የአውሮፓ ህብረት “በኢትዮጵያ የፌስቡክ ገፄ ተጠለፈብኝ” “ሀክ ተደርጌ ነው”ይላል።

0
0 0
Read Time:56 Second

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ይፋዊ የተረጋገጠ የፌስቡክ ገፅ ላይ የተጋራው የአንድ ግለሰብ አካውንት መልዕክት በበርካቶች ዘንድ ውግዘት ያደረሰ ሲሆን የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያሀክ ተደርጌ ነውብሏል።

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ በፌስቡክ ገፁ ላይ ያጋራው ከላይ የተያያዘውን “Adisalem Desta” የተባለ ግለሰብ ፅሁፍ ሲሆን ፅሁፉ ” የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ኃይሎች በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚቀርበውን ጥሪ ቸል በማለት የዘር ጭፍጨፋ ጦርነታቸውን እያባባሱ ነው / መላውን ትግራይ በመቆጣጠር የዚህን ሳምንት በአፍሪካ ህብረት መሪነት የሚካሄደውን የሰላም ንግግር የትጥቅ ማስፈታት ስነስርዓት ለማድረግ ነው ። ” የሚሉና ሌሎች ሀሳቦች የያዘ ነው።

ይኸው ፅሁፍ በገፁ ላይ ለ25 ደቂቃ ያህል የቆየ ሲሆን እጅግ በርካታ ሰዎች በአስተያየት መስጫው ላይ ከፍተኛ ውግዘት እና ተቃውሞ አሰምተዋል።

” ዓለም አቀፉ ተቋም የህወሓትን ቡድን ፕሮፖጋንዳ በግልፅ ማሰራጨቱን፣ ተቋሙ በሽብርተኝነት የተፈረጀውን ህወሓትን የመደገፍ አላማ እንዳለው፣ በዚህ ድርጊቱም ሊያፍር እንደሚገባ ” በመግለፅ ድርጊቱን ኮንነዋል።

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ልዑክ በገፁ ላይ የነበረው ፅሁፍ የጠፋ ሲሆን ብዙም ሳይቆይ ገፁ ” ተጠልፎ/ሀክ ተደርጎ ” እንደነበር ገልጿል።

ልዑኩ፤ “ዛሬ አካውንታችን እንደተጠለፈ እና ፖስት እንደተደረገ ለማሳወቅ ይወዳል” ያለ ሲሆን “ይህ የአውሮፓ ህብረት / በኢትዮጵያ የአውሮፓ ልዑክ ይፋዊ መልዕክት አይደለም” ብሏል።

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ልዑክ አካውንቱን መልሶ መቆጣጠሩን አመልክቶ ከጠለፋው (ሀክ መደረጉ) ጋር በተያያዘ ያለውን ሁኔታ እየመረመረ መሆኑን ገልጿል።

“ሀክ ተደርጌ ነው” ባለበት ፅሁፉ የአስተያየት መስጫውን #ቆልፎታል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *