የመብራት ኃይል በመላሀገሪቱ ተቋርጦ መዋሉን የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክኃይልአስታወቀ‼️

0
0 0
Read Time:31 Second

ዛሬ ከቀኑ 09:46 ጀምሮ ከባህርዳርና አካባቢው በስተቀር የኤሌክትሪክ ኃይል በመላው አገሪቱ መቋረጡን ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል በማህበራዊ ትስስር ገፁ በሲስተም ላይ በገጠመ ችግር ኃይል መቋረጡን እና ለጊዜው የችግሩን ምክንያት ለማወቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል።

የተቋረጠውን ኤሌክትሪክ መልሶ የማገናኘት ሥራ የተጀመረ ሲሆን ችግሩን በመቅረፍ ዳግም ሲስተሙን መልሶ እስከሚገናኝ ድረስ ሕብረተሰቡ በትዕግስት እንዲጠብቅም ተቋሙ ጠይቋል!

ነገር ግን አሁን ማምሻውንበመላ ሀገሪቱ የተቋረጠው ኃይል መልሶ መገናኘት ጀምሯል።

ዛሬ ከቀኑ 09:46 ጀምሮ ከባህርዳርና አካባቢው በስተቀር በመላው ኢትዮጵያ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል መልሶ መገናኘት ጀምሯል።

በዚህም መሰረት አብዛኛው የአዲስ አበባ ክፍል እና የተቀሩት የሀገሪቱ ክፍሎች መልሰው ኃይል ማግኘት ችለዋል።

የተቀሩትን አካባቢዎች መልሶ ለማገናኘት ጥረቱ ቀጥሏል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *