” በከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት ላይ ግድያ የፈጸሙና ያስፈጸሙ የፀጥታና የአስተዳደር አባላት ላይ ተገቢው የወንጀል ምርመራ ተደርጎ ለፍትሕ ሊቀርቡ ይገባል ” – ኢሰመኮ

0
0 0
Read Time:1 Minute, 57 Second

በከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት ላይ ግድያ የፈጸሙና ያስፈጸሙ የፀጥታና የአስተዳደር አባላት ላይ ተገቢው የወንጀል ምርመራ ተደርጎ ለፍትሕ ሊቀርቡ ይገባል ” – ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት ላይ ግድያ የፈጸሙና ያስፈጸሙ የፀጥታና የአስተዳደር አባላት ላይ ተገቢው የወንጀል ምርመራ ተደርጎ ለፍትሕ ሊቀርቡ ይገባል ብሏል።

ኮሚሽኑ ይህን ያለው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ነው።

ኢሰመኮ በምርመራ አሰባሰብኩኝ ባለው እና አገናዘብኩኝ ባላቸው ማስረጃዎች 14 የከረዩ የሚችሌ ገዳ አባላት በኅዳር 22 ቀን 2014 ዓ.ም.  በመንግስት የፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በግዳጅ ወደ ጫካ ቦታ ተወስደውና የፀጥታና የአካባቢ አስተዳደር ሰዎች ባሉበት፣ ጭካኔ በተሞላው ሁኔታ በጥይት ተመተው የተገደሉ መሆኑንና ይህም ከሕግ ውጭ የተፈጸመ ግድያ (extra judicial killing) ስለመሆኑ በምክንያታዊ ሁኔታ አሳማኝ (reasonable ground to believe) ሆኖ ማግኘቱን ገልጿል።

በተጨማሪም፣ በግዳጅ ከተወሰዱት 23 የጅላ አባላት መካከል አንድ ሰው ሞጆ ከተማ በሚገኝ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ካምፕ ውስጥ በቁጥጥር ስር እያለ ሕይወቱ አልፎ  ያለምንም ምርመራ አስክሬኑን ቤተሰቦቹ እንዲወስዱና እንዲቀበር መደረጉ ከዚሁ ጉዳይ ጋር የተያያዘ ተጨማሪ ከሕግ ውጭ የተፈጸመ ግድያ (extra judicial killing) መኖሩን በምክንያታዊ ሁኔታ አሳማኝ (reasonable ground to believe) ሆኖ ማግኘቱን ኢሰመኮ ከአሳውቋል።

ኢሰመኮ የላከልን ሙሉ መግለጫ ከላይ ተይያዟል።

ከኢሰመኮ ሪፖርት

ህዳር 21 ቀን 2014 ዓ.ም ለስራ ወደፈንታሌ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች ሄደው ከቀኑ 8፡00 ሰዓት አከባቢ ወደመተሃራ በመመለስ ላይ የነበሩ የፀጥታ አባላት ላይ በወረዳው ሀሮ ቀርሳ ቀበሌ ልዩ ስሙ ኢፍቱ በተባለ ቦታ ላይ ማንነታቸው ባልታወቀ የታጠቁ ኃይሎች በተፈጸመ ጥቃት የ11 ፖሊስ አባላት ሕይወት ማለፉና ቢያንስ 17 ሌሎች የፖሊስ አባላት መቁሳለቸው ታውቋል።

ይህንን ተከትሎ ህዳር 22 ቀን 2014 በግምት ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጥቃቱን ያደረሱ ተጠርጣሪዎችን ለመፈለግ በፈንታሌ ወረዳ ጡጢቲ ቀበሌ ልዩ ስሙ ዴዲቲ ካራ ከሚባል የከረዩ ሚችሌ አባገዳዎችና የጅላ አባላት የመኖሪያ ሰፈር የደረሱ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች 39 የጅላ አባላትን በቁጥጥር ስር አውለዋል።

በእነዚህ ፀጥታ አባላት ቁጥጥር ስር ከዋሉ የከረዩ የሚችሌ ገዳ አባላት መካከል 16 ሰዎች ወደ ጨቢ አኖሌ ጫካ ተወስደው14ቱ ሰዎች በጥይት ተመተው ተገድለዋል።

በዚህም፦

-የከረዩ አባገዳ #ከዲር_ሀዋስ

-ኦዳ ጫርጨር

-ቦሩ ፈንታሌ

-ፈንታሌ ቦሩ

-ቁምቢ ጉራቻ (ቃሉ ናቸው)

-ቦሩ ፈንታሌ

-ቡላ ፈንታሌ

-ሮባ ሀዋስ

-ቦሩ ጎዳና

-ጂሎ ደዲኦ

-ቡላ ፈንታሌ

-ቡልጋ ቦረኡ

-ጂሎ ዲዶ እና ቦሩ ጂሎን ጨምሮ 14 የከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት መሬት ላይ እንዲተኙ ተደርገው በጥይት ተመተው ተገድለዋል።

የሟቾችን አስከሬን ለማንሳት ግድያው ወደ ተፈጸመበት ቦታ የሄዱ ሰዎች በቦታው በነበሩ ፖሊሶች እንዳያነሱ በመከልከላቸው ፤ አስከሬኖቹ ለበርካታ ሰዓታት ሳይነሱ መቆየታቸውንና የፈነዱና በከፊል በዱር እንስሳ የተበሉ እንደነበሩ አስከሬኖቹን ያነሱና የቀበሩ ሰዎች ገልጸዋል።

አስከሬኖቹ ከጀርባ በኩል ወገባቸውና ጭንቅላታቸው ላይ በጥይት ተመተው መገደላቸውን የሚያሳዩ ምልክቶች ነበሩባቸው።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *