የአፍሪካ ኅብረት “ ድርድሩ በይፋ ሊጀመር ነው።”

0
0 0
Read Time:53 Second

የአፍሪካ ኅብረት የሰላም_ንግግሩን የሚመሩ አካላትን፤ ቀንና ስፍራን አሳውቆ የሰላም ውይይቱ እንዲጀመር ኦፊሴላዊ ጥሪ ማቅረቡ ተሰምቷል።

ይኸው በአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ የቀረበው ጥሪ እንደሚያሳየው፦

– የውይይት ቦታ 👉 ደቡብ አፍሪካ

– የውይይቱ ቀን 👉 ከፊታችን ጥቅምት 8/2022 ጀምሮ

– የሰላም ውይይቱ የሚመራው 👉 በቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዜዳንትና በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ

– የሰላም ሂደቱ ፓናሊስት ሆነው የሚያገለግሉ 👉 የቀድሞ የኬንያ ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፉምዚሌ ምላምቦ ንጉካ ናቸው።

የአፍሪካ ኅብረት ግብዣውን ለኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እንዲሁም ለህወሓት ነው ያቀረበው።

የአፍሪካ ህብረትን ግብዣ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት #መቀበሉን በይፋ አሳውቋል። ነገር ግን የውይይቱን መሪዎች፣ ቀንና ቦታ በዝርዝር አልገለፀም።

መንግስት ” የአፍሪካ ኅብረት ግብዣ መንግሥት ከዚህ በፊት ያቀረባቸውን አቋሞች የጠበቀ ሆኖ ተገኝቷል ” ብሏል።

” ንግግሩ በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ብቻ እንዲሆንና ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲደረግ መንግሥት አቋሙን ሲገልጥ መቆይቷል ” ሲልም አስታውሷል።

” ግጭቱን ለመፍታት ሁሉንም ዓይነት የመፍትሔ ርምጃዎች ለመውሰድ ስንቀሳቀስ ቆያቻለው ” ያለው የፌዴራል መንግስት ” ይህንኑ አጠናክሬ እቀጥላለሁ ” ብሏል። 

እስካሁን ድረስ በህወሓት በኩል ለዚሁ የአፍሪካ ህብረት የሰላም ንግግር ግብዣ ይፋዊ ምላሽ አልተሰጠም።

NB. ከላይ የተያያዘው በሙሳ ፋኪ የተፈረመው ደብዳቤ ለፌዴራል መንግስት እና ለህወሓት የተላከ መሆኑን ሮይተርስ ከዲፕሎማቲክ ምንጮች ማረጋገጡ አሳውቋል።

Happy
Happy
100 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *