የፃድቃን ንግግር ትርጉም ቃል በቃል ይሄ ነው ።

0
0 0
Read Time:3 Minute, 48 Second

በብርሃኑ ጁላ፣በእኔና ታደሰ ወረደ መካከል በየቀኑና በየጊዜው የሚደረግ ግንኙነት ነበር። ስለዚህ ይህን እናድርግ ብለን ነው የተስማማነው። አሜሪካውያኖች ናቸው ያመቻቹትና ያገናኙን። የደረስንበትን ውሳኔም ነግረናቸዋል። ያውቃሉ። ስለዚህ የተኩስ ማቆሙ የተደረገው በዚህ አግባብ ነው።

(እነ ብርሃኑ ጁላን?) ሻዕቢያንና አማራን ውጡ ስትሏቸው አንወጣም ቢሉ ምንድን ነው የምታደርጉት ብለን ስንጠይቃቸው:-

ውጡ ካልናቸው ይወጣሉ፤ አቅም የላቸውም። እኛ ላይ ተንጠልጥለው ነው ያሉት እንጅ አቅም የላቸውም ያልናቸውን ይፈፅማሉ አሉን። (እዚህ ላይ audience ይስቃል)

ያላችኋቸውን የሚያደርጉ ከሆነ ጥሩ። ያላችኋቸውን የማይፈፅሙ ከሆነስ ምን ታደርጋላችሁ አልናቸው።
አይ ግድየለም አሉን።

እኛ ግን ሻዕቢያን በሚመለከት የሚሰሟችሁ ከሆነ ጥሩ ካልሆነ ግን እናንተ ብቻ ውጡ እንጅ ለእኛ አይቸግረንም ብለናቸዋል።

ስለዚህ እነሱ የሚያደርጉት ነገር ካለ ጥሩ ከሌለ ግን ሻዕቢያ ላይ የፈለግነውን ለማድረግ የሚከለክለን ስምምነት የለም። እነሱም( አሜሪካኖችም) ያውቃሉ።

ይህን officially እነግራችኋለሁ አሜሪካኖች አሁን ላይ የሻዕቢያ መንግስት ለአለማቀፍ ህግጋት የማይገዛ rogue state ነው ብለው ነው የመደቡት። ይህ ማለት የwar lords፣ የኮንትሮባንዲስት፣ ውሉ ለማይታወቅ ጥርቅም ፣ ሰላም ለማይፈልግ ስብስብ የቆመ መንግስት እንደሆነ ነው የምናምነው ብለው በግልፅ ነግረውናል። ሻዕቢያ የቀጠናው spoiler ነው ብለን ነው የምናምነው ብለውናል። ሶማሌ ውስጥ ችግር የሚፈጥር፣ ሱዳን ውስጥ ችግር የሚፈጥር፣ጅቡቲ ውስጥ ችግር የሚፈጥር፣ኢትዮጵያ ውስጥ ችግር የሚፈጥር ሻዕቢያ ነው ብለውናል።

ምዕራባውያን ቀጠናው ላይ ሰፊ የሆነ interest አላቸው። የኢኮኖሚ interest አላቸው። ሱዳን ውስጥ ባለው ጉዳይ ችግር እየፈጠረባቸው ነው ያለው። አወሳስቦባቸዋል። ስለዚህ የዚህ አካባቢ ዋና የሰላም ጠንቅ፣ ቀይ ባህር ላይ ሁከት የሚፈጥር ፣የአፍሪካ ቀንድ ላይ አለመረጋጋት የሚፈጥር ሻዕቢያ ነው የሚል መደምደሚያ እንዳላቸው ነው የነገሩን።
End T A(101), [Apr 22, 2022 at 23:40]
“ወደ ኮምቦልቻና ደሴ እንገባለን የሚል ሀሳብ አልነበረንም፤ መንገዱ አልጋባልጋ ሲሆንልን የመጣልን ሀሳብ ነው። እናስብ የነበረው በመደራደር የትግራይ ህዝብ ጥቅሙን ያስከብራል ብለን ነበር።
ደብረብርሃን እንደደረስን ብዙ ነገሮችን ማየት ይጠበቅብን ነበር። በተለይ የዲፕሎማሲው አለም ላይ ጥንቃቄ ያስፈልግ ነበር። ከዛ ውጭ ከትግራይም በላይ እንደ አገር ትልልቅ ችግሮች ገጠሙ።
የመጀመሪያው የኢኮኖሚ ችግር ነው። አብይ ጦርነቱን ተጣድፎ ሲጀምር የUAE የተወሰነ ቢሊዮን ዶላሮች ስለነበሩት የሚያልቅ አልመሠለውም ነበር። ከዛም እየዞረ እባካችሁ ዶላር ላኩልን እባካችሁ ዩሮ አበድሩን እያለ ነበር።
በመጨረሻም የገባው ደወ የኢትዮጵያና የትግራይ ህዝብ ያፈራቸውን አገራዊ ሀብቶች ወደመሸጥና ገበያ ማቅረብ ነው። የኢትዮጵያ ቴሌና አየር መንገድን ታቋቸዋላችሁ።
ይሄ የሁላችንም ችግር ነው። ትግራይ አገር አይደለችም፣ የኢትዮጵያ አካል ነች።

አቅማችንን አውቀውታል። officially ነው የምነግራችሁ አሜሪካኖቹ ቃል በቃል “የትግራይ ህዝብ የቀጠናው የሰላምና ደህንነት ዋልታና ማገር ነው በሚገባ recognize አድርገናችኋል። በቀይ ባህርና የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ችላ የማይባል ሃይል ነው” ብለውናል። የትግራይ ምድር በቀጣይ ለኢኮኖሚያዊ እድገት አሉታዊ ነገር አለው” ብለውናል።
ይሄ ከሃይል በተጨማሪ በዲፕሎማሲው የመጣ ለውጥ ነው። የምታይዋቸው HR6600 የሰኔቶቹ ማዕቀብ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ UN ሁሉም ለኛ ድጋፍ አላቸው። ይሄ ለአብይ ከፍተኛ ጫና አድርሶበታል።
በከፍተኛ ወታደራዊ ስልጠናቸው ላይ የተወያዩበትና በኛ የወታደራዊ ስለላ ክፍል በተገኘው መረጃ ከፍተኛና ነባር አመራሮቹና ከባድ መሣሪያዎቹ ከ65-75 ከመቶ ከጥቅም ውጭ ሆነዋል።
አሁን ላይ እንደነ አዘርባጃን ካሉ አገራት የተወሰኑ መሳሪያ ቢሰበስብም በተለይ እንደ ድሮን አቅራቢ የነበሩ አገራት ችግራችሁን እዛው በሰላም ፍቱት ብለው አባረውታል።

በፖለቲካው በኩልም እያያችኋቸው ነው። ኦሮሞ በከፍተኛ ረብሻ ውስጥ ነው። የታጠቀውም ያልታጠቀውም ፍልሚያ ላይ ነው። የኦሮሞ ከፍተኛ ፖለቲከኞች ጋር ግንኙነት አለን፣ ኦነግ ሸኔ የሚያደርሰውን ጥፋት እያችሁት ነው፣ እዛው ስልጣን ውስጥ ያሉት ሁሉም በረብሻ ውስጥ ናቸው።
አማራም በከፍተኛ ግርግር ውስጥ ነው። በተለይ ውስጣዊ አንድነታቸው ተፈረካክሶ ልዩነታቸው ሰፍቷል ብዙ ክፍፍሎች አሉባቸው፣ የክፍፍል አጀንዳቸውንም ታቁታላችሁ።

በነዚህ ምክንያቶች ጠላቶቻችን ስለደከሙ ስለሰላም እንነጋገር ብለውን ወታደሮቻችንንም ሰብስበን እነሱም እንደኛ አድርገው ተገናኝተን ተነጋግርናል። በዚህም ሰብአዊ ድጋፎች ያለገደብ እንዲገቡ ተስማምተናል። ከአሜሪካና ከብልጽግና ወታደሮች ጋር።
በየእለቱ እንገናኛለን። ከኛ በኩል እኔና ታደሰ ወረደ ከነሱ እነ ብርሃኑ ጁላ በአሜሪካ አማካኝነት በተደጋጋሚ ተገናኝተናል። አሜሪካኖቹ ናቸው ወስደው ያገናኙን።
ጦርነት በማቆሙ ላይ ተስማምተናል። ጦራችሁን ዋጃና ጡሙጋ አንዲአርቃይ ላይ አቁሙ አሉን እሺ አልን። እኛም የአማራ ሃይሎች ከተነኮሱን ግን እንመታቸዋለን የኤርትራ ሃይላትም ከተነኮሱን እንወጋቸዋለን አልናቸው “እሺ” አሉን። ውጊያው በአፋርም እየመጣ ነው፣ እሱንም አንታገስም። እኛ በአፋር በኩል ካለን ታሪካዊ የህዝብ ዝምድና አንጻር መዋጋት አንፈልግም ነበር።

እኛ አማራንና ሻቢያን አስወጡልን(ከምዕራብ ትግራይ) ስንል እሺ ብለውናል። ቆይ አማራና ሻቢያ አንወጣም ቢሏችሁስ? አልናቸው። አይ ይወጣሉ፣ እኛን ተንጠልጥለው እንጂ እንደዚህ የሆኑት የምንላቸውን ይተገብራሉ’ አሉን። እኛም “እሺ እንደዚ ከሆነ ጥሩ፣ ካልሆነ ግን ሻቢያን በሚመለከት የፈለግነውን እርምጃ ለመውሰድ የሚከለክለን ህግ የለም ብለናቸዋል።
አሜሪካኖች ሻቢያን የአከባቢው የቀይ ባህርና የአፍሪካ ቀንድ የሁከት ምንጭ rogue state ብለው ነው የሚያምኑት። ሱዳን ፣ ጅቡቲ ሶማሊያ፣ ኢትዮጵያ …ሁሉ እየዞረ ችግር የሚፈጥር ሃይል ነው ብለዋል። አሁን ላይ የአፍሪካ ቀንድ የሰላም ሃይል እኛ እንደሆንን ነግረውናል፣ እንደሚያግዙንም ቃል ገብተውልናል።
እንዲደራደሩ ያደረግናቸው አስገድደን ነው በትግራይ ህዝብ ትግል ነው። አሁንም ውልፍት ካሉ ክንዳችንን ማሳየት ነው። ደብረሲና ስንደርስ የተከተሉን ወጣቶች ዛሬ ላይ ሰልጥነው ወታደሮች ህነዋል። የሃይል መሪዎች የጋንታ መሪዎችን አመራሮችን አሰልጥነናል አሁንም እያሰለጠንን ነው። ጠላቶቻችን ከኛ ጋር ሊደራደሩ የሚችሉት እምቢ ቢሉ በክንዳችን እንደምንጠመዝዛቸው ሲያውቁ ብቻ መሆኑን ልናውቅ ይገባል። (ለዚህ ነው በከፍተኛ ሁኔታ እያሠለጠንን ያለነው)። የሚሆነው ሁሉ በኛ በራሳችን ሃይልና ውስጣዊ አንድነት እንጂ ከውጭ አይደለም። የአለም ማህበረሰብም እያዘነልን ነው ልክ እንደ አገርም እያየን ነው። አአ የመጣ ዲፕሎማት መቀሌም መምጣት ጀመረዋል። የት እንደሚደርስ አናቅም ግን ፊታችን(ነጋችን) የሚወሰነው ባለን ሃይል ነው።
አንድ መታወቅ ያለበት ነገር የሰራዊታችን ጥንካሬ የሚወሰነው በውስጣችን ባለው ፖለቲካዊ ጥንካሬ ነው። እናንተ ስትጠነክሩ ሰራዊታችንም ይጠነክራል።

(ማስታወሻ ፣ ኦዲዮው ሙሉ ለሙሉ አላለቀም)
(የጻድቃን ሚስጥራዊ ንግግር ነው)

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *