ከአማራ ማህበር በዩናይትድ ኪንግደም የተሰጠ የአቋም መግለጫ።

0
0 0
Read Time:4 Minute, 19 Second

24 December 2022

የአማራ ህዝብ እንደሚታወቀው በመዋቅራዊ ጥቃት ብዙ መሰዋዕትነት መክፈል ከጀመረ ከሰላሳ አንድ አመታት በላይ አስቆጥሯል ዛሬም መደመርበተባለ ማግሥት በመንግሥትመዋቅር በወለጋ፣መተከል፣ ሸዋ እና በመላው ኢትዮጵያ የመንግሥት ታጣቂዎች የኦሮሞ ልዩ ሃይል; ኦነግ ሼኔ(ኦነግ), ጋቻሲሪና እና ኦዴፓ ብልፅግና ተጣምረው ዘር ማጥፋት እየፈጸሙ ባሉበት ሰዓት, አማራ ፋኖ እራሱን ለመከላከል የያዛትን መሣሪያ ይፍታ ማለት አጠያያቂ እና ሁሉም ማህበረሰብ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። ለሞቱት ፍትህ፣ ጉዳት ለደረሰባቸው የሞራል ካሣ, ይቅርታና እንዲሁም ንብረታቸው ለወደመባቸው ድጋፍ ተደርጎ ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ አስፈላጊው ጥበቃና ዋስትናም እንዲሰጣቸው,፣ ካላግባብ የተነጠቁት የአማራ አንጡራእርስት ወልቃይት፣ እራያ፣ ደራ እናመተከል ወደማንነታቸው እንዲመለሱ። አማራየማነንም ባህልም ሆነ ቋንቋ አትጠቀምብሎ አልከለከለም ዛሬ ከ80 ቋንቋ በላይ ተናጋሪ ባልነበረም ነበር, አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የአፍሪካ መዲና, በማንነት ከመጣ ደግሞ ባለቤት ያላት ማንኛውም ሕዝብ በጋራ የሚኖርባት ከተማ።

 1. የሕሊና እስረኞች, አቶ ታዲዮስ ታንቱ, መምህርት መስከረም አበራ, የአማራ ልሂቃን, ማህበራዊ አንቂዎች, ጋዜጠኞች, ፖለቲከኞች, ወጣቶችን እና የባልደራስ አባላት የመናገርመብታቸውን በመግፈፍ እንደ ወንጀለኛ በማፈን ማሰር, መግደል እንዲሁምንፁሃንን ማሳደድ፣ ማፈናቀል በአስቸኳይ እንዲቆም እና እንዲፈቱ እንጠይቃለን።
 2. በአዲስ አበባ ተማሪዎችን ተረጋግተው እንዳይማሩ የሚደረገው ትንኮሳና ማሸማቀቅ የትም የማይደርስ ቅዠትን ለማስፈፀም, የተረኛው መንግሥት በበላይነት የሚሄድበት የፈጠራ ታሪክን ሳይሆን, እውነታውን በመገንዘብ ኦሮሞ ከህዝብ ጋር ተስማምቶ ካልኖረ; የታሪክ እውነታን ትቶ ገመድን እንጎትት ከተባለ ጉዳቱ ለማን እንደሚሆንይታወቃል። ስለዚህ ስለሕዝባችሁ በማሰብ ተበደልን የሚባል የዝቅተኝነት ስሜት በቋንቋና በባንዲራ መቀየር የሚፈታ ሳይሆን እኔም አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ነኝ ብሎ እራሱን በማሳመን ችግሩን መፍታት እና አማራ በማንነቱ የሚደርስበት ሥቃይ በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን።
 3. በኦሮሞ ክልል በወለጋ የሚኖረው አማራ በገዛ አገሩ የመኖር መብቱ ተገፎ ከሰው ስብዕና በወረደ መልኩ በዚህ በ21ኛ ክፍለዘመን አይደለም በየትኛውም ዘመን ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ አይነት በወለጋ በየቀኑ በመቶዎች-በሺዎች የሚገደሉበት የሚጨፈጨፉበት አሳዛኝ እና ልብ ሰባሪው የንፁሃን እልቅትና የመንግሥት ሙሉ ሎጅስቲክ አቅርቦት እና መዋቅራዊ ሽፋን የሚሰጥበት የሰው ቄራው እርጉዞችን ፣ ህፃናቶችን፣ ሴቶችን እና አዛውንቶችን በመጨፍጨፍ የሚገነባ አዲስ ነገር ማምጣት አይደለም ያለህበትንም የሚያሳጣ መንግሥታዊ ፋሽሽትነት በአስቸኳይ እንዲቆም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋን እንዲያስቆምና ወንጀለኞችን ለፍርድ እንዲያቀርብ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
 4. ከአማራ ክልል ወደ መናገሻ ከተማው አዲስ አበባ የሚመጣውን ተጓዥ መንገደኛን በሰላም ወጥቶ መመለስ ያልቻለባቸው ጊዜዎች መበራከትና የኦነግ ሠራዊቶች ሲዘርፉ ንብረት ሲያወድምና ህዝብን ሲያርድ፣ሲያፍን ዝምታን የመረጠው ተባባሪው መንግሥት ተጠያቂ ነው! ከጎንደር, ከጎጃም አዲስ አበባ መስመር በኦነግ የሚታገቱ አማራዎች እስከ አንድ ሚሊዬን ብር እንዲከፍሉ የሚጠየቁበት እና ገንዘቡ የሚከፈለው በኦሮሚያ ባንክ መሆኑ ስለተረጋገጠ የመንግሥት እጅ እንዳለበት የሚያሳይ ስለሆነ ይህ አካል አገርና ህዝብን በሰላምና በብቃት ያስተዳድራል ብሎ መጠበቅ ከእባብ እንቁላል እርግብ እንደመጠበቅይቆጠራል, ስለዚህ የወንጀለኛው አካል የሆነው የአብይአህመድ መንግሥት በአስቸኳይ ስልጣኑን ለህዝብ እንዲያስረክብ እንጠይቃለን።
 5. የአማራ ህዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እራስህን-ፋኖን እና አገርህን ለማዳን በአንድነት በመነሳት ከስርህ በወጡ ሆድ አደር ከሃዲዎች ከእኩይ ተግባራቸው እንድታስቆም, አልመከርካለም ተገቢውን እርምጃመውሰድ ጊዜው የሚጠይቀው የህልውና ትግሉ አካል ነው። ብአዴን ማለት በተወረርህበት ሰዓት ጥሎ የፈረጠጠ የተረጋጋ ሲመስለው ደግሞ ተመልሶ አንተን የሚያሳድድ፣ የተላላኪ ስብስቦችን አሳፍረህ አሰናብተው። መላው የአማራ ሕዝብ በፋኖዎች ላይ የሚደርሰውን የተቀነባበረ ዘመቻ ለማስቆም አስፈላጊውን ጫና በማድረግ የአማራ ህዝብ ውስጣዊ ጠላቶቹን ለመመከት ሕዝባዊ አመፅ እና ተገቢውን ትግል እንዲያደርግ እናሳስባለን።
 6. የአማራ እሴት በሆነው “ሽምግልና” ስም አታሎ በማምጣት ውንብድና የተፈፀመበት ጀግናው አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሤ እና ባልደረቦቹ እንዲሁም ከ25,000 በላይ በግፍ የታሰሩ ፋኖዎቻችን ካለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ! መላው የአማራ ሕዝብ ፋኖ እራስን የመከላከል ተፈጥሯዊ መብትህን በመጠቀም አልታሰርም በማለት ከፊትህ የቆመውን ተላላኪ ማሰብ ከተሳነው በሚገባው ቋንቋ አስተናግደው, በአራቱም ማዕዘን በጠላት በከፍተኛ ዝግጅት ጦር እየሰበቀ በከበባ ውስጥ ያለን ማህበረሰብ ትጥቅ ፍታ ማለት ተቀባይነት የሌለው ስለሆነ መብትህን በክንድህ እንድታስመልስ ጥሪ እናደርጋለን።
 7. አብይ አህመድ አሊ እና ተመስገን ጥሩነህ, ከህግ በላይ ህግ ሆነው አማራን ባለበት እያሳፈኑ ፍርድ ቤት የፈታውን ከህግ በላይ በመሆን መልሰው በማሰር አማራ የሲዖል ህይወትን እንዲገፋ እና ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማጥፋት በመንግሥት ድጋፍና አመራር እየተሰጠ በወለጋ፣ በመተከል ሰው መርጦ ባልተፈጠረበት ማንነትና በውሸት ትርክት የተጀመረው የአማራ ህዝብ እንደ አውሬ ተጨፍጭፎ ዘር ማጥፋት እየተፈፀመበት, እንዲሁምየአማራ ተማሪዎችን የዩንቨርስቲ መግቢያ ውጤት መቀነስ እና ከዚህ ሁሉ መሰናክል አልፈው ትምህርታቸው ላይ የተገኙትን ተማሪዎች ማስገደል፣ ደምቢዶሎ ዩንቨርስቲ ከሦስት ዓመት በፊት የታፈኑ 17 ሴት ተማሪዎች ሳይገኙ አሁንም ለሁለተኛ ጊዜ ከ26
  ተማሪዎች በላይ ታግተዋል። ለዚህም ትምህርት ሚኒስትር እና የፌደራሉን መንግሥት የተማሪዎችን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ የመንግሥት የሥራ ድርሻ ስለሆነ ልጆቻችንን የደረሱበትን በአስቸኳይ እንዲያሳውቅ እንጠይቃለን።
 8. ብአዴን, አማራ ነን ባሉ በከሃዲ ምስለኔዎች የተሞላው የአለቃችውን ትዕዛዝ ተቀብለው ፋኖን ለማጥፋት የሚጋጋጡ በአማራው ጠላት የደህንነት ሹሙ ተመስገን ጥሩነህ, ደመቀ መኮንን , ግርማ የሺጥላ, አገኘሁ ተሻገር በመሳሰሉ የአስተሳሰብ ሰንካሎች በፋኖ፣ ሚኒሻና ልዩ ሃይሉን እንዲሁም ወጣቶችን በማፈን አጎንባሽነቱን ያስመሰከረ ስለሆነ በአጠቃላይ የአማራ ህዝብ እና የሰለጠነው ፋኖ በጋራ በመቆም, ወጥመዱን እንዲሻገር ፣ በአማራ ክልል የገባው አማረኛ ተናጋሪው የኦነግ ሠራዊት ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ ከውስብስብ ችግሮች እንድትወጣ እያሳሰብን ይህን በማንነቱ የመጣውን አደጋ እንዲቀለብስ ለመላው አማራ ጥሪ እናደርጋለን።
 9. የክልሉ መንግስት አመራሮች (ሰው የሆናችሁ) በተለይም በፀጥታ መዋቅሩ አመራርነት ላይ ያላችሁ ወንድሞቻችን የፋኖ እና የአማራ ልዩ ኃይል መሰልጠን፣መደራጀት እናመታጠቅአገርንእና ወገንንከውርደት የሚታደግ መሆኑንተገንዝባችሁ ከፋኖው ጋር በመተሳሰብ የህልውና ሥጋት በሆኑ ጠላቶቻችንላይ በአንድነት በመቆም ከመጣው ጥፋት እና ከክልሉ ውጭ የሚኖረውን አማራ እንድትታደጉ፣ የአንድም አማራ ፋኖ ህይወት እንዳይጠፋ ከተላላኪ ጥቅመኛ ባንዳዎች ትንኮሳን አስቁማችሁ አማራ የተጋረጠበትን አደጋ ሰብሮ እንዲወጣ በትጥቅና ስንቅ እገዛ በማድረግ የመሪነቱን ድርሻ እንድትወጡ እንጠይቃለን።

