መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ምን አሉ ?

0
0 0
Read Time:58 Second

ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ፦

” … በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ከስር መሰረቱ ለመፍታት የእስረኞችን ክስ ማቋረጥ አስፈልጓል።

የክሱ መቋረጥ ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት እና ዋስትና ያለው የዴሞክራሲ ስርዓት  በመገንባት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስቀጠል ከማሰብ የመነጨ መሰረታዊ ጉዳይ ነው።

በእነ አቶ ጃዋር መሃመድና አቶ እስክንድር ነጋ ስር የነበሩ ተከሳሾች ክስ መቋረጥ በስራቸው በርካታ ተከታይ ያላቸው መሆናቸውን ከግንዛቤ በማስገባት ለብሔራዊ አካታች ምክክሩ ጉልህ ሚና እንዳላቸው በመገንዘብ ነው።

በሽብር ቡዱኑ መሪ ደብረፂዮን ገብረ ሚካኤል ስር ያሉ የክስ ሂደት መቋረጥ ከጤና እና እድሜ መግፋት ጋር የተያያዘ ነው።

ኢትዮጵያዊያን ክሳቸው የተቋረጡ ዜጎችን በሚመለከት ህዝብና መንግስትን በማጋጨት እራሳቸውን ደብቀው የሚያራግቡ አካላትን በቃቹህ በማለት ለዘላቂ ብሔራዊ ጥቅም ዘብ መሆን ይገባል “

#ኢዜአ

ዶ/ር ለገሰ ፥ መንግስት ለያዘው ሀገራዊ ምክክርና ብሄራዊ መግባባት ለመፍጠር ሁሉን አካታች የሆነ ውይይት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል ብለዋል።

ይህን ሀገራዊ አንድነት ለማምጣትም ብዙ ተከታይ ያላቸውን እስረኞች ክስ ማቋረጥ ማስፈለጉን ነው የተናገሩት።

በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ፣ የተመቻቸ ፖለቲካዊ ሁኔታን ለመዘርጋት ፣ዋስትና ያለው ዲሞክራሲ ለመገንባት ያለመ ነው ውሳኔው ብለዋል።

ውሳኔው በየደረጃው የሚመለከተው አካል ተወያይቶበት የወሰነው ሲሆን ዘላቂውን የሀገር ጥቅም ከግምት ያስገባም መሆኑን ነው ሚንስትሩ ያነሱት።

ዶ/ር ለገሰ ፥ መንግስት የእነዚህን ግለሰቦች ክስ እንዲቋረጥ ሲያደርግ ግለሰቦቹ ለሀገራዊ መግባባት ያላቸውን ሚና አምኖበት ስለሆነ ለሰላማዊ ምክክር የተሰጣቸውን እድል እንዲጠቀሙበትም ጥሪ ቀርቦላቸዋል ብለዋል።

#ኤኤምኤን

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *