“የንጋቷ ኮኮብ ታሪክ አስተርአየ ብርሃን “

0
1 0
Read Time:3 Minute, 30 Second


ከአለባቸው ደሳለኝ አበሻ
(ለንደን)

እንደምን አላችሁልኝ ውድ የፊስ ቡክ ወዳጆቼ : :

በእርግጥ አንዳንድ ሀሳቦች ፣ሰወር ብለው በተመልካች ዘንድ ፣ጥያቄና የአእምሮ ሙግት ሲፈጥሩ፣ ሐሳብን ማንሸራሸር ተገቢ ነው: :
ለንደን ተዘጋጅቶ በነበረው 128ኛ የአድዋ ድል መታሰቢያ ፣.ክብረ በአል ላይ ፣ ተጋባዥ ከነበሩት የጥበብ ባለሞያዎች አንዷ የጦቢያዋ የንጋት ኮኮብ ታሪክ አስተርአየ ብርሃን ነበረች : :
ብዕሬን ከደረት ኪሴ ያስመዘዘችኝ ::
እናም ትውልዷንና እድገቷን በይደር አቆይቼው ፣ በነበረን ቆይታ ጠይቂያት የሰጠችኝን ምልስና የራሴን ምልከታ ጨምሬ ላወጋችሁ ነው : :
አለም በእርግጥ
የትያትር መድረክ ናት :: ታሪክ አስተርአየ ብርሃን
ደግሞ በጥበቡ ውስጥ የበቀለች የህይወት እስትንፋስ ፣የነፍስ ምግብ ናት : :


ትያትር የራሷ የህይውቷ አንዱ አካሏ እስክሚምስል ድረስ ስትጫወት ተመልክቼ ፣ ስቂያለሁ አልቅሻለሁ አድናቆቴን ለመግለፅ ቆሜ አጨብጭቢላታለሁ : : እኔ ብቻ ሳልሆን መላው ተመልካች አብሮ ስቆ አብሮ አልቅሷል: :
ታሪክ ብትወና ስራዎቿ ነፍስ ሆና ነፍስ ትዘራባቸዋለች : :

በአጠቃላይ
የሰው ልጆች የሚታመሙትን ሕመም ደስታቸውና ሐዘናቸውን የምትካፈል የህይወትን ውጣ ውረድ የምታሳይ ኮንፖስ ናት::
በሰው ልጆች የህይወት ገጠመኞች ውስጥ ያሉትን ምስቅልቅል እውነታዎች የሚያልፉባቸውን
የተለያዩ አስቂኝ ወይም አሳዛኝ ጊዚያቶችን መልሳ በተውኔት እየቀዳች በመድረክ ስትጭወታቸው ማየት ልዩ ክብር …ልዩ አድናቆት ያሰጣታል: :
በኔ ሚዛን በተመልካቹ ዘንድ የምትፈጥረው ትፍስህት የማይመዘንና የማይለካ ነው :: በተለይ
የተመልካቹን ቀልብ አጥብቃ የመያዝ ችሎታዋ ታዳሚውን የፈጠራው ሒደት ተሳታፊ አድርጋው ማምሸቷን አንዱ የአይን ምስክር ነኝ ::
አሁን ድረስ ይህንን ፅሁፍ እየፃፍኩ የፊቷ አገላለፅ የድምፅ አወጣጥ
አቋቋሟ በአጠቃላይ ድንቅ የሆነው ትወናዋ አንድናቆቴን እንዳልንፍጋት በምስል ይታየኛል : :

በእርግጥ የቲያትር ጥበብ በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ሰዎች ካለፈት ማህበረሰቦች የወረስዋቸውን ቁሳዊና
እለታዊ ትውፉቶች ÷ በየዕለቱ ውጣ ውረዳቸው ያካበቷቸውንና ያዳበሯቸውን ባህሎች ፣
ልምድች፣ እሴቶች በውስጡ ማንፀባረቃቸው እርግጥ ነው: :
ትያትር ተዋንያንና ተመልካች በየበኩላቸው ልብ ለልብ የሚያወያዩበት መድረክ በመሆኑ
ታሪክ አስተርአየ ብርሃን ጣራና ግድግዳ ሆና አሳይታናለች : :
ብቻ ምርጥ ተዋናይ ነች: : ከአይን ያውጣሽ !! : :


በመጨረሻ አጋጣሚውን ተጠቅሜ ስለሞያሽ ብጥይቅሽ ቅር ይልሻል አልኳት: :
ታርክ ..በደስታ ጥያቄህ ምንድ ነው?
ሞያሽን ምን ያህል ትወጅዋለሽ ?
አልኳት
ታሪክ ፣ ሞያየን በጣም እወደዋለሁ: መውደድ ብቻ አይምሰልህ ያለምንም ማጋነን ነው የምንግርህ: :
የኔ መኖር ለተውኔት እንድገት አንድ አስተዋፅዎ ያደርጋል ብየ ስለማስብ የርሴን አሻራ የማስቀምጥ ይምስለኛል ::
ጥያቄን ቀጠልኩ የምትወክያቸውን ገፀ ባህሪያት በትክክል ተጫውተሽ ተዋጥተውልኛል ትይለሽ ?
መለኪያሽ ምንድ ነው?

ታሪክ…በእኔ ግምት የምጫወታቸው ገፀባህሪያት በእውኑ አለም ያሉ ሰዎች በመሆናቸው እነሱን ነው የምወክለው: :
ሰው በባህሪው ደካማም ጠንካራም ፣ ቸርም ስስታምም፣ አፍቃሪም ግደለሽም ወዘተ ነው
ስለዚህ ወክዬ የምጫውታቸው ገፀ ባህራያት እንደሰው
የሚናገሩ፣ የሚያዲምጡ፣ የሚበሉ የሚጠጡ፣ በመሆናቸዉ በምናብ ሳይሆን በአንድ ወቅትና ቦታ የማውቃቸው ሰዎች እስኪመስሉኝ ድረስ ባህሪያቸውን ወክዬ ለመጫዎት እጥራለሁ: ፡
ሌላው በልምምድ ውቅት
የምወክላቸውን ባህሪያት እያንዳንዱን እንቅስቃሴ
ተአማኒነት እንዲኖራቸው ለማድረግ
በግዴለሸነት ሳይሆን
በጥንቃቄ ነው የምለማመዳቸው: :

ጥያቄ .. ትልቁ የሞያ ስኬትሽ ሚስጥሩ ምንድ ነው ? አላማዬን አሳክቻለሁ ብለሽ ታስቢያለሽ ? : :
ታሪክ …ሚስጥሩ አስተዳደጌ ይመስለኛል ::
ከልጅነቴ ጀምሮ በትምህርት ቤት ትያትር ስጫዎት ነው ያደኩት: :
እኔን ለማገዝ ቅን የሆኑ ደጋግ ኢትዮጵያዊያኖችና
አስተማሪዎቼ
የወላጆቼ ድጋፍም ስላልተለየኝ አሁን ለደረስኩበት ስኬት መሰረቱን የጣሉት እነሱ ናቸው : :
አባቴ በቤተክህነቱ ውስጥ ትልቅ ሊቅ ናቸው :: የናትና አባቴ ቤተሰቦችም በሙሉ አራት አይና የሚባሉ የቤተክርስቲያን መርጌታዎች(ሊቆች) ናቸው: :
ከነሱም ብዙ ቱርፋቶችን አግኝቻለሁ: :
ሁሉንም ክብር የሚወስደው ግን እጄን ይዞ ለዚህ ያበቃኝ ፈጣሪዬ እየሱስ ክርስቶስ
ብቻ ነው: : ክብሩ ሁሉ ለሱ ይሁንልኝ :: ከነጉድለቱም ቢሆን አላማዬ ተሳክቷል ::
ነገር ግን ገና ብዙ ህልም አለኝ ::
ጥያቄ : ተሳክቶልኛል ስትይ ምን ማለትሽ ነው: :

ታሪክ .. ገና ከልጅነቴ ጀምሬ አዲስ አበባ ዩኒቭርስቲ ገብቼ ትያትር ማጥናት እስከጀመርኩበት ድረስ መፈክሬ ይቻላል ነበር !! ለመጀመሪያ ጊዜ እነ ወጋየሁ ንጋቱ ፣ አለም ፀሀይ ወዳጆ እነ ደበበ እሸቱ ተክሌ ደስታ ጌትነት እንየው ብዙ ስመጥር አርቲስቶች … የዘበኑበት ብሔራዊ ትያትር ቤት መድረክ ላይ ቆሜ ስጫወት በትክክል ስኬት ላይ እየድረስኩ መሆኔን ምልክቱን ያየሁትበት አጋጣሚ ነው ። ለዚህ ላበቃኝ እግዚአብሔር ምን ምንግዜም ምስጋናዬ ይድረስልኝ: : ክብሩን እሱ ይውሰድ : :
ቀጠልኩ :: በሞያሽ ውስጥ ለአንች ደስታ የሚፈጥርልሽ ምንድ ነው ?
ታሪክ .. በጣም አስደሳቹ ነገር በተመልካቾችና በአናቂዎቼ እንዲሁም በሞያ ጏደኞቼ የሚሰጡኝ ማበራታቻ ሞራልና አድናቆት ናቸው : : ስራወቼን እንዴት በትኩረት እንደሚከታተሉት
ስለምረዳ እደሰታለሁ ::
ሌላው ውጤታማ የሚደርገኝ በልምምድ ወቅት አላሾፍም ዳይሬክተሩን በትወናዬ እስከማሳምን ድረስ ልምምዴን እቀጥላለሁ ።
በተረፈ ከሌሎች የሞያ አጋሮቼ ጋር በትብብርና በፍቅር መስራትን ያስደስተኛል: :
እራሴን ማወዳደር ብዙም አልፈልግም ::
የመጨርሻ ጥያቄ ነው::
ያዘንሽባቸው ገጠመኞች አሉሽ
ማለት ይህ ባይሆን ጥሩ ነበር የምትይው?
ታሪክ ስው አይደለሁ ::
ይኖራል እንጂ …ጥቂት ዝምታ !
ብቻ …ብዙም ዝርዝር ውስጥ ባልገባ ደስ ይለኛል ::
እንደምታውቀው ሙያው ከተለያዩ አቅጣጫዎች ብዙ ጫና ያለበት በመሆኑ ብልህነትን አስተዋይነትንና፣ ታጋሽነትን ግልፅነትን ይጠይቃል ::
ለሴት ልጆች challenging ከባድ ነው: : ያው ይገባሀል ብዬ አምናለሁ: :እነዚህን ሁሉ በፅናት ተቋቁመህ ነው የስኬት ጣራ ላይ ለመድረስ የምትፍጨረጨረው ::
ወደፊት አስተሳሰባችን ሲሞረድ አይምሮአችን ከተለመደው. አስተሳሰብ ሲላቀቅ ጤነኛ አመለካከት ይኖረናል ብየ እገምታለሁ ።
አመለካከታችንን ከለወጥን ሁሉም ነገር ይለወጣል። አመለካከታችንን ስንለውጥ ፤ የምናያቸው ነገሮች ሁሉ አብረውይለውጣሉ።
መቼ? የሚለውን ግን መመለስ አልችልም : :
በኔ በኩል ጥያቄዬን ጨርሻለሁ ስለሰጠሽኝ ጊዜ አመሰግናለሁ: :
ታሪክ አንድ ነገር ሳልናገር ብቀር ግን
ቅር ይለኛል: : ሞያየን አይተህ ለሰጠህኝ ክብርና ምስጋና ከልቤ አመሰግናለሁ: : እንዳንተ ያሉ ንፉግ ያልሆኑ ደጋግ ኢትዮጵያዊያ ቢኖርልን
ደግሞ ለሞያችን ከፍታ መሰላሎች ይሆኑንን ነበር ..እናም ወንድምዬ እባክህ ምስጋናዬን ተቀበለኝ: :
ክብረት ይስጥልኝ ሌላ ምን እላለሁ : :
እኔም በድጋሚ አመስግኜ የንጋቷን ኮኮብ ታሪክ አስተርአየ ብርሃን ” ተሰናበትኩ: :
በሌላ ዝግጅት እስከምንገንኝ ቸር ይግጠመን: :
ትሸርት

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *