የአውሮፓ ኅብረት የፌዴራልና የትግራይ ክልል መንግሥታትን ለማግባባት ጥረት መጀመሩ ተሰማ

0
0 0
Read Time:49 Second

የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ግንኙነትና ደኅንነት ፖሊሲ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆሴፕ ቦሬሌ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር
የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ግንኙነትና ደኅንነት ፖሊሲ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆሴፕ ቦሬሌ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር
የአውሮፓ ኅብረት የፌዴራልና የትግራይ ክልል መንግሥታትን ለማግባባት ጥረት መጀመሩ ተሰማ፡፡

የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ግንኙነትና ደኅንነት ፖሊሲ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆሴፕ ቦሬሌ የተመራ ልዑካን ቡድን ከሁለት ሳምንት በፊት ከፌዴራል መንግሥትና ከትግራይ ክልል መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች፣ እንዲሁም በሁለቱም መንግሥታት ገዥ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር መወያየታቸውን የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡

የኅብረቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በወቅቱ ተገናኝተው መምከራቸውን ሪፖርተር ከምንጮች ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኅብረቱ ከፍተኛ ልዑካን ወደ ትግራይ ክልልም በማምራት፣ ከክልሉ መንግሥት አመራሮች፣ እንዲሁም ከደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ጋር መወያየታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ይኼው ቡድን በሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች ጋርም በአካል ተገናኝቶ የመከረ ሲሆን፣ ይህንንም የሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ አባል የሆኑ አቶ ጌታቸው ረዳ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ሕወሓትን በመወከል ከኅብረቱ ልዑካን ጋር ውይይት ካደረጉት መካከል አንዱ እሳቸው እንደነበሩ የገለጹት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የኅብረቱ ከፍተኛ ልዑክ በፌዴራል መንግሥትና በትግራይ ክልል መንግሥት መካከል

Source: Ethiopianreporter

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *