መሐመድ ከሌፍ (ሼንጎሌ) ጨምሮ ሶስት የአልሻባብ አመራሮች ተደመሰሱ

0
0 0
Read Time:33 Second

የአልሻባብ ቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ኃላፊን ፏአድ መሐመድ ከሌፍ (ሼንጎሌ) ጨምሮ ሶስት የቡድኑ አመራሮች ተደመሰሱ።

የአልሻባብ ቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ኃላፊን ፏአድ መሐመድ ከሌፍ (ሼንጎሌ) ጨምሮ ሶስት የቡድኑ አመራሮች መደምሰሳቸውን የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊና ጊዜያዊ የፀጥታ ኮማንድፖስት አስተባባሪ ሜጀር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ተናገሩ።

ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ እንደተናገሩት፤ ባለፉት ቀናት ከኢፌዴሪ አየር ኃይል ጋር በመቀናጀት በተወሰደው ርምጃ የሽብር ቡድኑ ኢትዮጵያን ለማጥቃት ያዘጋጃቸውን የትጥቅና ስንቅ ዴፖዎች ማውደም ተችሏል፡፡

በተጨማሪም የአሸባሪ ቡድኑ አመራሮችና ታጣቂዎች በተወሰደው ርምጃ ተደምስሰዋል። ከተደመሰሱት ውስጥ የአልሸባብ ከፍተኛ ኮማንደሮች ውስጥ:-

1. ፏአድ መሐመድ ከለፍ (ሼንጎሌ) የአልሸባብ ቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ሃላፊ፣

2.አብዱላዚዝ አቡ ሙሳ የአልሸባብ ቃል አቀባይ፣

3.ኡቤዳ ኑር ኢሴ የአልሸባብ የቦኮል ዞንና የኢትዮጵያ ድንበሮች አዋሳኝ ሃላፊ መደምሰሳቸውን ሜጀር ጄኔራል ተስፋዬ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *