ማኅበረ ቅዱሳን የስርጭት አገልግሎት እንዳይሰጥ እግድ ተጣለበት

0
0 0
Read Time:45 Second

የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን የስርጭት አገልግሎት እንዳይሰጥ እግድ ተጣለበት

ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ ዛሬ ግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም ሰበር ዜና በሚል ባሰራጨው ዘገባ ምክንያት፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ጊዜያዊ እግድ ጣለበት።

ባለስልጣኑ እግዱን የጣለው፣ ጣቢያው “ሰበር ዚና” ያሰራጨው ዜና፣ ከሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን ሚና ውጪ በሆነ አግባብ፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያካሄደውን ስብሰባ የሚያውክና ህዝብን ለግጭት የሚያነሳሳ መልዕክት መሆኑን በማረጋገጡ መሆኑን ዛሬ ግንቦት 13 ቀን 2015 ዓም በባለሥልጣኑ የሕዝብ፤ የማህበረሰብና የሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን ክትትልና አቅም ግንባታ ዳይሬክተር አቶ አብዩ መኮንንፊርማ ወጪ የተደረገው ደብዳቤ ይገልፃል።

በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ድንጋጌ መሠረት የሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን፣ በሐይማኖት ተከታዮች መካከል የእርስ በእርስ ግጭት ማነሳሳት ወይም በሐይማኖት ተከታዮች መካከል አለመቻቻል እንዲፈጠር መቀስቀስ እንደሌለባቸው መደንገጉን የጠቆመው ባለስልጣኑ፣ የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥንግን የመገናኛ ብዙኃን አዋጅን የሚተላለፍና በአገር ሁለንተናዊ ሰላም ላይ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል ዘገባ ማስተላለፉን ገልጿል፡፡ በመሆኑም ከጉዳዩ አጣዳፊነትና ሊያስከትለው ከሚችለው ጉዳት አንፃር በቀጣይ በባለሥልጣኑ ቦርድ ታይቶ ዘላቂ ውሳኔ እስከሚሰጥበት ጊዜ ድረስ የጣቢያው ፈቃድ በጊዜያዊነት መታገዱን አሳውቋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *