑል መኮንን ኃይለሥላሴ የሐረር መስፍን ሆነው ሐረርን መርተዋል።

ሐረር በኢትዮጵያ ሀገራችን በአራቱም ማዕዘናት የሀገራቸውን ሉዋሏዊነት የሕዝባቸውን አድንነት በማስጠበቅ መስዋዕትነት የከፍሉ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በሐረር ገነት ጦር ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ሰልጥነው የወጡበት የሀገር ታሪክ ፍቅር ፍሬ ያፈራበት የካራማራ ድል የታወጀበት ደማቅ ባለውለታ ሆና ያገለገለች የምሥራቅ ጮራ የሆነች ዝነኛ የሀገራችን ኢትዮጵያ ዐቢይ ክፍል ነች።

አንድ ሀገር እስካለንበት ዘመን ደረስ ተጠብቆ ሊቆይ የቻለው በየዘመኑና በጊዜው የተሾሙ መሪዎች በተሰጣቸው ኃላፊነትና አደራ ጠብቀውና አስከብረው በማለፋቸው እንጅ ሀገር ቁጭ ብሎ ትውልዱን የሚጠብቅ አይደለም፤ ሀገር ጠባቂ የነበረውና ያለው ሆኖ ስለቆየ ለዛሬው ትውልድ መኖሪያ ምድር መሆን ችሏል። ሀገር ወድቆ የተገኘ ገጸ በረከት ሳይሆን በደምና በአጥንት ግብር የተጠበቀ ነው። ለዚህ ነው የሀገራችን አርበኞች፡፟-

“ተላላ ነው፤ ሀገር ተላላ ነው፤
ይሄዳል የጓዛል እንደ ሰው፤
በየበሩ ሆኖ ጀግና ካመለሰው።”

በማለት የሀገራቸን ደንበር በደም ባጥንታቸው ጠብቀውና አስጠብቀው ያቆዩልን ሲሆኑ፤ ዛሬ በበታችነት ስሜት የገነኑ ሕወሀታዊ የአፍራሽነት ምልምል በመሆን ያለምንም የታሪክ ተጠያቂነትና ኃላፊነት በጎደለው መልኩ፣ “ኢትዮጵያ ትውደም፣ ነፍጠኛ ይውደም፣ ምንሊክ ይውደም!” የሚለው የሞራል ዝቅተኞች ስብስብ የአክራሪ “ኢስላማያ ኦሮሚያ” ደካማ ትውልድ በኢትዮጵያ ስነ-ሕይወት ውስጥ ያቆየው ጥሪትና ቅርስ እንዲሁም የታሪክ አሻራ የለም፣ ያበረከተውም አስተዋጾ አይታወቅም።

ያልሠሩትን ወይም ያልደከሙበትን ሀገር ማፈረስ ቀላል ሊሆን ይችላል፤ በጥንት ታሪክ ነጻ ሆና የቆየች ሀገርን ጠብቆ ለትውልድ ማቆየት ግን ከባድ ነበር። ሕሊና ባለው ሰው አዕምሮ የጋራ ሀገር የጠበቀ ታሪክ ያቆየ ሕዝብ የሚመሠገን እንጅ በቆሸሸ አፍ የሚወቀስና በአሰቃቂ ሁኔታ የሚገደል አልነበረም።

የሐረር የዘመናዊ ሥልጣኔ ሕይወትና ታሪክ ከልዑል ራስ መኮንን እና ከልጆቻቸው ጋር የተጣመረ ታሪካዊ ክስተትና ሕልውና ያለው ነው። ልዑል ራስ መኮንንም ሆነ ልጆቻቸው ቀዳማዊ ኃለሥላሴ ሐረርን በልዩ ፍቅር የሚወዱትና የሚንከባከቡት የሀገራችን ክፍል ነበር።

ልዑል ራስ መኮንን ከሐረር ጠቅላይ ግዛት ጀምሮ የሀገራችን የውጪ ጉዳይ ምንስትር በመሆን፤ የሀገሪቱ የውጪ ድፕሎማቲክ ልዑክ በመምራት፤ ወደ እንግሊዝ ወደ ፈረንሳይ ወደ ጣሊያና እና ጀርመን ሀገራት በመሄድ የሀገራችን ዘመናዊ አስተዳደርና የውጪ ግኑኝነት ካቀኑትና የሃኛው ክፍለ ዘመን የሥልጣኔ ንቃተ-ሕሊና በውል የተረዱ እጅግ ሲበዛ ቅን መንፈሳዊ፣ ትግሥተኛ፣ የተረጋጋ መንፈንስ የነበራቸው ልዑል ነበሩ። ከላይ ስማቸው ከተጠቀሰው ታላላቅ የውጪ ሀገራት የከፍተኛ የጦር መሪና የዲፕሎማሲ ግኙኝነት የላቁ ዓለም አቀፍ እውቅና ያላቸው ልዩ ልዩ መዳሊያዎችን ተሸለመዋል።

ሉዑል ራስ መኮንን በጣሊያን የመጀምሪያው ወረራ ጊዜ በጦር አዝማችነት በአንባላጌ በኩል የተሰልፈውን የኢትዮጵያ ጦር እየመሩ የአድዋ ድል ባለቤት ካደረጉን ግንባር ቀደም ተዋቂ አርበኞች መካከል ስመ ጥርና ዝነኛ ነበሩ።

ሀገራችን ኢትዮጵያ እስልምና በተፈጠረ በአራት ዓመቱ በመካ መዲና አምልኮታቸውን መፈጸም ያልቻሉ የመጀመሪያዎቹ ሙስሊማን፤ በአረብ የቆሪሽ ተወላጆች ከፍ በሎ አንገታቸው ዝቅ ብሎ ባታቸው እየተቆረጠ ከእነ ሕይወታቸው ሲቀበሩና ሲሳደዱ፤ በስድስት መቶ አሥራ አራት ዓመተ ምህረት በንጉሥ አርምሐ ዘመነ መንግሥት ለመጀመሪያ ወደ ኢትዮጵያ በጥገኝነት የተቀበለችው ሃማኖት ነው።

ይህም ማለት እምነተ አይሁድና ክርስትና በኢትዮጵያ ውስጥ ከተሰበከ ከአንድ ሺህ ሰባት መቶ ዓመታት በኃላ እስልምና መነሻውን በቀጥታ መካ መዲና አድርጎ በጥገኝነትን ወደ ኢትዮጵያ የገባ ሃይማኖት ነው።

የዓለም ታሪክ ይህን ታሪካዊ ክስተት፤ ኢትዮጵያ በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ በትወልድ ሀገራቸው መኖርና ሃይማኖታቸውን ማምለክ ላልቻሉ ሙስሊማን ስደተኞች ጥገኝነትን የፈቀደችና የሰው ልጆችን የመኖር በነጻነት የማምለክ መብታቸውን (Human right and Refugee States ) ያከበረች ሀገር ሲል በታሪክ ማኅደሩ ውስጥ መዝግቦታል።

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የሚታወቀው የኢትዮጵያ እስልምና አምልኮት፤ ኢትዮጵያዊ እስልምና ባህሪ ያለው ነበር። ይህም ማለት እስልምናውን ተቀብሎ ኢትዮጵያዊ ባህሉንና ታሪኩን አማክሎ ተቻቸሎ የሚኖር እስልምና ማለታችን ነው።

የእስልምና አምልኮት በኢትዮጵያ መልኩን እየቀየረና የአክራሪነት ተዋስያን ተጠቂ እየሆነ የመጣው በተለይም ከዛፍና ከባህር ጣኦት አምልኮት በቀጥታ ውደ እስልምና የገቡት ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ቁጥር እየበዛ ሲመጣ ነው።

አክራሪነት ማለት ከዘማናዊነት ጋር የሚጋጭ፣ ያልነበረበትን የሚቀማ፣ ከሌሎች ሃይማኖቶች ጋር ተቻችሎ የመኖር ሕሊና ወይም ትግሥት የሌለው፣ በሃይማኖት ተሸፍኖ የሥልጣን የበላይነት የሚሻ፤ ቀደምት ታሪክና የታሪካዊ አሻራዎችን የሚደመሥስ፤ በጭካኔ የሰው ልጆችን ሕይወት ማጥፋት የእምነቱ አካል የሚያደርግ፣ የሚገድልና የሚያሳድድ ማለት ነው።

ጠቅለል ባለ መልኹ ኃይልና ጉልበት ባገኛችሁ ጊዜ ከእስልምና የወጣውን ወይም ያፈነገጠውን ሁሉ አሳዳችሁ ግዱላቸው አጥፏቸው ሀብትና ንብረታቸውን ውረሱ አቃጥሉ በሚል ክፉ አጋንንታዊ መርህ የሚመራ ማለት ነው።

የሐረር ከተማ ነባር ሰዎች የሐራሪ፣ የአደሬና የብሌን ተወላጆች ይልቅ ሥርዓት ጋብቻን ዘግይቶ የተቀበለውና ከባህርና ከዛፍ አምልኮት ቀጥታ ወደ ስልምና የመጣው አንድ አክራሪ ኢስላም ኦርሞ ከሁለትና ከሦስት ሚስቶች ብዙ ልጆችን በመወለድ በከፍተኛ ቁጥር ተስፋፍቶ የሐረርን ቀደምት ዲምግራፊ ባህልና ትፍውፊት በቀላሉ በማመናመን ያልተለመደ አክራሪነት እንግዳ ደራሽ ነብሰ ገዳይነት እንደዋዛ ሊያቆጠቁጥ ቻለ።

የፍቅር ሀገር በመባል የምትታወቀው ዘነኛዋ ሐረር ሃይማኖቱ ከጠባብ የአክራሪ አግላይነት ፓለቲካ ጋር የተሳከረባቸው ማንም ስልጣን ፈላጊ ደንቆሮ እንደ ከብት በመንጋ የሚነዳው ማስብ የተሳነው የሰፈረባት የሰው ልጅ በአሰቃቂ ሁኔታ የሚገድለባት፤ ሀብትና ንብረት የሚቃጠልባት፣ ጽንፈኝነት የሰፋበት፣ የመሪዋን ኃውልት ያፈረሰች አደራ በላተኛ ክሕደት የተፈጸመባት ከታማ ሁናለች።

ሐረር የኢትዮጵያ ምስራቃዊ ፈርጥ የደጋጎቹ እንግዳ ተቀባዮች ሐራሪ፣ አደሪዎችና ብሌኖች የታላላቅ አሚሮችና ሡልጣኔቶች ብርቅየ ተናፋቂ ከተማ ሆና ሳለ ዛሬ የካሃዲዎች የነብሰ ገዳዮች የአረማውያን ዋሻ ሁናለች።

የምሥራቅ ጮራ፣ የበርበራ ገነት፣ የሰላም ማማ ፣ የፍቅር አውደማ፣ የልዑል ራስ መኮንን ግርማ፣ ሐረር እንኳን ሰው ጅብ የሚለምድባት ከተማ፤ ሰው አርደው የሰው ደም የሚጠጡ የአረማውያን ከተማ ሁናለች።

የማይሰርቅ የማይዋሸው የሐራሪ የአደሬው የብሌኑ፣ የሚስረቀረቅ ድምጽ፣ ውበት ከደም ግባት የተሰጣቸው የወይዛዝርቱ የፍቅር ከተማ ሐረር፤ ወይስ ዛሬ የመሪዋን ኃውልት የምታፈርስ፤ የታሪክ አሻራ የሚደመሰስባት፣ የሰው ሕይወት በግፍና አሰቃቂ በሆነ መልኩ የሚጠፋባት ንብረት የሚዘረፍባት አደራ በላተኛ የካህዲያን ከተማ ሐረር።

መንገሻ መልኬ

ሎንዶን 2020

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
100 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *