ጠ. ሚንስትር ዐቢይ :- በኢትዮጵያዊነት የምትሠራ ነህ ወይስ በጠላት መሣሪያነት ! ? አፍረጥርጠው ! ! ማንን ፈርተህ!!!
ኮማንደር አሰፋ ሰይፉ
Yigrem
ለይ ! ! !
ሚያዝያ 19/13
ጠ. ሚንስትር ዐቢይ :-
በኢትዮጵያዊነት የምትሠራ ነህ ወይስ በጠላት
መሣሪያነት ! ?
አፍረጥርጠው ! ! ማንን ፈርተህ!!!
“ኢትዮጵያ ሆይ ረስቼስ እንደኾን ቀኜ ትርሳኝ!
አላሰብሁሽ እንደኾን ምላሴ ከታነጋዬ ትጣበቅ
ከደስታዬ ኹሉ በላይ ኢትዮጵያ ሆይ ከፍ!ከፍ!
ባላደርግሽ…”
(ከጥቅምት 9፤ 1968 ስደት ከጀመርሁበት ዕለት ጀምሮ ካፌም ኾነ ከልቤ ያልተለየ
(ከዳዊት መዝሙር ~ ትርጉሙን ከሚያውቅ መጠየቅ ክብደቱን ያስተምራል!!)
Artimodorous to Julius Ceasar
“ Read mine first, for, mine is a suit that touches Ceasar Nearest!” ሽማግሌው ሊነግረው የፈለገው ሊገድሉት መዘጋጀታችወን ነበር፡፡ ሲዘር አልሰማም፡፡ ገባ! ተገደለ! ሮምንም እንድትመሰቃቀል አደረገ፡፡ አንተም በሙሉ ብታነብብ ይሻልሃል!!
ክፍል አንድ
ለመተዋወቂያ ያህል
በንግግርሮችህ ኢትዮጵያዊነትን የምታንጸባርቅ በመሆንህ በውስጥም በውጪም ያለነው ኢትዮጵያውያን በሙሉ፦ በሚባል ደረጃ፦ ልባችንን ሰጥተንህ ነበር፡፡ “ ከእባብ እንቁላል ርግብ … ይቻላልን” የሚሉም አልጠፉም ፡፡
ባኹኑ ጊዜ ስለአገሬ የሚሰማኝ በ66 ዓም የተሰማኝ ዓይነት ነው፡፡ በዚያን ጊዜ ስጋቴን ለአንድ መስፍንና ለብዙ መኳንንት፦ ሳሳውቅና ለክቡራን ሚኒስትሮችም ሳካፍል ስጋቴ ስጋታቸው መኾኑን ከመግለጽ በላይ ከነሱ መፍትሄ ባለማግኘቴ
“ ለውጥ በሰላም ለሰላም !”
በሚል ርዕስ ስጋቴን ለሕዝብ በሚያዝያ ወር አደረስሁ፡፡ መፍትሄ የመሰሉኝንም!!! ፍሬ ነገሮቹም፦
_ ን. ነገሥቱ ፍጹም ሥልጣንን ለሕዝቡ በምክር ቤት አማካይነት እንዲመልሱ፦
_ ጠ. ሚኒስትሩም የሥልጣን ዘመኑ በጊዜያዊነት ታውቆ በ6 ወራት እንዲወሰን ( ትምሕርቱና ችሎታው የማይጠየቅ ቢኾንም)
_ ግዳጁም ለአገራችን እቅድ/ ፕሮግራም አለን ከሚሉት ከ 3 እስከ 5 የሚኾኑትን በምክር ቤት አወዳድሮ 2/3ኛ ድምጽ የሚያገኘው የሥራ ጓደኞቹን መርጦ በንጉሠ ነገሥቱ አጸድቆ በሽግግር መንግስትነት እንድዲታወቅ:-
የሽግግር መንግሥቱም ግዳጅ፦ መሻሻል ላይ የነበረው ሕገ መንግሥት ያለምንም ተጽዕኖም ኾነ ጥድፊያ ሲጸድቅ በጸደቀው ሕገመንግሥት መሠረት
ሕዝብ አስተዳዳሪውን እንዲመርጥ ነበር፡፡ በዚህ ምርጫ ሥልጣኑን ለአሸጋጋሪው የለቀቀው ጠቅላይ ሚኒስትርም የመወዳደር መብቱ የተጠበቀ ይኾናልበማለት፡፡
ይህ ካልኾነ ግን እርስ በርስ በመፋጀት የወገን ማለቂያ
የጠላት መሳለቂያ ፦ የወዳጅ መሰቀቂያ እንኾናለን!፡ ነበር፡፡ (አገሬንና ወገኔን በማውቀው መጠን!! ከዚያ የሚብስ ነገር አልጠበቅሁም ነበር፡፡) ግን ይሄንን ያነበቡና የሰሙት የቀኃሥ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሃሳቤን እንዳብራራላቸው ጠይቀውኝ አዎንታዬን ሲያገኙ ቀጠሯችንን ማስታወቂያ መለጠፊያቸው ላይ ለጥፈውት ፕሮ. መስፍን ፦ መሬት ይቅለለውና፦አይቶ በብዙ ፍለጋ ሲያገኘኝ፦ ኮስተር ባለ መልክ፦ ሰላምታ እንኳን ሳንለዋወጥ
_ ሌላ አሰፋ ሰይፉ ባሕር ኃይል ውስጥ አለ? ይለኛል
_ ጋሼ ፦ ባሕር ኃይል እያደገ ነው፡፡ የለም ልልህ ኣልችልም፡፡
_ ኮማንደርስ?
_ ኮማንደር እንኳን የለም፡፡
_ ታዲያ! አንተ ነህ … ንግግር ለማድረግ የምትመጣው?
_ አዎን!
_ __
_የአስተማሪዎቻቸውን… ስሞች ዘርዝሮ ‘ በሶሺያሊዝም ኮትኩተው ያሳደጓቸውን “ ቀስ በሉ! ረጋ በሉ!” ቢሏቸው ሊደበድቧቸው ተጋብዘውባቸው በስንት ግልግል መትረፋቸውንስ?
_ ሰምቻለሁ፡፡
_ ታዲያ፦ ‘ ቀስ በሉ! ረጋ በሉ!’ ስላሏቸው እንደዚያ ሲጋበዙባቸው አንተ እንዲያውም የተነሱበትንና የታገሉበትን ኹሉ አፍርሰህ የምትሄደው ምን ለመኾን ነው?
~ ጋሼ ፦አገራችን እጦርነት ዓይነት ኹናቴ ውስጥ እንዳለች ታምንልኛለህ?
_ በአዎንታ ራሱን ነቀነቀ፡፡
_ 3 _
_ እንዲያውም፡ ከጦርነት እባሰ ኹላንቴ ላይ መኾንዋንስ?
_ በማሰብ የበለጠ ጊዜ ወስዶ ከመጀመሪያው ባነሰ ፦ የግምባር አዎንታ አሳየኝ
_ ታዲያ! አገር በንዲህ ዓይነት ላይ እያለች፦ እንኳን አንድ ጊዜ መለዮ ለባሽ የነበረ ማንኛውም ዜጋ እጦር ሚዳው ተገኝቶ ቢችል አንድ ኹለቱን ገድሎ ባይችል አቁስሎ ይመለሳል እንጂ ከጦር ሜዳው ይሸሻል? ስለው፡፡ እጆቹን በብስጭት አራግቦ “ ጠበቅ ባለ ድምጽ “ እብድ!!! “ ብሎኝ ሄደ፡፡
_ 3_
በቀጠሮው ዕለትና ሰአት የአሜሪካው ም/ ፕሬዚዳንት ሂውበርት ሃምፈሪ በሌላ አዳራሽ ውስጥ ንግግር ያደርጉ ነበር፡፡ የእኛው ራስ መኮንን ሲኾን ድምጽ ማጉያው ወጪውንም ኹሉ ነበር፡፡ ጢም ብሎ ነበር!!!
ዋናው ይህንን ኹሉ ያስወተወተኝ በንግግሬ ውስጥ “ ሕዝብ ከመረጠው ፦ገብረማርያምነቱንም ኾነ መሃመድነቱን፦ ሃጎስነቱንም ኾነ በላቸውነቱን፡ ደበላነቱንም ኾነ ደንድርነቱን ወዘተ….በአጭሩ ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያን ታሪክና ዳር ድንበር አክብሮ ካስከበረ ልጆችዋንም በአቻነት እስታስተዳደረ ድረስ መሪዬ ነው፡፡” ማለቴን ለማበከር ነው፡፡ ይህን ያልሁትም በ1966 ዓም መኾኑ ይሠመርበት!! እንኳን ዱላ ጭቅጭቅ ሳይኖር በፍቅር ተለያየን!!!
ይህን ክፍል ከመዝጋቴ በፊት፦ ጽሑፌን ለአባቴ ሳሳይ በፈጣን አንባቢነቱ ጨርሶ ትክ ብሎ እያየኝ፦
“ስንት ቀፎ እንደቀሰቀስህ አስተውለሃል?” አለኝ
እኔም በአዎንታ መለስሁ፡፡ እንድቀጥል በግምባሩ አመለከተኝ፦ እኔም
_ ጠ. ሚኒስትሩና ባልደረቦቹ፦
_ የተማሪዎች ማሕበር
_ የአስተማሪዎች ማሕበር
_ የሠራተኞች ማሕበር አልሁ፡
“ሌላስ? “ አለኝ፦ ምንም የማያመልጠው አባቴ፦ እኔም
_ ጃንሆይማ ሕገመንግሥቱ ይሻሻል ብለዋል፦ ስል
“ እርሳቸውስ እንዳልከው ብለዋል፦ ሌሎቹስ
ጥቅማቸው የሚነካባቸው?” አለኝ
እኔም እነሱንም አስቤያቸዋለሁ፡፡ ስል
_ “ታዲያ ይህን ኹሉ እያየህ፦እያወቅህ! ለምን?” አለኝ
እኔም “ መመሪያህን በመከተል!” ስለው በግምባሩ እንዳብራራ አዘዘኝ፦
“ እግዚአብሔርህን ፍራ! ሕዝብን አክብር! ለኅሊናህ ተገዛ!” ያልከኝን ስለው?
_ ከእኔ ያገኘኸው መመሪያ ይህን ብቻ ነው?” ሲለኝ
አይደለም? ግን ለአኹኑ የተጠቅምሁት በሱ ነው፡፡ ስል፦ እንደመተከዝ ብሎ ቆየት አለና
“ አኹን አንድ ልጨምርልህ፦ በልመና!” ሲል እንደማቋረጥ ብዬ “ ከመቼ ወዲህ ነው የምትለምነኝ? እዘዘኝ እንጂ!” ስለው፦ ፈገግ እንደማለት ብሎ “ ይህን ልለምንህ!” ሲል ፦ ላቋርጠውም ሲዳዳኝ ዓይቶ በእጅ ምልክት አስቁሞኝ፦
“ በቀል የኔ ነው፡፡” ያለውን አንብበህ የለ?” ሲለኝ በአዎንታ መለስሁ፡፡ እርሱም
“ የምለምንህ ይህንን ትእዛዝ፡በምንም ምክንያት እንዳታፈርሰው ነው!”
እነሆ! የሰማያዊ አባታችንን ትእዛዝ፦ እንዳላፈርስ ምድራዊ አባቴ በዚህ ዓይነት አሰረኝ፡፡
እኔም የስደተኛነቴን የመጀመሪያዎቹን 16 ዓመታት በቢ ቢ ሲ ሬዲዮ በየሳምንቱ 2_3ተዬ አንዳንድዬም በበለጠ ዜና እንዳገኘሁ የደርግን መንግሥት እጠዘጥዝ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ በመሃላ የዛቱብኝ የመንግሥቱ የቅርብ ሰዎች እንደነበሩ ወዲያውኑ ደረሰኝ፡፡
የእምዬን ጉዳይ ስለምከታተል በ83 ዓም መንግሥቱ ካገር የመውጣቱ ጉዳይ ዘመድ ወዳጆቹን እውጪ ቁልፍ እሚባሉ ቦታዎች ሲመድብ ታየኝ፡፡ ስለዚህም
BBC NEWSNIGHT TV ( እንግሊዝ አገር ከነበርክና የዓለምን ጉዳይ ትከታታል ከነበረ ማወቅ አለብህ) ላይ
“አሜሪካ ፈርዲናንድ ማርቆስን ከፊሊፒንስ በማስወጣቱ ሕዝብ ሳይተላለቅና አገሪቱም ሳትጎዳ እንደዳነች አኹንም፦ አሜሪካ ከጸጥታው ጉባኤ ጋር ኾና መንግሥቱን ብታወጣና ሸንጎው የሽግግር መንግሥት ቢያቋቁም ደም ከምፍሰስ ንብረት ከመውደም ይድናል፡፡” ያልኩት መጋቢት ግማሽ ላይ ነበር፡፡ ጄምስ ጆና የሚባል አፍሪካዊ የተመ ረዳት ዋና ጸሐፊም ነበረ፡፡ ይህን ስል የአሜሪካንን ዐቅዋም አጥቼው ሳይኾን ድንገት ቢራራ በማለት ነበር፡፡
የመንግሥቱም ‘ መሄድ’ ልበለው? ከዛቱብኝ አገናኘን፡፡ ለማሳጠር ስለአድዋ 100ኛ የድል በዓል አከባበር የኢትዮጵያን ታሪክና ሕልውና በማጥፋት ላይ የነበርውን የጠላት መሣሪያና፦ ጠላት ! ቢጠይቁት ፦ “ ምን ያስፈልጋል? ከተከበረም እዚያው እቦታው ላይ መኾን አለበት!” ማለቱን ሰምቼ፦ ልበል ተነሮኝ፤፟ ለንደን በደመቀ መልክ ልናከበር ስንዘጋጅ ጀምሮ የተኪያሄደብኝን ተንኮልና ደባ የሚያውቅ ያውቀዋል፡፡የዛቱብኝ ከ26 ዓመታት በላይ የሚያደርጉትን አድርገዋል!ያደርጋሉም!! ፦ እኔም “በሰማዩ አባቴ ትእዛዝና በምድራዊ አባቴ ልመና “ተወጥሬ
“የሚጠሏችሁን ውደዱ፦ የሚረግሟችሁን መርቁ!” ባለው ትዕዛዝ ፀንቼ ስኖር፦በጠላት አስተምሕሮና መሪነት ተመርዘው በጠላት መሣሪያነት ታሪካቸውን የሚያጎድፉ/ ብሎም የሚክዱ፦ ወገኖቻቸውን የሚያባሉ ሲመጡ፦ ባድግሁበት ባህል ላይ እድሜና የአገር የወገን ሥቃይ ሲጨመር መድሃኒት የሚፈለገው ከፈጣሪ ስለኾነ ስጸልይ፦
_ ሻማ አበራለሁ፦ ሳበራም “ በጠላት መሣሪያነትአገር
ወገንን የሚያባሉትን እንደዚህ አንድዳቸው!”
_ ከሰል ሳቀጣጥልም “ እንደዚህ አክስላቸው! ድምጥማጣቸውንም አጥፋ! ስል
ቸሩ አምላክ ግብጽ ውስጥ የነበሩትን አይሁድ በፈርኦንና ሕዝቡ ይፈጸምባቸው ስለነበረው ግፍ “ ሃዘናቸውን ሰምቼ እንባቸውንም ዓይቼ..” ብሎ ሙሴን ልኮላቸው ሙሴም ሰብስቦ ወደአገራቸው ለማሻገር ባሕሩ ዘንድ ሰብስቦ፡ ጌታ በቸርነቱ ውሃውን ገምሶ እሥራኤላውያንን በደረቁ ሲያሻግር፦ ፈርኦንም ሠራዊቱን ከትቶ ሊያጠፋቸው/ሊመልሳቸው ተከትሎ ሲገባ ውሃውን መልሶ ፈሮንንና ሠራዊቱን ደምጥማጡን እንዳጠፋ በጠላት መሣሪያነት ኢትዮጵያን የሚያጠፉትን ልጆችዋን በየአገሩ የሚያንከራቱትትን… እያልሁ ርግማኔን ሳዥጎደጉድ የሰማዩ አባቴን ትዕዛዝ፦ የምድራዊ አባቴን “ ልመና!” ማፍረሴን የተረዳሁት በቅርቡ ነው፡፡
በቀጥታ በእኔ ላይ የፈጸሙብኝንና የሚፈጽሙብኝን እንጂ እነዚህን ማውገዜ ፦ መርገሜ ትእዛዝ ማፍረሴ መኾኑን አልተረዳሁም ነበር፡፡
ጡረታዬን ማግኘቴ ጥቅሙ አያጠያይቅም ግን ማንን ጠይቄ?? በቁም የሞተውን፦ የአገርን ታሪክ የናደና ወገንን በማበጣበት ለዘላለማዊ የውጪ ተበዥባዥነት ለማድረግ የሸጠውን?! አይታሰብም፡፡ እርሱን ሲገላግለን የተተካው ደግሞ “ የመለስ ሌጋሲ…” እያለ ሲያላዝን “ ነፍስህን ይማር!” ብዬ አለፍሁት፡፡
አንተ ስትመጣ ብዙ አዎንታዊ ነገር ባይም መቆየቱን መረጥሁ፦ ልቤ እሺ አላለምና!
አኹን፡ የበደሉኝ በአገር ምክንያት እንጂ በግል ኣለመኾኑን እንድገነዘብ ላስቻለኝ ጌታ ክብር ምስጋና ይግባውና ፦ ንስሃዬን ለማውረድ የገዳማትን እርዳታ ስለምፈልግ ጡረታዬን በምዑዘ ጥበባት ዲ. ዳንኤል ባልደረባነት ይከበርልኝና፦ በሊ. ጳጳስ ብፁዕ አባ መቃርዮስና (ማቴ. 23፡4) በማሕበረ ቅዱሳን ሊ. መንበር በኩል ሁለት መቶ ሺህ ብር ለገዳምት ተስጥቶልኝ ለሥርየት እንዲጸልዩልኝ በአደራ እጠይቃለሁ፡፡ ምዑዘ ጥበባትም “ ሳያውቀኝ! ሳይጠይቀኝ!” ሳትል እንድትፈጽምልኝ አደራዬ ጥብቅ ነው፡፡ እኔን ማግኘት አትቸገርም፡፡ ጥያቄዬን ለነርሱ አቀርባልሁ፡፡እንደነ ፕሮ. ሕዝቅኤል ያሉት በሃዘን ባልኩባቸው ሳይኾን ተመልሰው አገር ወገን ቢያገለግሉ ጥቅሙ የትዬእሌሌ! አይኾንም? ለመመለስ ደግሞ ዕውነትን መቀበልና ከነባር ኹናቴው ጋር በማገናዘብ ጠላት ምንያህል “ለወገን መጨራረሻ ለአገር ማፍረሻነት” እንደተጠቀሙባቸው ተንገንዝበው አገራቸውን ለመገንባት ወገናቸውን ከቱሃንና ቁንጫ ገላግለው ወደአለንበት ክፍለ ዘመን ለማድረስ ግዳጃቸውን እንዲወጡ ገዳማት እንዲማጸኑላቸው (እንዲማጸኑልኝ) ነው፡፡ አምላክ ምን ይሳነዋል?
አደራ! ልጄ ወንድሜ ዳንኤል!!!
የጸሎትን ነገር ሳነሳ አገራችን ከኹሉ በላይ የሚያስፈልጋትና የሚያድናት መኾኑን ምናልባት አንተ ፦ ጠ. ሚኒስትር:- ታስተምረኝ ይኾናል፡፡ ለክርስቲያኖቹ፦ ደቀመዛሙርቱ አንድ ርኩስ መንፈስ የተጠናወትውን ልጅ ማዳን አቅቷቸው ወደጌታ ሲያመጡትና ሲፈውሰው፦ ደቀመዛሙርቱ “ እኛ ለምን ልናወጣው አልቻልንም?” ሲሉት “ ይህ የሚኾነው በጾምና በጸሎት ብቻ ነው!” ያለውን ታብራራልናለህ፡፡ አንድ እንግሊዛዊ ደራሲ ደግሞ
ሃዋርድ ፓይል የሚባል ፦ ስለንጉሥ አርተርና አሥራ ኹለቱ ጀግኖቹ፦ ሲጽፍ፡
ንጉሡ በጠና ታምሞ አልጋ ላይ በነበረበት ወቅት ጀግኖቹ ኹሉ በጭንቀት ከብበውት ቆመው፦
“ ከኹሉም በላይ ለነፍሴ ጸልዩላት፡፡ በጸሎት፦ ይህ ዓለም ከሚያስበው በላይ ማድረግ ይቻላልና! “ ያለውንም ልጨምር ብዬ ነው፡፡ ቅ. ቁራንም ተመሳሳይ ትምሕርት ይኖረዋል ብዬ አምናለሁ፡፡
ፈጣሪ የጥፋት ውሃንና የሰዶም እሳትን በምድር ላይ ለምን እንዳመጣ፦ አኹንም አንተ፦ ጠ. ሚ. ልታስተምር ትችላላህ፦ የታወቀ ነው፡፡
ታዲያ ፦ አዲስ አበባ የነዚህ የጥፋት/የሃጢአት ተግባራት መናኸሪያ መኾኗንና ወደ ሌላ ከተሞቻችንስ ማራባቷን አታውቅም?! መልሱን ለአንተው ልተውና፦
ሊ. ትጉሃን ፦ መምሕር ደረጀንና ዶክቶር ሥዩም አንቶኒዮስን ለባለሥልጣኖችህና ለሃይማኖት ተቅዋማት ባልሥልጣኖች ባለህበት ገለጻ እንዲያደርጉላቸውና ፦ በኢ.ቲ.ቪም የመግለጽ እድል እንድታመቻችላቸው በአገር ድኅነት ስም በአጽንኦት እጠይቅሃለሁ፡፡
ክፍል ኹለት፦
በዚህ ክፍል አንተ ሥልጣን ያገኘህበት ወቅትና ቀ. ኃ. ሥ . ከስደት የተመለሱበትን ጊዜ በማመሳሰል አንድ ኹለት ቁምነገሮች አሳይቼህ ፦ ( ስደት ስል፦ የወጡት ጣሊያን ሕዝቡ ላይ ብቻ ሳይኾን እንስሳቱንና አራዊቱንም የሚያወድም መርዝ በአይሮፕላን ያዘንም ስለነበር፦ የን.ነገሥቱ መያዝም ኾነ መገደል በሕዝቡ ላይ ተስፋ መቁረጥን ለኢጣሊያን ድል ማረጋግጥን ስለሚያስከትል ጥቂት መሳፍንትና መኳንንት ጃንሆይ ከአውሮፓና ከአሜሪካ መንግሥታት የነበራቸውን ውል ( ከሊግ ኦቭ ኔሽንስ) ያስፈጽሙ ዘንድ ለሙግት መውጣታቸውንና ከመውጣታቸውም በፊት ራስ እምሩን ትግሉን ከወደ ጎሬ ኾነው እንዲያስቀጥሉ ማድረጋቸው ሊሠመርበት የሚገባ ታሪክ ነው፡፡
እንግሊዞች፦ እንዲያውም የ2ኛው ዓለም ጦርነት ቃልኪዳን አባላት ጀርመን ከሰሜን ወደ መሃከለኛው ምሥራቅ ( የነዳጅ እምብርትና) የስዌዝ መተላለፊያ ስትገሠግስ ጃፓን ደግሞ ወደዚሁ አካባቢ ስትገፋ ተሽቀዳድመው አካባቢውን ለመያዝ እንግሊዞችና ፈረንሳዮች ሙሶሊኒን ገፍተው ያስያዟትን ኢትዮጵያን ከጀርመን ከወገነችው ኢጣሊያን እጅ ማውጣት ግድ ኾነባቸው፡፡ ምስጢረ ብዙው የኢትዮጵያ አምላክ መሄጃው አይታወቅምና!!! ዝርዝሩን አልፌው እንግሊዞች ቀ. ኃ.ሥን ሱዳን ድንበር አስቀምጠው መሣሪያ ለታወቁ መኳንንት አሰራጭው፦ ን. ነገሥቱ በቅርብ እንደሚገቡ ወረቀት ባየር አገሩን ኹሉ አዳርሰው፡ ጣሊያንን መውጋቱ ተፋፋመ፡፡ _ በን ነገሥቱ ሥር በኮሎ. ዊንጌት የሚታዘዝ (ቀላል መሣሪያ የያዘ ሲታዘዝ ብቻ ይዟቸው የሚገባ ተደርጎ) ዋናው ጦር በደቡብ በኩል ገባ፡፡ ቆፍጣናውና ተጠራጣሪው አርበኛ ግን “ንጉሣችሁን አምጥተናል!” ብላችኋል፡፡ ካላመጣችሁ ለኛ ነጭ _ ነጭ ነው! እንግሊዝንና ጣሊያንን መለየት አንችልም!!!” እያለ ጃንሆይም፡ እንግባ! ብለው _ ዊንጌት እንደሚታዘዝ ሲያረጋግጥላቸው አንድ አዋጅ በሬዲዮ ለሕዝባቸው አስተላለፉ፡፡ ይኸውም ባጭሩ እዚህ ያበቃቸውን ፈጣሪያቸውን አመስግነው ለአርበኞች መሪዎች ኹሉ ጥብቅ ትአዛዝ፦ አስተላለፉ፡ ይኸውም፦ ባንዳ የተባሉት ወደነርሱ ሲመጡ በሰላም እንዲቀበሏቸው፡፡ ገንዘባቸውንም ኾነ መሣሪያቸውንም እንዳይነኩባቸው አዘዙ፦ ከዚህም አልፈው ወታደር ያልኾኑትን ልዩ ልዩ ሞያ ያላቸውን ጣሊያኖችንም በሰላም እንዲኖሩ መፍቀዳቸውን፡ አካትተው ነበር፡፡ እንግሊዝ ምኑ ሞኝ? የኢትዮጵያን ሥላጣኔ ለማፋጠን? ባለሞያ ጣሊያኖችን ጠራርጎ ወደየኮሎኒዎቹ ወሰዳቸው፡፡ ቀ. ኃ . ሥ ግን መጀመሪያ ላይ አንድ ሳንቲም፦ የእኔ የሚሉት 10 ወታደር ሳይኖራቸው አገራቸውን ገነቡ፡፡
“ እናት ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!”
የተባለው ለዚህ ነው፡፡
ዳዊት ያልደገመው አርበኛው ጀግና የትምሕርት ሚኒስትር ሊኾን ይችል ነበር? …
የሰላም ሽልማት የቀሩባቸው ምክንያት(ቶች)
የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን ሲያቋቁሙ ምዕራባውያን ሊያስቆሟቸው አይችሉም ነበር፡፡ ግን የካዛብላንካንና የሞንሮቪያን ሻጥር በመፍጠር “ ሰሜን አረብ አፍሪካና ጥቁር አፍሮካ ድርጅት!” እንዲፈጠር ተንኮል ታቅዶ ነበር፡፡
“እንኳን ይሄንና የዝምብ ጠንጋራ የሚያውቁት” አባጠቅል፦ በትንታጉ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትራቸው በአቶ ከተማ ይፍሩ ጥረት ግርማዊነታቸውም ወደ ኹለቱም ከተማዎች በመሄድ አሸነፉ!”
ታዲያ የአፍሪካ ኣንድነት ድርጅት አንጸባራቂ አባት (በ80ኛው ልደታቸው እንደተገለጸው) በ122 ገለልተኛ አገሮች ውስጥ በነበራቸው ታላቅ ክብር ላይ የሰላሙ ሽልማት ቢጨመር ለምዕራባውያን የማይዋጥ ስለነበር እንዳስቀሩባቸው መገንዘቡ የአስተሳሰብ ሚዛን ለመያዝ ይጠቅም ይኾን???!!!
አንተ ሥልጣን ላይ ስትወጣ በዚያው “ እቤትህ !” በሚባል ደረጃ መጠነኚያ ችግር ነበረብህ፡፡ ከጃንሆይ ጋር ግን አይመጣጠንም፦ እንዲያውም አይቀራረብም ፡፡ እስቲ በጥሞና ኹሉንም አስበህ አመዛዝነው፡፤ ፍረድም፡፤ የ” ትሕነግ”ን፦ ትቼ” አገር ውስጥም ኾነ እውጪ ካሉት ኢትዮጵያውያን ድጋፍህ ጋር ሲተያይ ተቃውሞህ እኮ እዚህ ግባ አይባልም ነበር፡፡ የአሜሪካን ዩኒቨርሲቲን ያጨናነቁ፦ ብዙ ዓለም ዐቀፍ ድርጅቶች ውስጥ ልምድ ያካበቱ ስንቱን ልቁጠር አገራቸውን ለማገልገል ሲጓጉ፡_ አንተ ምን አደረግህ?
የሚያፋጀውን ሕገ መንግሥት ለመለወጥ ሳትፈልግ…ሳታሞክር በ”ብሔርህ” ሰዎች ሰገሰግኸው፡፡ ብዙ ጊዜ “ መከላከያ ግቡ ሲሏቸው አይገቡም! ፈደራል ግቡ ሲሏቸው አይገቡም!” ትላለህ፡፡ ወጣት ኹሉ በሥራ አጥነት ከሚንገላወድ አልካቸው ድርጅቶች መግባት ጠልቶ ነው? መልሱን ለአንተ ከመተው ላፍርጥርጥልህ እድገትም ኾነ ሹመት በብሄርህ ብቻ፦ እንደ ትሕነግ ስላደረግህ ነው፡፡ ኦሮሞ ልዩ ኃይል ውስጥ የተሰሰጉት ለምንድን ነው? ሌሎች ብሔራዊ ክልሎችም? እድገትና ሹመት ኹሉ ለአንድ ብሔር በመደረጉ ነው፡፡ አማራው ክልል ውስጥ ግን ኃይል መገንባት አይፈቀድም!!!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶቅስ ቤ/ክ “ አገር ነው!” ብለህ አልነበረም? በዚህስ ዕምነት አልነበረም ሲኖዶሶቹን ያግባባኸው? ታዲያ “ ኢትዮጵያን ለማጥፋት አንዱ መጥፋት ያለበት እርሱ መኾኑን አታውቅም!?” በግሳጼ ተባልክ እንዴ?? እንዲያ የዞርክባቸው!!!
አብያተ ክርስቲያናት ሲነድዱ፦ ካህናትም ሲቃጠሉና ሲታረዱ ምን አደርግህ? እንዲያውም፦
እዚህ ላይ ቆም ብዬ “ ሕገመንግሥት !” ተብዬው ጸደቀ ተብሎ በተደረገው ግብዣ ላይ የተባለውንና ሾልኮ የደረሰኝን በጥሞና እንድታዳምጠውና እንድታጤነው በአደራ አካፍልሃለው፡፡ ከግብዣው ታዳሚዎች ውስጥ አንዱ፦ በእንግሊዝኛ
_ “በዚህ ሰነድ ኢትዮጵያን እጃችን ውስጥ አስገባናት
አይደል?” የሚል ነገር ስሰማ በድንጋጤ ፦
ዞር ብዬ ሳይ አራት የምዕራብ አገሮች አምባሳደሮች ናቸው አለ፡)
ኹለተኛው፦ “ አዎን … ግን” ይልና ዝም ሲል
ሌላው “ ‘ግን!’? ምን? ምን ቀረ?”
የመጀመሪያው “ ኦርቶዶቅስን ደኅና እያዳከምን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እኮ አገር ወዳዶች ናቸው፡፡ እነሱንም በአክራሪዎች መበረዝ አለብን፡፡” ብሎ ለዚህ ነው “ መሣሪያቸው ፦ መለስ የ’ይድረስ_ የይድረስ’ ሙስሊም ወገኖቻችን ላይ ያመጣውን ያመጣው፡፡ ሙስሊም ወገኖቻችንም በቀላሉ ሊገላገሉ የቻሉት፤፡ ሲቀጥሉ
“ ኦርቶዶቅስ ላይም እኮ ተጨማሪ ሥራ መሥራት አለብን፦ በወንጌላውያን ብዙ መበረዝ አለብን፡” የተባለውም ተቀባይነት አግኝቶ ሥራ ላይ ውሎ የለ?
አንተ ከሾምካቸው ውስጥ ሾልከው የገቡ ሌሎች ክርስቲያኖች ስንት ይኾኑ?
የአማራውና የኦርቶዶቅሱ እልቂት ብቻ ሳይኾን ፍጹም አረመናዊ ወንጀል እኔ የትም ሰምቼ አላውቅም፡፡ ድርስ እርጉዟን ሆዷን ቀድዶ ሽሉን መጣል!! ይባስ ብሎም፦ የወንጀል ውድድር ያለ ይመስል፦ እናቲቱን ማሳቀፍ!! ጎልማሳ ወንድማቸውን አብሮ ከተሰለፈበት ማንጅራቱን መትቶ እሳት ውስጥ መጨመር፦ እሳቱ በዝቶበት ተንከባልሎ ሲወጣ መልሶ እሳቱ ውስጥ መጣል!!
በግፍ የተጨፈጨፉትስ፦ ወገኖቻቸው ከግፈኞች አምልጠው፦ ለቀብር እንኳን ሳይበቁ በገዛ አገራቸው ለአራዊት የተዳረጉት?! ይህ ኹሉ በአንተ፦ በዐቢይ አሕመድ ዘመን መኾኑ የጽሑፍ ብቻ ሳይኾን የምስል ማስረጃም አለ፡፡
ለዚህ ኹሉ ወንጀል አንተ፦ ጠ. ሚ. ዐቢይ፦ ምን አደረግህ? የሠለጠነ ፖሊስ ባለበት ስንቶቹ ለፍርድ ቀረቡ?
አቶ ለማ የክልላችሁ ገዢ በነበረበት ወቅት ም. ወለጋ ወንጀሉ ሲጧጧፍ “ እኛ እኮ ኃይሉም መሣሪያውም አለን፡፡ እርስ በርሳቸው ተጋደሉ እንዳይሉን ነው እንጂ!” ሲል አንተ ሳታውቅ ነው? በይሉኝታ ወንጀል ሲፋፋም ሰው በግፍ ሲጨፈጨፍ ዝም ይባላል? ኅሊና የሚባለው የሰውን ልጅ በበጎ የሚመራው እናንተ ዘንድ ሲደርስ በነነ እንዴ? ታሪክን ባትፈሩ ለልጆቻችሁ አታስቡም? ይህ የአረመኔንት ወንጀል “ አቤት” ሲያስብል፦ ሰውን ገድለው መብላትም ተጨመረ፡፡ በእንዲህ ዓይነት በግፍ የተጨፈጨፈውንስ በየሃይማኖታቸው ተለይተው በወግ ተቀበሩ? በአንተ ጊዜ፦ በኦሮሞው! ይህማ የ” ሰው” ሥራ ይኾናል? በግሬደር ገፍቶ አፈር ማልበስ ሲቀልል!!! አይሰቅቅህም? አታፍርም? በአንተ፦ በአንተ፦ በዐቢይ አሕመድ ጊዜ፦ በኦሮሞ መንግሥት ይህ ሲደረግ??!! ዋሽቶ ለማዋረድ እንኳን ቦታ አልሰጠህም፡፡ ሃቁ ከልብ ወለዱ ከፍቷልና!!!
እስቲ ወደ ሻሸመኔው ዕልቂትና ግፍ መለስ እንበል፡፡ የሻሸመኔው ከንቲባ ደንግጦ ለክልሉ ፕሬዚዳንት ሲደውል መጀመሪያ ያገኘውን መልስ አላስታውስም፡፡ ኹለተኛ ሲደውልና አደጋው እንደተቃረብ ስጋቱን/ፍርሃቱን ሲያመለክተው የክልሉ ገዢ መልስ “ ዝም ብለህ ተኛ!” እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ አንዱ አንድምታ፦የመጀመሪያው ስልክ ጥሪ ሲደርሰው ለአንተ እንዳስታወቀህ ያመልክታል፡፡ ይህ ከኾነ “ ዝም ብለህ ተኛ!” ያንተ መመሪያ መኾኑ ነው? ይህማ ባይኾን እንዴት ሽመልስን ተጠያቂ ሳታደርገው ትቀር ነበር? ይላል፡፡ የእኔ ብጤ ሞኙ፡፡ እሳቱ ደግሞ ዐቢይ መቼና ማንን ለእንዲህ ዓይነቱ ቁጥር ስፍር ለሌላቸው፦ በአማራና በኦርቶዶቅስ ላይ ለተፈጸሙት ወንጀሎች፦ ለወደሙት አብያተ ክርስቲያናትና ካህናት እንዲሁም ንብረቶቻቸው ማን ተጠያቂ ሲደረግ አይህ? ሲባል መልሱ “ በዕውቅ፦ በመመሪያ ለተፈጸሙት ወንጀሎች፦ ለፈጻሚዎቹ ሽልማት እንጂ!” የሚሉም አይጠፉ፡፡ በጥንት ዘመን የፖሊስ ነገር ሳይታወቅ እንኳን፦ አበው በአውጫጭኝ ወንጀለኛ አያመልጣቸውም ነበር፡፡ ባለሥልጣኖቹ ለሕዝቡ ፍቅር፦ ለሃላፊነታቸው ክብር፦ ለፈጣሪያቸው ፍርሃት ነበራቸውና!!!
አኹን ደግሞ ለአገር ለወገን ስጋቴ አላስቀምጥ አላስተኛ ሲለኝ ስለአሳስብኩህ ጉዳዮች አንድ _ አንድ ልበል፦ በቅደም ተከተል
1_ ከኦጋዴን ስለተፈናቀሉት 1 ሚሊዮን ያህል ኦሮሞ
ወገኖቻችን፦
ጌታ ለአገራችን ካስቀረላት ጥቂት ባለሥልጣኖች አንዱ ፦ ፕሬዚዳንት ሙስጠፌ ፡ “እባካችሁ መልሷቸው! ኹሉ ነገር ይመለስላቸዋል!” እያለ ሲወተውት አቶ ለማ መገርሳ እንዳለው፡” አባገዳዎችን በብዙ ችግር አሳምኖ!” ወደአዲስ አበባና አካባቢዋ በቅጽበት አሰፈራቸው፡፡ በምን አመጣቸው? ወጪውን ማን ቻለ? መስፈሪያቸውንስ? የምን እጅ አለበት አያስብልም?
እንግሊዞች ጣሊያንን ለማስወጣት ከረዱን በኋላ ኦጋዴንን አንለቅቅም ብለው በ 12 ዓመታት ውትወታና ጭቅጭቅ ጃንሆይና መንግሥታቸው ለማስለቀቅ ቻሉ፡፡ እውስጧ 6.4 ትሪሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የነዳጅ ጋዝ ክምችት እንዳለ ብቻ ሳይኾን እርሱንም ለማውጣት የስደት አገሬ ጠ. ሚ. የነበረ ባሌ ድረስ መጥቶ አንተንና አቶ ለማን ብቻ ሳይኾን አንድ ሌላ ሰውም ስሞ መዋዋሉ ተነገረ፡፡ የሚገርመው እንኳን ጠ. ሚ. የነበረ ተራውም እንግሊዝ ነጩንም አቅፎ ሲስም አይቼ አላውቅም እንኳንስ ጥቁርን፡፡ ጎበዝ! ለአገሩ ጥቅም ሲል አደረገው፡፡ ይህን ኹሉ በመጥቀስ፦ እንኳንስ አገራችን ከዕዳ የምትገላገልበትን ሃብት ይዛ፦ አሸዋም ይዛ መሬታችን መለቀቅ የለበትም፡፡ ይህን በማድረግ ለኦጋዴን ነጻ አውጪ ግምባርና፦ ለታላቋ ሶማሌ ባለሕልሞች ማምቻቸት ይኾናል፤ ብዬ ስማጸን የአባ ገዳዎችን ትብብር ለማግኘት ፕሮ. መረራንም ጨምሩ የሚል ምክር አክዬ ነበር፤፡ “ ታላቋ ሶማሌ፦ ታላቋ ትግራይ” የሚባሉትን አባዜዎች ማን እንዳመጣብን፡ ታውቅ የለ? አኹን ደግሞ እንግሊዞች በቅኝ ገዥነት አካባቢያችንን ይዘው በነበረበት ወቅት፦ መሃሏ፦ ዕድሜ ለምኒልክ የማትደፈር ስለነብረች፦ ምዕራቡን ክፍላችንን በአካባቢው ቅኝ ገዥ እጥቅም ክልል ውስጥ (sphere of influence) አስገብተው ነበር፡፡ አኹን ያንን ክፍል በሱዳን አስወርሮ መቀመጡ እንደምሥራቁ መኾኑ ነው? እመልስበታለሁ፡፡
2_ ከጎለምስሁባት አገሬ ከኤርትራ ጋር “ ሰላም
ተፈጥሮ” ማየቱ ኹለተኛ ልደት ዓይነት ነበር
የተሰማኝ፡፡ ነገር ግን የሰሜኑ ጦር በትሕነግ ሥር
መኾኑ እጅግ ያሳስበኝ ነበር፡፡ የትሕነግን እኩይ
ተግባር እንደሚያውቅና እንደሚያስታውስ ኹሉ፡፡
ከዕለታት በአንዱ ዕውቁን የኢሳት ጋዜጠኛና የሰባዊ
መብት ተቆርቋሪውን ወንድማገኝ ጋሹን ለአንድ
ጉዳይ ስደውልለት፡ አይሮፕላን ማረፊያ እንዳለና
ወደ አዲስ አበባ ሊጓዝ መኾኑን ሲነግረኝ፦ “ቀደም ብለን ብንማክርበት ጥሩ ነበር፡፡ግን ባለን መጠቀም መሞከር አለብን በማለት፦ የሚሄደው የአንተን የመጀመሪያው የጠ.ሚ. የኢሐድግ ስብሰባ በአዋሳ ሊከታተል መኾኑን ሳረጋግጥ ” ከባድ እንደኾን እረዳለሁ መሞከር ግን አለብን፡፤ የአገር ሽማግሌዎችን የማግኘት ዕድል ካገጠመህ እባክህ ‘ ልጆቻችን ናፍቀውናል!! ካየናቸው ረጅም ጊዜ ኾኗል፡፡ አኹን ሰላም ስለኾነ ልጆቻችን ይመለሱልን!” ዓይነት ጥያቄ ጉባኤውን እንዲጠይቁ እንዲሞክር አደራ ስለው፡፤ እምቢ እንዳይል፦ ጨዋ ስለኽነና የጉዳዩን ከባድነት ስለተረዳ “ እሺ! እሞክራለሁ!” ሲለኝ ቀጥዬ “ አይሮፕላኖችና ሄሊኮፕተሮች መኖራቸውንና ካሉም ቁጥራቸውን እንዲጠይቅልኝ ስጨምርበት አኹንም በተፈጥሯዊ ጨዋነቱ እንደሚሞክር ተስማምተን በምርቃት ተሰነባበትን፡፡ አልኾነለትም፡፡
ከወራት በኋላ አንድ ቀን ዜና ሳይ የሰሜኑ ጦር ታንኮቹን ወደየት እንደሚወስድ አላውቅም፦ ግን ልጆች አላስኬድ ሲሏቸው፦ በኋላም ታንኮቹ እስፖርት ሜዳ ( ስቴዴየም) ውስጥ ተዘግቶባቸው ሳይ ጥርጣሬዬን አረጋገጠልኝ፡፤
ጥብቅ መልዕክትም ላክሁብህ፡፡ መድረሱን በማልጠራጠርበት፦ ውዬ አድሬ ስለአፈጻጸሙም ሃሳብ ጨመርሁ፡፡
አንተ ምንም አላደርግህም ብቻ ሳይኾን ልታደርግ ስትል ለጎረቤት ባለሥልጣን ነግረኸው “መብረቃዊ!” ጭፍጨፋ አካሄድባቸው፡፡ “ አልነገርሁም!” ባትል ይሻልሃል!” በኪሱ በሚይዘው የቀዳውን ለዓለም እንዳያሳማው፡፡ የአገር “ መሰጠቱም” አለ አይደእዚህ ኹለት ነጥቦችን አንስቼ ዋናውን አቆየዋለሁ፤፡
መርዶውን ላስቀድም፦” የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት፦ በሰላም አስከባሪነት፡ የዋለባቸውን “ሳይዋረድ” እያልህ ስትዘረዝር፦ በዕውነት ነው የምላችሁ “ ኧረ ወይድ!” ብዬ ጭህሁ! የኢትዮጵያ የመከላከያ በሰላም አስከባሪነቱ ነው የሚለካው? እንዲህ ስንጨረጨር ፊታ.ሃብተጊዮርጊስ ትዝ አሉኝ፡፡ የቆሎ ጓደኛዬ ይመስል፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ እኚህ ድንቅ እምዬ ምኒልክ ያሳደጓቸው ጋላና ጉራጌ፦ ፍጹም ኢትዮጵያዊ አባታችንን አንድ አዲስ መጥ የኢጣሊያን ባሁኑ አጠራር ዲፕሎማት ለአውሮፓውያን መሰሎቹ ኹሉ “ እናንተ እንዲህ የምታደንቁትን… ብኹለት ጥያቄዎች ጉድ አደርገዋለሁ! ብሎ ፎክሮ በቀጠሮ ሄደ፡፡ ቸኩሎም “ እባክዎ አንድ ኹለት ጥያቄዎች እንድጠይቅዎ ይፍቀዱልኝ፦ ሲል፦ ምናለ ካወቅሁ የምትፈልገውን እነግርሃልሁ ሲሉት ፈንድቆ፦
_ በአገርዎ ውስጥ አንድ የባቡር መስመር ብቻ ነው
ያለው፦ ክጅቡቲ አዲስ አበባ፡፡ ስንት ኪሎሜትር
ነው? ይላል፦ እየፈነደቀ፦
አባመቻልም፦ “ደግ! ምናለ ታዲያ ፦ አስቀድመህ ግን ወደእኔ ስትመጣ አንተ ከቤትህ እኔ ድረስ ስንት ኪሎሜትር እንደመጣህ ንገረኝ፡፡”ሲሉት ያ ፍንደቃ ጠፋ፡፡
አባ መቻልም፡ “ ኹለተኛውስ ጥያቄህ ምን ነበር?” ሲሉት
የቀድሞው የድንፋታ ኹናቴው መለስ ብሎ፦
“ እንዲያው ስለ ሰገሌ ጦርነት ቢነግሩኝ ብዬ ነው፡፡”
አባ መቻል በፈግግታ፦ “ ሰገሌማ የወንድማማቾች ጨዋታ ነው፡፡ ስለጦርነት እናውጋ ካልህ ስለ አድዋ እንጫወት!” ብለው ቦታውን አስያዙት፡፡
ጠ. ሚኒስትር ሆይ፦ ስለ ኢትዮጵያ መከላከያ ዝና መናገር ከፈልግህማ በአድዋ ላይ ስለ ኮሪያ ለማያውቅ ማስተማር ትችል ነበር፡፡
ስለ ኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ዝና ማውራት ከፈልግህማ በአድዋ ላይ ኮሪያን ጨምር፦ ኃያላን የተባሉት ምዕራባውያን ጋር ሌሎች ስመጥር ተዋጊዎች ግሪኮችና ቱርኮች ተጨምረውብት ከነበሩት ጀግኖች የኢትዮጵያ ልጆች ብቻ አዎን ብቻ ናቸው እንኳን ደኅናውን ቁስለኛውን ወንድማቸውን እንኳን ያላስማረኩ፡፡ እንዲህ ዓይነቱን አኩሪ ሠራዊት ነው፦ በሰላም አስከባሪነት የዳኘኸው፡፡ በአገርህ ክብር የምትኮራ ከኾነ የኢትዮጵያን የመከላከያ ሠራዊት ደግምህ! ደጋግመህ!! “ ይቅርታ ትለምናለህ!” ዝርዝሩን ከወደድህ ከጀግኖቻችን ከአንዱ ከወንድሜ ከኮሎኔል መለሰ ተሰማ ታገኘዋለህ፡፤
ለአገር ድኅነት ተማጽኖኤን በመቀጠል፦ በግድቡ ምክንያት “ ጦር” ከመስበቅ ስላላረፈችው አገር ብትሞክር አንዳንድ ሃሳቦች ከማቅረቤ በላይ፦ ዘልቃ ከገባች መቼም ካላበደች ከተማዎቻችንን በአይሮፕላን አትደበድብም፡፡ የ… “ ሜዳ!” ያላችኋቸውን በብድር የተገንቡትን… ትችላላች፡፡ ጉዳቱን ለመቀነስ የእሳት አደጋ መከላከያውን አስቀድሞ ማዘጋጀት ብልህነት ነው፡፡ ባሕር ኃይል የሚፈራው በዋናነት እሳትን ነው፡፡ይህንንም ለመከላከል ጥሩ ሥልጠና ያኪይሂዳል፤፡ እንግሊዝ ባሕር ኃይል ድረስም ልኮ ያሠለጠናቸው ነበሩ፡፡ አኹንም ይኖራሉ ብዬ አስባለሁ፡፡ እሳት አደጋ መከላከያ ውስጥ ከሚኖሩት አሰልጣኞች ጋር ኾነው ለተጠቀሱት ድርጅቶች ኹሉ ሰዎቹን ብቻ ሳይኾን የሚሉትን ኹሉ ማሟላት ከኪሳራ ያድናል፡፡ ወጪውም በኩባንያዎች ሊሸፈን ይችላል፡፡ ይህ አንደኛው ብቻ ነው፡፡
ኹለተኛው፦ በጠባቂነት የቀድሞ ሠራዊት ( ፖሊስንም)በዘበኝነት መቅጠር፦( የዘበኞች አለቃ) ይህ ደግሞ ከሠርጎ ገቦችና በቀላሉ ከሚገዙት አደጋ መከላከያ ይኾናል ስል አሳስቤ ነበር፡፡ በ “ ነበር” ልለፈው፡፡
ይህን ክፍል ከመዝጋቴ በፊት ስለባሕር ኃይል ያልኋቸውን ሳልጠቅስ ባልፍ ልክ አይኾንም፡፡ በ65 መጨረሻ/በ66 መጀመሪያ ላይ፦ በመካከለኛው ምሥራቅ የአሚሪካን የመከላክያ ኃይል አዛዥ የነበሩት አድሚራል ነበሩ፡፡ ለጉብኝት አገራችን መጥተው፦ ሌላውን ትቼ፡ ለግርማዊነታቸው ስለ ባሕር ኃይል የተናገሩትን ላንሳልህ፡፡
“ ግርማዊ ሆይ፦ የርስዎ የባሕር ኃይል መኮንኖች መጀመሪያ ግርማዊነትዎ ካቋቋሙት በጣም ጥሩ አካዳሚ የተመረቁ፦ከዚያ ኖርዌይ ባሕር ኃይል ውስጥ የተለማመዱ፦ ከዚያ እንግሊዝ ባሕር ኃይል ውስጥ ለተጨማሪ ትምሕርትና ልምምድ የነበሩ በመጨረሻም እኛ ዘንድ ከፍተኞች ተቅዋማቶች ውስጥ የዳበሩ ግሩም መኮንኖች ናቸው፡፡ ይህንን እኮ እኛም ኾንን የእንግሊዝ የባሕር ኃይል መኮንኖች አላገኘንም፡፡” ሲሉ የመሠከሩላቸውን መኮንኖች በእድሜም እየገፉ ስለኾነ ተሽቀዳድሞ አዲሱን ተቅዋም እንዲመሠርቱ፤ ተጠቀምባቸው ስል አሳስቤ ነብር፡፡ ማን ሰምቶ አዛዥ ያደረግኸውን መኮንን በሰሜኑ ጦር ምክንያት ገለጻዎቹን ሳይና ስሰማ፦ ጎበዝ ቆፍጣና መኮንንነቱ በግልጽ ይታይ ነበር፡፡ ይህንን ጎበዝ በብሔር ትንትን ለሌለ ኃይል አዛዥ ማድረግ … ቃሉን እንዴት ላውጣው? አንተው ድረስበት፡፡ የኃይሉ አስፈላጊነት የማያጠራጥር እንደመኾኑ ያህል አገራችን ባሏት ልጆችዋ እንዳትገነባ ማድረግ… ይኾናልና፡፡ ይታሰብበት፡፡ በውጪ አሠልጣኞች ማሰልጠን የሚስከትለው ጉዳት የገንዘብ ብቻ አይደለም!!
ወደ ምራቡ ያገራችን ክፍል ስሄድ የመከላከሉን ሃሳብ ልለፈውና ፦ መተከል ላይ ለጥቃቱ በብዛት የሚሰጠው ሰበብ ሳሩ ነው፤፡ ተራ ሳር አለምኾኑና ወፍረቱንና ቁመቱን ነግረውን አጥቂዎች በሳሩ ደባቂነት እየገቡ ነው ስለተባለ በአንተ፦ በጠ.ሚኒስትሩም ጭምር፦
ወገኖቻችንን ለመቅበሪያ ያገለግሉትን “ግሬደሮች!” ከሰው ሠፈር እስከተወሰነ ርቀት ድረስ ለሳሩ ማስተኚያ እንዲያደረጉ፦ እርግጠኛ ለመኾንም በተወሰኑ ርቀቶች ማማዎች ተሠርተው ጥበቃው እንዲጠናከር ሳሳስብ፦
“ቤንሻንጉል የእኔ ነው!” የምትለዋ ጎረቤትና ሸማቂዎቹም በድምበር ስለሚገቡ በዚያም በኩል፦ እንዲያውም ጠለቅ ባለ ርቀት ሳሩን ማስተኛት እንደሚጠቅም፦ ለቃፊር የሚኾኑም ማማዎች ማቆሙም እንደሚጠቅም ባሳሰብሁ በአሥረኛው ቀን፦
“ ቺፍ ኦፍ ስታፉ!” በመከተል ዙሪያ ንጹሃንን እየገደለ ያለውን ታጣቂ ኃይል ማሸነፍ እንዳልተቻለ ተናገሩ፦( የገዥው ፓርቲ ልሳን ኢዜማ) መከላከያ የሠለጠነው፦ ለመደበኛ ውጊያ ነው፡፡ቦታው አስቸጋሪ! መጥፎ! በሰው ቁመት ልክ ሳር በመኖሩ አስቸጋሪ ሆኖብናል፡፡ …” የሚታመን ነው?!?!
እኔ የሰሜኑ ፍልሚያ ታንክ የሚፈልግበት ደረጃ ላይ አለመኾኑን ባውቅም “ ታንክ ይምጣ !” አላልኩም ባለሥልጣኑ እንደሚለው የውጪ ጠላት እጅ ካለበት ታንክ ሳር ይፈራል ሲሉ አልሰማሁም፦ ታንኮቹንና ግሬደሮችን አምጥቶ እክሉን ማጥፋት ያልተፈለገብት ምክንያቱ ሌላ ይመስለኛል፡፡ እመልስበታለሁ፡፡”
‘ወታደር አገር እንጂ ብሔር የለውም፡!’ ተብሎ መሐላ ተፈጽሞ እመከተል ላይ ያለውን የብሔር ዕቅድ ሲባል ወታደራዊ ሞያውን ማስደፈር ውሎ አድሮ ሃፍረትን ማስከተሉ አይቀርም፡፡ የባሰው ግን ድምበሩን አስመልክቶ “ አንዳንዴ እኛ እንገፋለን …” ፈጽሞ መግለጫ ቃሉን ትቼ “ ትክክል “ አይደለም ብዬ ለጠላት ምስክርነቱን የሚያፈርስ ማስተባበያ ሊሰጥ ሲገባ እስካሁን አልሰማሁም፡፡ “ከመቅረት መዘግየት” ነውና ይታሰብበት፡፡
በሰሜኑ ጦራችን ላይ በደርሰው የክህደት ጭፍጨፋ በደለኛውን ከማጋለጥ ልለፍና፦
__ ድል አግኝተናል ተብሎ ሲነገር “ ምዕራባዊ
የትግራይ ክልል” ሲባል _ በደም የተያዘውን ብዙ ግፍና ዕልቂት የተፈጸመበትን አኹን ደግሞ በደምና በሕይወት ክፍያ የተመለሰውን ጥንታዊውን የአማራ አስተዳደርና ሕዝብ “ ምዕራብ ትግራይ!” ማለት ትልቅ ወንጀል ነው፡፡ “የአይጥ ምስክሯ ድምቢጥ!“ እንዲሉ ይህን ወንጀል ሕጋዊ ሽፋን ለመስጠት የመከላከያ ሚኒስትር ተብዬው “ እኛ ድምበር ለማካለል አይደለም፦ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ለዚህ ያቋቋምነው የድምበር ኮሚሽን አለ!” ፦ አንድ አባባል ትዝ አለኝ፡፡ “ ጮሃ የማታውቅ ወፍ ስትጮህ እለቁ! እለቁ! “ ትላለች ይባላል፡፡ ሕገመንግሥት ተብዬው ፈርሶ አይደለም እንዴ ጦርነቱ የተጀመረው፡፡ ስለ ሕገመንግሥት ማፍረስማ ጠ. ሚኒስትሩ ሊቅ አይደለም እንዴ? የማያውቅ አለ?
የአማራን መሬት ለመመለስ የቀድሞ ገጸ ምድሮችን (ካርታዎችን) የሰው ምስክሮችን ይዞ መፈጸም ይቻል ነበር፡፡ ሰላም ፈላጊ፦ ኢትዮጵያዊነት ያለው ካለ!!
በሕገመንግሥቱማ መሠረት፦
_ አዲስ አበባ በራስዋ በመረጠችው ትተዳደር ነበር፦
_ ሲዳማ ክልልነቷን ልጆችዋ ሳይጨፈጨፉ ታገኝ
ነበር፦
_ ደቡብ ውስጥ የተከማቹት “የክልልነት መብታችን
ይከበርልን!” ሲሉ በተደጋጋሚ “… መኪና
ፈልጋችሁ ነው !” እያሉ በባሰ ውርደት ደቡብ ውስጥ “ ሽማግሌ!” የሌለ ይመስል የኦሮሞ “ ሽማግሌ” ተላከባቸው፡፡ ኦነግ ካርታ ውስጥም ተጠቃለለ፡፡
_ ሕገመንግሥቱ የአገሪቱ የሥራ ቋንቋ አማርኛ ነው እያለ በዘፈቀደ ሦስት ሌሎች ጨመረ፦ ወዘተ. ስለዚህ አማራን ለመጉዳት ሲባል ሕገመንግስት መጥቀሱ የውጭ ተገዥነትን ለማያውቅ ከማረጋገጥ ሌላ የሚስከትለው መገዳደልን ነው፡፡
የውጪዎቹ “ የአማራና የኤርትራ ጦር ከትግራይ ይውጣ!” እንዲሉ ማመቻቸት አልኾነም?
ይባስ ደግሞ፦ ቁጥሩን ለመናገር የሚቀፍፍ ግድያና… ፈጽመው ወደ ሱዳን የኮበለሉትን “ ወደ አገራችሁ ተመለሱ!” የተባለው ደሙ ያልደረቀ፦ ትኩስ ሬሳ ያለውን አማራ ምን ለማድረግ ነው? ግፉ አልበዛም!!!
የዚህን መዘዝ ከውጪ መሣሪያነትና ወቀሳ፦ ዛቻ ለመዳን በሰሜኑ ጦር ላይ የተፈጸመውን ዝርዝር ሳይደብቁ ማውጣት ግድ ይላል፦
_ እንደተኙ የተጨፈጨፉት ቁጥር ስንት ነው?
ዕውነቱን 32 ሺህ 36 ሺህም ሲባል ስምቻለሁ
(የራስን ስህተትም ኾነ ወንጀል ለመደበቅ ሲባል
መደበቁ፦
_ የአፍጻጸሙ ዓይነትና ዝርዝር ቢቻል በምስል
አስደግፎ፦
_ ስለሬሳቸው
_ ስለ ሴቶች ወታደሮች አኹንም በምስል አስደግፎ ማውጣቱ በውጪ ያሉትን ኤምባሲዎች መሣሪያውን ነስታችሁ አትውቀሱ/አታስወቅሱ
_ የውጪ መንግሥታትም እነዚህን ኢሰባዊ ወንጀሎች ሲያዩ አድብ መግዛታቸው አይቀርም፡፡
ጠ. ሚኒስትር ሆይ፦ በአጭሩ ዘመንህ አገር ወገናችን ላይ የደረሰውን ኹሉ ከምዘርዘር ተቆጥቤ የነገውን እንመልከት፦ በርዕሱ ላይ እንደገለጽሁት ቁርጡን ንገረን፦
አገራቻን ተወርራ መንፈቅ ሊኾን አይደለም? እየከተሙ ከምኾን አልፈው መንገድም እየሠሩ መኾናቸው ይነገራል፡፡ አኹንማ ልጆቻችንንም መድፈር ጀምረዋል ይባላል፡፡ “የልጆቻችን አግር ነው!፡፤ “ እንዲባል ነው? ወራሪዎች ተጨማሪ ጦር ሲያሠለጥኑ አንተ “ ሰላም አስከባሪዎችን እንኳን መልሰሃል? ሌላው መከላከያ/ፌደራል አልገባም አማራው ክልሉን እንዲጠብቅ እንኳን ልዩ ኃይሉን እንዲያጠነክር አይደረገም!? አይ ሞት! የሚል ወዳጅ ነበረኝ፡፡ “በኦሮሞ ዘመን ምን ያልኾንነው አለ!? የሚል ዘፈን/እሮሮ/እንጉርጉሮ አይሰማህም!? ወይስ “ በዐቢይ ዘመን!” ነው??
_ በአንደኛውና በኹለተኛው የዓለም ጦርነቶች ላይ በቅኝ ገዢዎቻቸው አገልጋይነት አዎን አገልጋይነት!መሣሪያማ ለመያዝ ጥቁር አሜሪካኖች እንኳን በኹለተኛው ነው የተፈቀደላቸው፡፡ የፕሬ. ኦባማ ኬንያዊ አያት በውጥቤትነት ኹለተኛውን እንደተካፈሉ መናገራቸውን ያልሰማ ካለ፦ማረጋገጫ!!!
ኢትዮጵያዊ ግን… ለማንኛውም ዝርዝሮቹን አባሪ አድርጌልሃለሁ፦
ስለ ሰንደቅ አላማ፦
መጀመሪያ እንደሰማሁት ማዋረድ የጀመረው ሰንደቅ አላማችንን ነው፡፡ ምክንያቱቹ ግልጽ ናቸው፦ ፈጣሪዎቹ ፦
_ ጥንታዊዋንና ታሪካዊዋን ሰንደቅ አላማችንን ሊያጠፉ የፈለጉባቸውን ምክንያቶች አስበህ/ ዐውቀህ ተስማምተህ ነው?
በመጀመሪያ ሌላውን ትተን በአፍሪካ ቀደም ሲል የነጻነት ተስፋ በኋላም የነጻነት ምልክት ኾኗል፡፡ ከ አፍሪካ መጀምሪያ ነጻ የኾነችው ጋና የእኛን ቀለማት ዘቅዝቃ ኮክብ መሃልዋ ላይ ስታደርግ ሊሎች ከ30 በላይ የሚኾኑ አፍሪካ አገሮች የእኛን ቀለማት በተለያዩ ኅብር አስገብተዋል፡፡ እንደ ቀኃሥ፦ ንክሩማና ሌሎች አላማ አፍሪካን አንድ ለማድረግ ነበር፡፡ ሂደቱም ያዝግም እንጂ ደግ ነበር፡፡ ለዚህም ሰንደቅ ዓላማ ከፍተኛ ሚና አለው፡፡ ለዚህ ሲሉ ነው የማያንቀላፉ የኢትይጵያችን ጠላቶች እንኳን በአፍሪካ በኢትዮጵያም ውስጥ ተቃዋሚዎቹን ያበዙባት፡፡
አንዳንዶች ሰበብ ሲፈልጉ ከቀለማቱ ትርጉም ውስጥ
“ብጫ!” ሃይማኖት ነውና አይወክለንም ሊሉ ይፈልጋሉ፡፡ ሰበብ ፈልገው በጠላት መሣሪያነት ካልጸኑ በስተቀር፦ “ኦርቶዶቅስ/ተዋህዶ!” አይልም፡፡ እያንዳንዱ በየሃይማኖቱ ለፈጣሪው ታማኝ እንደሚኾን ለአገሩም ይኹን ማለት ነው፡፡ አገራችን ውስጥ፡ የአይሁድ ፦ የኦርቶዶቅስ፦የሙስሊም፦ የካቶሊክ፦የፕሮተስታንት ሃይማኖት ተከታዮች ኹሉ ለሰንደቅ አላማቸው ታማኝነት ጥርጣሬ አልነበረም፡፡ በአሜሪካኖች ከተፈጠሩት በአጠቃላይ “ጴንጤ” ከሚባሉት ውስጥ አንዳንዶቹ ሌላ ትርጉም ሊሰጡት ይፈልጋሉ፤፡ የሰንደቅ አላማችን ቀለማት መነሻ ፦ ጌታ ዳግመኛ ምድርን በውሃ እንደማይቀጣት ቃል የሰጠበት ምልክት ነው፡፡ ቀለሙም ኾነ ትርጉሙ እምነት ላለው ሌላ ምክኛት ከሌለው፦ቅሬታ ሊኖረው አይገባም፡፡
እንግዲህ፦ ጠ. ሚኒስትር ሆይ ከመነሻው የቀረበልህን ጥያቄ የምትመልስበት መንገድ እነሆ!
“ኢትዮጵያዊ በእናት አገሩና በባንዲራው ቀልድ አያውቅም!” ብለህ ደጋግመህ ተናግረህ ከኾነና “ እኛ ሳንፈርስ ኢትዮጵያ አትፈርስምስ!” ያልከው በእንግሊዝኛ “ የገንፎው መጣፈጥ የሚታወቀው በመበላቱ ነው፡፡” እንደሚባለው የአንተንም ኢትዮጵያዊነትህንና ለኢትዮጵያ እንደምትሞትላት ለማሳየት
ሚያዝያ 27 ቀን ( የዕለቱን ትርጉሞችንም አስታውሰህ)
_ እምዬ ምኒልክ ሃውልት ፊት ሰደቅ አላማህን ለብሰህ፦ የላክሁልህን በማያገባቸው ጦርነት በገዢዎቻቸው አገልጋይነት ሲሰዉ ኢትዮጵያውያንን ግን ከዚህ አድነው፦ማእድኖቻቸውን… ኹሉ ሳያስነኩባቸው በክብር ጠብቀው ለትውልድ
ስላስተላለፉት ታላቁ ንነ መምሕር ታዬ ቦጋለ፦ የውጪ መሪዎችና ምሑሮች ስለርሳቸው ለትውልድ ያስቀሩትን ፕሮ. ፍቅሬ ቶሎሳ ነጠብጣብ ሰጥተውህ በአማረ አንደበትህ ብታዥጎደጉደው፡8 የልብን ዐዋቂ እግዚአብሔር ቢኾንም እንቀበልሃለን፡፡ ከዚያ በፊት ግን ሰንደቅ ዓላማችንን እቦታው ብትመልስ እናከብርሃለን፡፡ ካልደፈርህ “ ማንም ሰውም ኾነ ድርጅት ጥንታዊውዉን ሰንደቅ አላማ ለፈለገው ነገር የማዋል መብቱን የሚያስከብር አዋጅ እንጠብቃለን፡፡
ይህንን በዕለቱ ሳታደርግ ብትቀር
_
ኢ