የወገናችን የአማራ ጉዳይ ከትላንቱ ዛሬ የባሰና የአብይ አህመድ መንግሥት በተቻለ መጠን ኢትዮጵያን ብለው ጠንክረው የቆሙትን አገር ፈጣሪና ምሰሶዎችን መንቀል ከዛም ነጥሎ መምታትና ማደከም፣ እየተካሄደ ያለውን የአማራን ዘር የማጥፋት መንግሥታዊ ዘመቻ ከአረገዘች እናት፣ ህፃናትን , አዛውንቶችን በጭካኔ ማረድ፣ ቤት ዘግቶ ሙሉ ቤተሰብን ማቃጠል የሰው ሥጋ መብላት ደም መጠጣትን እያስፈፀሙ, በአገርም በአለም አደባባይ መወገዝ ያለበትና አገር አፍርሶ የኦሮሙማ አገር ለመመሥረት ቅርስ ማጥፋትና ስለእውነት የተናገሩና የሞገቱትን, እንደ አቶ ታዲዮስ ታንቱ እውነት ተናጋሪዎችን ማሳደድና ማሰር ፣ ኢትዮጵያ በእራሷ የተቀረፀ ፊደልና መግባቢያ ቋንቋ ያላት፣ የአፍሪካ የነፃነት ምልክት የሆነችው አገራችንንበጋራ የምንኖርበት የሁላችን መሆኗንበመገንዘብ የዘረኛውና ህዝብን የናቀው የአብይ አህመድ መንግሥትን በማስወገድ ህዝባችንተከባብሮና በሰላም የሚኖርበት አገርለማድረግ መላውሰላም ወዳድህዝባችን በጋራ በመቆም ነፃነቱን እንዲያስከብር ጥሪ እናቀርባለን።

ኢ-መደበኛ መንግሥት እንጂ, ኢ-መደበኛ ህዝብ-ፋኖ የለም!
አማራ በልጆቹ ትግል ነፃነቱን ይጎናፀፋለ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *