የዶክተር ብርሃኑ እልህ በእናት ፓርቲ ተወገዘ። “ሚኒስቴሩ …እልህ መጋባቱ ከመንግስት ጠባይ የሚጠበቅ” አይደለም

0
1 0
Read Time:1 Minute, 0 Second

ተመጣጣኝ ቅጣት በማሳለፍ ድጋሚ ሊፈተኑ የሚችሉበት እድል ይመቻችላቸው ” – እናት ፓርቲ

እናት ፓርቲ በላከልን መግለጫ፤ የትምህርት ሚኒስቴር ላለፋት አስርት ዓመታት ይስተዋል የነበረውንና እንደነውር ሳይሆን እንደባህል ጭምር እየተቆጠረ የመጣውን የፈተና ሥርቆትና ማጭበርበር ለማስቀረት ተማሪዎች በዩኒቨርስቲዎች እንዲፈተኑ በማድረግ በትምህርት ጥራት ላይ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት የሄደበትን ርቀትና ጥረት በበጎ ጅምር በአድናቆት እንደሚመለከተው ገልጿል።

በዚሁ ሂደት ላይ ግን በአማራ ክልል 12,000 ገደማ ተማሪዎች “ፈተና ተሰርቋልና አንፈተንም” በሚሉና ሌሎች ምክንያቶች በወቅቱ ይሰጥ የነበረውን ፈተና ሳይወስዱ ቀርተዋል ሲል በመግለጫው አመልክቷል።

” ትምህርት ሚኒስቴር ጥቅምት 15 በሰጠው መግለጫ ፈተናውን ያልወሰዱ ተማሪዎችን ድጋሚ እንደማይፈትን አሳውቋል ” ያለው እናት ፓርቲ ፤ ” ምንም እንኳን ፈተናውን ላለመውሰዳቸው የተማሪዎቹ #ጥፋትና #ሓላፊነቱንም ራሳቸው የሚወስዱ ቢሆንም ምን አልባት ክልሉ በአጠቃላይ ከቆየበት ሁኔታ፣ ልጆቹ ያሉበት እድሜ እና መሰል ውዥንብሮች ተጽዕኖ አድርገውባቸው በመሆኑና በጥቂቶች ጥፋት አብዛኞቹ ሰላባ በመሆናቸው የተፈጠረ ችግር ነው ብለን እናምናለን ” ብሏል።

ፓርቲው፤ ሚኒስቴሩ በአንድ በኩል ለወጥ የሄደበትን ርቀት የሚያጠለሽበት በመሆኑ በሌላ በኩል እልህ መጋባቱ ከመንግስት ጠባይ የሚጠበቅ ባለመሆኑን የልጆቹን የዓመታት ድካም፣ የወላጅ ጥሪት አሟጦ ማስተማርና የሀገር ሀብት ብክነት ጭምር ግንዛቤ ውስጥ ገብቶ ለዘላለም ከመንገዳቸው ከማሰናከል ይልቅ በቀጣይ የፈተና ጊዜያትና ዓመታት ለሚፈተኑ ተማሪዎች ጭምር ጥብቅ መልዕክት በሚያስተላልፍ መልኩ ተመጣጣኝ ቅጣት በማሳለፍ ድጋሚ ሊፈተኑ የሚችሉበትን እድል እንዲያመቻችላቸው ጠይቋል።

ፌስቡክ https: https://www.facebook.com/TheEthiopianTribune
ቴሌግራም https://t.me/TheEthiopianTribune
ዩቲዩብ https://youtube.com/c/TheEthiopianTribune
ቲዊተር https://twitter.com/EthTribune

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *