ስማቸው ያልተገለፀ የአሜሪካው ከፍተኛ ባለሥልጣን ለጋዜጠኞች ምን አሉ ?

0
0 0
Read Time:35 Second

• የኢትዮጵያ መንግስት ከአሜሪካ የንግድ ልዑክ የተነሱትን ቅሬታዎች በተመለከተ ተጨማሪ ” አዎንታዊ እና ገንቢ ” ዕርምጃዎች የሚወስድ ከሆነ ኢትዮጵያ ከተጠቃሚነት የተሰረዘችበትን የ #AGOA ዕድል በተመለከተ የንግግር ሒደት ውስጥ ለመግባት ፈቃደኛ መሆኑን ገልፀዋል።

•  ታኅሳስ 28 ቀን 2014 ከጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር ንግግር ማድረጋቸው የተገለጸው የቀድሞ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ ያደረጉት ” በኢትዮጵያ መንግሥት ጥያቄ ”  መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

• አዲሱ ተሿሚ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ መቼ ወደ ቀጣናው ለመጓዝ እንዳሰቡ አልታወቀም ፤ ነገር ግን ረዥም [ጊዜ] እንደማይሆን ተገልጿል።

• ጥር 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በስልክ ንግግር ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ሁለቱ መሪዎች ንግግር ያደረጉት በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጥያቄ መሠረት መሆኑን ተናግረዋል።

Credit : Reporter Newspaper

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *