‹‹የኃይሌ ሪዞርት ሲቃጠል የመከላከያ እና የፖሊስ ኃይል አባላት እየሳቁ እሳት ይሞቁ ነበር››

0

‹የኃይሌ ሪዞርት ሲቃጠል የመከላከያ እና የፖሊስ ኃይል አባላት እየሳቁ እሳት ይሞቁ ነበር››የሻሸመኔ ከተማ አስተዳደርናፀጥታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ

0 0
Read Time:2 Minute, 45 Second

‹‹በመንግሥት የፀጥታ አካላት ፊት ሕይወትም ንብረትም ጠፍቷል››የሻሽመኔ ከተማ ነዋሪዎች

‹‹የኃይሌ ሪዞርት ሲቃጠል የመከላከያ እና የፖሊስ ኃይል አባላት እየሳቁ እሳት ይሞቁ ነበር››የሻሸመኔ ከተማ አስተዳደርናፀጥታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል ተከስቶ በነበረው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት ተጠቂ የነበሩ ዜጎች የሚገኙበትን ወቅታዊ ሁኔታ የሚገመግም በብሔራዊ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የሚመራ ቡድን በማቋቋም ችግሮች ወደ ተከሰቱባቸው ከተሞች በማቅናት የችግሩን ጥልቀት እና ተጎጂዎች ያሉበትን ወቀታዊ ሁኔታ ተመለከተ፡፡

ቡድኑ በሻሸመኔ ከተማ የተለያዩ ቦታዎች የደረሱትን ውድመቶች ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡ስለ ሁኔታው ያነጋገራቸው ጉዳት የደረሰባቸው የከተማው ነዋሪዎች የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት ከተሰማበት ከሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ከምሽቱ 4፡00 ሰአት ጀምሮ በከተማዋ ግርግር የሚመስሉ እንቅስቃሴዎች ይስተዋሉ እንደነበር ገልፀዋል፡፡የተጠና በሚመስል ሁኔታ በእለተ ሰኞ ለሊት (ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም)ለማክሰኞ (ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም)አጥቢያ ከለሊቱ8፡00 ሰዓት ጀምሮ ጩኸት ከየቦታው መሰማት መጀመሩን እና በተመረጡ ቤቶች ላይ ቤንዚን እየተርከፈከፈ ቤቶች ይቃጠሉ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ይህ ሲሆንም በቦታው የደረሰው የመከላከያ ሠራዊትም ሆነ የከተማዋ ፖሊስ ሠራዊት ቆሞ ከማየት በዘለል ትእዛዝ አልተሰጠንም በሚል ምክንያት ሁኔታውን ለመቆጣጥር ባለመፈለጋቸው በሰው ሕይወት እና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጥፋት እንዲደርስ ሆኗል ብለዋል፡ ፡ ‹‹እኛም ሕይወታችንን ለማትረፍ ምንም ሳንይዝ ወደ አብያተ ክርስቲያናት በመሮጥ ሸሽተን አምልጠናል›› በማለት ክስተቱን መለስ ብለው አስታውሰዋል፡፡

ስለክስተቱ እንዲያስረዱ የሻሸመኔ ከተማ አስተዳደርና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ስንታየሁ ጥላሁን ተጠይቀው በሰጡት አስተያየት ‹‹ክስተቱ እጅግ የሚያሳዝን ከመሆኑም በላይ የክልሉ መንግሥት ለፌደራል መንግስት ፈቃድ ባለመጠየቁ እና በመዘግየቱ የመከላከያ ሠራዊት በሰዓቱ በቦታው ቢገኝም ትእዛዝ ስላልደረሰው ምንም እርምጃ አልወሰደም፡፡የኃይሌ ሪዞርት ሲቃጠል የመከላከያ እና የፖሊስ ኃይል አባላት እየሳቁ እሳት ይሞቁ ነበር››ብለዋል፡፡

የኢዜማ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ እና የአጥኚ ቡድኑ መሪ ዋስይሁን ተስፋዬ ተጎጂዎቹ አሁንም የደህንነት ስጋት እንዳለባቸው መታዘባቸውን ገልፀው መንግሥት አስፈላጊ የሚባለውን ቁሳቁስ እያቀረበላቸው አይደለም ብለዋል፡፡ «በጎ አድራጊ ዜጎች ናቸው ለተጎጂዎቹ አስፈላጊ የሚባለውን ድጋፍ እያደረጉ ያሉት እንጂ በመንግሥት በኩል እየተደረገ ያለው ድጋፍ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን ለመታዘብ ችለናል።»ያሉት ድርጅት ጉዳይ ኃላፊው፣ተጎጂዎቹ ተጠልለው የሚገኙበት ሁኔታም ለኮቪድ በሽታ በሚያጋልጥ ሁኔታ ውስጥ ስለሆነ ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡

በተመሳሳይ በአርሲ ዞን ዴራ ከተማ መድሐኒዓለም ቤተክርስቲያን ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ዜጎችን ለመጎብኘት ወደስፍራው ያመራው ቡድን ያነጋገራቸው ሲሆን በቤተክርስቲያኑ ተጠልለው ከሚገኙ ዜጎች ጋር በተደረገው ውይይት ወቅት የቡድኑ አባል ባንቲገኝ ታምራት(ዶክተር) ‹‹እኛ እዚህ ቦታ የተገኘነው ክስተቱ ከተፈጠረበት እለት ጀምሮ ያሳለፋችኋቸውን መራርና ቃላት የማይገልፁትን በደል ከናናንተው አንደበት ሰምተን እስካሁኗ ደቂቃ በምን ሁኔታ ውስጥ እንዳላችሁ ለመረዳት እና ወደፊትም የዜግነታችሁ መብት እስኪከበር የእናንተ ድምጽ ለመሆን ነው›› ብለዋል።

በዴራ ከተማ መድሐኒዓለም ቤተክርስቲያን ተጠልለው የሚገኙት ኢትዮጵያዊያን ከሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የደረሰባቸውን ግፍ ለቡድኑ ያስረዱ ሲሆን ችግሩ ከተፈጠረ ከ50 ቀን በላይ ቢሆነውም እስካሁን ከመንግሥት የረባ እርዳታ እንዳለተደረገላቸው እና ወደ መኖሪያ ቦታቸው ለመመለስ የተደረገ ጥረት እንደሌለ ጠቅሰው አሁንም ዛቻ እና ማስፈራሪያው መቆም እንዳልቻለ አስረድተዋል። «ኢዜማ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በመነጋገር ለዘለቄታዊ መፍትሄ የምናገኝበትን ሁኔታ ያመቻችልን።» ሲሉም ጠይቀዋል፡፡

ችግሮቹን ያዳመጡት ኢዜማ አመራሮች ፓርቲው በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች በፍጥነት መልሰው የሚቋቋሙበት እና ደህንነታቸው ለዘለቄታው ተረጋግጦ የሚኖሩበት ሁኔታ እንዲመቻች ማድረግ የሚቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል። አመራሮቹ በከተማዋ ስለተፈጠሩ ሁኔታዎች የዴራከተማ ከንቲባን ለማነጋገር ያደረጉት ጥረት ከንተባው በጽሕፈት ቤታቸው ባለመኖራቸው ምክንያት ሊሳካ አልቻለም፡፡

የብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን ያካተተው ቡድን በሥራ እንቅስቃሴው ወቅት በሻሸመኔ ከተማ«ያለማንም ፈቃድ ከተማችን በመግባት ፎቶ አንስታችኋል»በሚል በኃይል ወደ ከተማ አስተዳደሩ ጽሕፈት ቤት ተወስዶ የነበረ ቢሆንም በከተማ አስተዳደሩ ጽሕፈት ቤት በተካሄደ ውይይት ችግሮቹ በመግባባት ተፈተው ቡድኑ ወደ ጉብኝቱ እንዲመለስ ተደርጓል፡፡ ቡድኑ ጉብኝቱን አጠናቆ ወደ አዲስ አበባ መግባቱን እና ዝርዝር ሪፖርት በማጠናከር ላይ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ዝርዝር ሪፖርቱ በቅርቡ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ የቡድኑ መሪ እና የኢዜማ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ዋስይሁን ተስፋዬ ለዜጎች መድረክ ገልፀዋል፡፡

Source – የዜጎች መድረክ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *