የሕወሓት ሀይል ባለባቸውና ክልሉ በሚዋሰንባቸው አካባቢዎች ሰላም ለማስፈን እየተሰራ መሆኑን የአማራ ክልል መንግስት አስታወቀ፡፡

0
0 0
Read Time:32 Second

የሕወሓት ሀይል ባለባቸውና ክልሉ በሚዋሰንባቸው አካባቢዎች ሰላም ለማስፈን እየተሰራ መሆኑን የአማራ ክልል መንግስት አስታወቀ፡፡

በአማራ ክልል አሁንም የሕወሓት ወራሪ ሀይል ባለባቸው አካባቢዎችና ክልሉ በሚዋሰንባቸው አካባቢዎች ሰላም እንዲሰፍን እየተሰራ መሆኑን የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ሃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ተናግረዋል፡፡

ከሰሞኑ ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ በንፋስ መውጫ ተፈጥሯል ያሉትን ክስተት ያስታወሱት ሃላፊው፤ አንዳንድ ሌባ ቡድኖች እያደረጉ ያሉትን መሰል እንቅስቃሴ መልክ ለማስያዝና በቀጣይ እንዳይፈጠር እየተሰራበት ነው ማለታቸውን የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት አስነብቧል፡፡

በክልሉ የሰሜን ወሎ፣ ዋግ፣ ሰሜን ጎንደርና ሌሎች ዞኖች ከውስን አካባቢዎች በስተቀር ነጻ ሆነው መደበኛ ስራቸውን እያከናወኑ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡

የህወሃት ወራሪ ቡድን በወረራ ከያዛቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች እንዲወጣ ቢደረግም አሁንም ድረስ ከክልሉ ያልወጣባቸው አካባቢዎች መኖራቸውን የክልሉ መንግስት ሲገልጽ ቆይቷል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *