የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

0
0 0
Read Time:28 Second

በዛሬው እለት የካቲት 8 ቀን 2014 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በመስቀል አደባባይና በጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት ቦታዎች በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ የጋራ ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

ውይይቱ በፍጹም ቅን ልቡና፣ መደማመጥና መግባባት በተሞላበት ስሜት መካሄዱ ተገልጿል።


በውይይቱ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመስቀል አደባባይና የጃንሜዳ ባሕረ ጥምቀትን በተመለከተ የተነሱትን ጥያቄዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም ቀጣይ ውይይቶችን መሠረት በማድረግ የማያዳግም ምላሽ ለመስጠት የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

ወደፊት ቤተ ክርስቲያንና የከተማ አስተዳደሩ በልማት፣ በሰላምና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተቀራርበው እንደሚሰሩ ይፋ ገልፀዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *