የፌዴራል ፖሊስ መቐለ ከተማ ገብቶ ኃላፊነቱን መወጣት ጀምሯል።

Read Time:33 Second

የሰላም የስምምነቱን አፈፃፀም የሚከታተለዉ የአፍሪካ ህብረት የክትትል፣ ማረጋገጥ እና ማስከበር (monitoring, verification and compliance) ቡድን በይፋ ተቋቁሟል።
• የተልዕኮ ቡድኑ 3 አባላት ያሉት ሲሆን በሰላም ስምምነቱ መሰረት የሲቪልና ወታደራዊ ስምምነቱን አፈፃፀም የሚከታተል ይሆናል።
• ሜጀር ጀነራል ራዲና ስቴፈን ከኬንያ፣ ኮሎኔል ሩፋይ ኡመር ማይሪጋ ከናይጄሪያ ፣ ኮሎኔል ቴፎ ሰኮል ከደቡብ አፍሪካ የተልዕኮ ቡድኑ አባላት ሆነው ተሰይመዋል።
• አባላቱ በዛሬው እለት የፌደራል ፖሊስ በመቐለ ከተማ ያሉ የመንግስት ተቋማትን የማረካከብ ሂደትን አስፈጽመዋል።
• የአፍሪካ ህብረት የክትትል፣ ማረጋገጥ እና ማስከበር ኮሚቴ ኣጉላዕ ተገኝቶ የትግራይ ኃይሎች የካባድ መሳርያ ትጥቅ የተሰበሰበበት አከባቢ ጎበኝቷል።
– የፌዴራል ፖሊስ መቐለ ከተማ ገብቶ ኃላፊነቱን መወጣት ጀምሯል።

– የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከመቀለ በቅርብ ርቀት ላይ ወዳለችው አጉዕላ ገብተዋል ፤ የትግራይ ኃይሎች የፈቱትን ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ይረከባሉ።
Photo Credit : ebc