ዘላለም ሙላቱ በሕግ እንዲጠየቁ ባልደራስ ለምርጫ ቦርድ ደብዳቤ አስገባ

0
0 0
Read Time:35 Second

ገዥውን ፓርቲ በመወከል የአዲስ አበባ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባልና የትምህርት ቢሮ ሓላፊ የሆኑት ዘላለም ሙላቱ፣ የከተማዋ ምክር ቤት የካቲት 3 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ላይ ባሰሙት ንግግር፣” በፊንፊኔ ዙሪያ የሚገኘው የኦሮሚያ ልዩ ዞን ፣አዲስ አበባ ከርሷን ሞልታ ፈርሷን የምትጥልባቸው ናቸው” በማለት በአደባባይ ሕዝብን ዘልፈዋል። ይህን ተከትሎ፣ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ዘላፊው ከሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባልነታቸው የሚነሱበትንና የማሟያ ምርጫ የሚደረግበትን እንቅስቃሴ ጀምሯል።

በዚህም መሠረት፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሂደቱን የማስጀመሪያ ሕጋዊ ድጋፍ እንዲሰጠው ባልደራስ ጠይቋል። የጥያቄውን ሙሉ መልዕክት የያዘ ደብዳቤም ዛሬ ሰኞ የካቲት 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በፕሬዚደንቱ እስክንድር ነጋ እና በአደረጃጀት ጉዳዮች ሓላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል በኩል የቦርዱ ዋና ጽ/ቤት በአካል ተኝተው አቅርበዋል። ደብዳቤውን እታች በሰፈረው ምስል ላይ ይመልከቱ፦

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *