የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጨፎ የተመራ ልዑክ መቀሌ ገባ።

Read Time:23 Second

መቐለ የሚገኘው የፌዴራል መንግስት ልዑክ ፦
– በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጨፎ የተመራ ነው።
– ልዑኩ ከ50 በላይ አባላት ያሉት ሲሆን ሚኒስትሮች፣ የፌደራል መስርያ ቤት ዋና ኃላፊዎች እና ዲፕሎማቶች ይገኙበታል።

– በልዑካን ቡዱኑ የጠ/ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፣ የፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ፣ #የኢትዮ_ቴሌኮም ዋና ስራ ስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሪት ፍሬህይወት ታሙሩ ፤ #የባንክ_ኃላፊዎች በርካታ ሚኒስቴሮች ይገኙበታል።

– የፌዴራሉ መንግሥት ልዑክ ፤ ዛሬ መቐለ መግባቱ የሰላም ስምምነቱን ተግባራዊነት እንደሚያጠናክረው ታምኗል።
Credit : Demtsi Weyane