በእንተ ነገረ ፓስተር ዮናታን

0
0 0
Read Time:6 Minute, 20 Second

ባለፉት ቀናት ፓስተር ዮናታን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓተ እምነት (ዶግማ)፣ ቀኖና፣ ትውፊትና ታሪክን በሚያንቋሽሽ መልኩ የሰነዘራቸው እኩይ አስተምሕሮዎች መነጋገሪያ መሆናቸውን እየተመለከትን ነው። ለእነዚህ እኩይና ነገር ጫሪ ምልከታዎቹን በኹለት መንገድ መመልከትና መመከት ይቻላል። አንድም ከእምነት አንፃር አንድም ከምድራዊ ሕግጋት አንፃር። በምድራዊው ሕግጋት የአንድ ኃይማኖት (እምነት) መጋቢ ወይም መምህር በማያምንበትና በማይከተው እምነት ሥነ መለኮታዊና ቀኖናዊ አስተምሮዎች በመነሳት ማንቋሸሽ፣ ማዋረድ፣ መዝለፍና መንቀፍ አይችልም። ካንቋሸሼ፣ ከዘለፈና ጠብ አጫሪ ከሆነ አንድም በሕገ መንግሥቱ አንድም በኃይማኖት ተቋማት የጋራ ምክር ቤት አስፈላጊውና ሕጋዊው ርምጃ ይወደሰድበታል። ከእምነት አንፃር ደግሞ ተንቋሻሹና ተዘላፊው የእምነት ተቋም ለተሰነዘሩበት ትችቶችና ስድቦች ከእምነቱ ዶግማዊና ቀኖናዊ አስተምሕሮዎች ግብረ መልስ መስጠትና እንደ ሕጋዊ የእምነት ተቋም ለሚመለከተው የመንግሥት ተቋም አቤት ማለት ይችላል።

የፓስተር ዮናታን ፀረ ተዋሕዶ ዘመቻ ሥነ መለኮትን፣ ነገረ ማርያምንና ትውፊትን መሠረት ያደረገ ሳይሆን ፖለቲካዊ ማናለብኝነትን መርሕ ያደረገ ፖለቲካዊ ትንኮሳ ነው። ምናልባት የሌሎች እምነት መጋቢያን ከእስልምናም ሆነ ከካቶሊክ፣ ከወንጌላውያንም ሆነ ከይሖዋ ምስክሮች ይህን ያህል የጥላቻ ጠብ አጫሪነት በአደባባይ የማይሰነዘረው ፖለቲካዊ ከለላ ስለሌላቸው ብቻ ሳይሆን የዘመናት አብሮ ኖሪነትንና ደም አፋሳሽ ጠብ አጫሪነትን በእምነት ሽፋን በሀገርና በሕዝብ መካከል ላለማውረድ ነው። ፓስተር ዮናታን ከነገረ ኃይማኖት እውቀቱ ይልቅ ለጊዜው ያለው ፖለቲካዊ ከለላ ስለሚበልጥበት እንጂ ይህን ያህል በድፍረት አይወራጭም ነበር። ዛሬ ዛሬ ነው። ነገ ደግሞ ስለራሱ ያውቃልና ዛሬ የሚሰነዘሩ ምናለብኝነቶች የነገና የከነገ ወዲያ ፖለቲካዊ ከለላዎችን ፓስተሩና የፓስተሩ አንጋቾች የተረዱት አይመስልም።

ፖለቲካዊ ከለላ ለማለት የሚያስችለው የሌሎች እምነቶችን አስተምሕሮዎች አይደለም በአደባባይ በመዝለፍ የራሳቸውን እምነት አስተምሕሮዎች ለማራመድ በሞከሩ የኦርቶዶስ ተዋሕዶ ሰባኪያነ ወንጌል፣ የእስልምና ኡስታዞችና የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት መጋቢያን ወሕኒ ሲወርዱና አካላዊ ጥቃት ሲፈፀምባቸው ስለተመለከትን ነው። በዘመነ ኢሕአዴግ መጅሊሳችን ይከበር ያሉ የድምፃችን ይሰማ አባላትና ደጋፊዎች በእስር፣ በዘመነ ደርግ ቤተክርስቲያናችን ትከበር ያሉ ኦርቶዶክሳዊ ሊቃነ ጳጳሳት በእስርና በግፍ ሲገደሉ፣ ዛሬም የሌሎችም እምነቶች መምህራን ተመሳሳይ ድርጊት ሲፈፀምባቸው በታሪክ መነፅር ስለተመለከትን ነው። የሁሉም ዕምነት አባቲችና መምህራን የእስርና ለሞት የበቁት ለኃይማኖታቸው ቀናኢ ስለሆኑ ብቻ ሳይሆን በሰሙነኛው መንግሥት ስላልተወደዱ ነው።

ፓስተር ዮናታን በየአዳራሹ ለሚያካሂዳቸው ጉባኤያት በመንግሥት ከፍተኛ አመራሮችና ተቋማት የመዋዕለ ነዋይና ሌሎች ተዛማች ድጋፎችና ማበረታቻዎች ስለሚደረግለት ራሱን የመንግሥት ንስሐ አባት አድርጎ መቁጠሩ ትክክል ሊመስለው ይችላል። ግን ይሄ አይዞህ ባይነት ሰሙናዊ እንጂ ዘመን ተሻጋሪ ሆኖ አይቆይም። የአንድ እምነት መምህር የራሱን እምነት ከማስከበር በዘለለ የሌሎችንም እምነቶች አስተምሕሮዎች ባያምንባቸውም ባይተገብራቸውም ሊያከብራቸው ግን ግድ ይላል። በዘለፋና በስድብ፣ በሰይፍና በጦር ሰውን ወደ እምነቱ መሳብ ጊዜ ያለፈበት መንገድ ነው። የእምነት ሰው የትናንቱንም የዛሬውንም የነገውንም በተለይም ከሞትና ከተፍፃሜተ ዓለም በኋላ ስለሚኖረውና የሰው ልጆች በዕምነት ተስፋ ስለሚያደርጉት የእግዚአብሔር መንግሥት በማሰብ፣ መለኮታዊውን ብቻ ሳይሆን ዓለምና የሰው ልጆች በሰላምና በመከባበር ለመኖር በጋራ የሚተዳደሩባቸውን ምድራዊ ሕግጋት ሊረዳና ሊያስረዳ ይገባዋል። አንድ የተዋሕዶ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ምዕመን የቤተክርስቲያኗን መሠረታዊ ዶግማና ቀኖናዊ አስተምሕሮዎችን ተምሮ፣ አምኖና ተረድቶ መኖር ግዴታው ነው። ለእምነቱ አጋዥ ግንዛቤ ለማግኘትም አዋልድና ሌሎች ድጋፍ ሰጪ መጻሕፍትን በማንበብ፣ ከመምህራን እግር ስር በመማርና በመጠየቅ ግንዛቤን ማሳደግ፣ በእምነትና በምግባር መጠንከር ጥያቄ የሌለው የምዕመኑ ተግባር ነው። ከዚያ በተረፈ የሌሎችንም እምነቶች አስተምሕሮዎች ለማነፃፀሪያና ለጠቅላላ ግንዛቤ ማንበቡና መረዳቱ ሙሉ ሰው ያደርጋል እንጂ ወንጀል አይሆንም። ወንጀል የሚሆነው የማያምኑበትን ሌሎች ግን የሚከተሉትን እምነት መዝለፍና ለጠብ ማነሳሳት ነው። በግሌ የሌሎች ዕምነቶችን አስተምሕሮች አቅሜ በፈቀደው ለመረዳት መሞከሬ ሰፋ ያለ ግንዛቤን እንጂ ጠላትነትን አልጫረብኝም። ከ 15 ዓመታት በፊት ትውልደ ጋናዊው የፕሮቴስታንት መጋቢ ሜንሣ ