በቤኒሻንጉል ክልል በሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ላይ በተከፈተ ተኩስ 34 ሰዎች ባሰቃቂ ሁኔታ ሳይገደሉ እንዳልቀረ ኮሚሽኑ አስታወቀ

0
0 0
Read Time:52 Second

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ቅዳሜ ኅዳር 5 ቀን 2013 ዓ.ም. ሌሊቱን፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በደባጤ ወረዳ ከወንበራ ወደ ቻግኒ በመጓዝ ላይ በነበረ የሕዝብ ማመላሻ አውቶብስ ላይ በህገወጥ ታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ በ34 ንፁሃን ተጓዦች ላይ ዘግናኝ ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ። ኢሰመኮ በደረሰው መረጃ መሰረት በተመሳሳይ ወቅት በሌሎች የክልሉ ወረዳዎች (ውብጊሽ፣ያምፕ እና ቂዶህ) ጥቃት መሰንዘሩንና ለጊዜው ሕይወታቸውን ለማዳን የሸሹ ሰዎች መኖራቸው በመነገሩ፣ በአሁኑ ወቅት የሚገመተው የተጎጂዎች ቁጥር 34 ቢሆንም ሊጨምር እንደሚችል ገልጿል። የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ “ይህ ጥቃት ሁላችንም በጋራ የተሸከምነውን(ዶ/ር) የሰው ሕይወት ክፍያ ዛሬም በአሳዛኝ ሁኔታ የሚያሻቅብ ነው። የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በፍጥነት ጥቃቱ የበለጠ እንዳይባባስ እርምጃ መውሰዳቸው አበረታች ነው” ብለዋል።


መስከረም 16 ቀን 2013 ዓ.ም. ኢሰመኮ ያወጣውንና በክልሉ የሚከሰቱ ጥቃቶች ተደጋጋሚነትና አስከፊ ባሕሪይ በተለየ ሁኔታ ያሰመረበትን መግለጫ በማስታወስ፣ ዋና ኮሚሽነሩ እንደገለጹት “በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ፋታ የማይሰጥ ሆኖ በመቀጠሉ፤ በፌዴራልና በክልሉ መንግሥታት የፀጥታ ኃይሎች መካከል በፍጥነትና ንቁ ሆኖ መጠበቅ ላይ የተመሰረተ የተሻለ ቅንጅት ያስፈልጋል። የፌዴራልና የክልሉ የፀጥታና የፍትሕ አካላት ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር በመሆን እነዚህን ጥቃቶች ሊያስቆም የሚችል አዲስ ክልላዊ የፀጥታ ስትራቴጂ ሊነድፉ ይገባል” ብለዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *