መንግሥት መቀመጫቸውን አዲስአበባ ላደረጉ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ እየሠጠ ነው

0
0 0
Read Time:47 Second


ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጎረቤት ሀገራት እና የኢጋድ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል አምባሳደር ፍሰሃ ሻውል በሰጡት ማብራሪያ መንግሥት በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን በርካታ እርምጃ መጓዙን ገልፀዋል።

ሆኖም አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት አሁንም ለአሸባሪው ህወሓት በመወገን የኢትዮጵያን ስም እያጠፉነው ብለዋል።

አሸባሪ ቡድኑ ከዚህ ቀደም በአማራና አፋር ክልሎች ካደረሰው ውድመት ባሻገር አሁንም በአብአላ በኩል በከፈተው ወረራ በርካቶችን ለሞትና መፈናቀል ዳርጓል።

ወደ ትግራይ ክልል የሚደረጉ የሰብዓዊ እርዳታዎችም እንዳይደርሱ እንቅፋት መፍጠሩን ነው ያነሱት።

መንግሥት ለሰላም ካለው ፅኑ አቋም የተነሳ ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠር ሀገራዊ ምክክር ለማድረግ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሀገራዊ ምክክሩ የሚካሄድ ቢሆንም የአሸባሪው ህወሓት ኃይሎች ላጠፉት ጥፋት ተጠያቂ ይሆናሉ ብለዋል።

ኢትዮጵያ በውስጧ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት እንዲፀና ከጎረቤቶቿ ጋር ያላትን መልካም ወዳጅነት በማጠናከር ሚናዋን ትወጣለችም ነው ያሉት አምባሳደሩ።

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የውጭ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀኔራል ቡልቲ ታደሰ አሸባሪው ህወሓት የተሳሳተ መንገድ በመከተል ኢትዮጵያን ለማፍረስ ቢሞክርም በጀግኖች የኢትዮጵያ ኃይሎች መክሸፉን አንስተዋል።

የሽብር ቡድኑ በመከላከያ ሰሜን ዕዝ፣ በአፋርና በአማራ ህዝብ ላይ በይፋ ከፈፀመው አስከፊ ጥቃት ባሻገር አሁንም ትንኮሳውን አላቆመም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *