የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ሠራተኞቹ ከቢሮ ሳይወጡ ከ2 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ አላግባብ አበል መክፈሉ ተገለጸ፡፡

0
0 0
Read Time:59 Second

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስደዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ ታሕሳስ 19/2015 የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ምርምር ልማት ማዕከልን የ2013 በጀት ዓመት ሂሳብ ኦዲት ሪፖርት ባደመጠበት ወቅት ነው፡፡

የማዕከሉ ሠራተኞች ባልተሳተፉበት ስብሰባ አበል ያወራርዱ እንደነበር እና ከሕግ አግባብ ውጭ የሆኑ ግዥዎች ሲፈጸሙ ነበር ተብሏል፡፡

በዚህም ከ46 ሺሕ ብር በላይ ከመስሪያ ቤቱ ውጭ ላሉ ባለሙያዎች ክፍያ ተፈጽሟል የተባለ ሲሆን፣ ከ204 ሺሕ ብር በላይም ለጸረ ሙስና ኮሚሽን ባለሙያ በሕግ አግባብ ውጭ የተከፈለ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ መላኩ አለበል፤ ሠራተኞች ከቢሮ ሳይወጡ የተከፈለው 2 ነጥብ 96 ሚሊዮን ብር ሙሉ በሙሉ የባከነ ነው ወይስ በውስጡ ህጋዊ ወጭዎች ተካተውበታል የሚለውን እያጣራን ነው ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

አላግባብ ከወጣው በጀት ገንዘቡ እንዲመለስ እንዲሁም አጥፊዎችን ለህግ እንዲቀርቡ እንሰራለም ሲሉ አክለዋል፡፡

በማዕከሉ እያንዳንዱ የኦዲት ግኝት ላይ የፋይናንስ ህግ ጥሰት፣ የበጀት አጠቃቀም ጉድለት፣ የንብረት አያያዝ ችግር እንዲሁም ሰፋ ያሉ የስነምግባር ብልሽቶች እንዳሉ ቋሚ ኮሚቴው አስገንዝቧል፡፡ ፍትህ ሚኒስቴር በተፈጸሙ ጥፋቶች ላይ በቂ ምርመራ በማድረግ በኹለት ወር ጊዜ ውስጥ እንዲያሳውቀን ሲል አሳስቧል፡፡

ተቋማት የፋይናንስ ህጎችን በቸልተኝነት በመጣስ የመንግስትና የህዝብ ገንዘብ በተለይም በአበል፣ በግዥ እና በጨረታ አላግባብ እየባከነ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በኦዲት ግኝቶች ላይ ተገቢ የሆነ ክትትልና እርምጃ የሚወስድ ጠንካራ ተቋምና አካል ባለመኖሩም፣ በማዕከሉ ከ2010 ጀምሮ የተገኙ የኦዲት ግኝቶች እስካሁን ማስተካከያ አልተሰጠባቸውምም ተብሏል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *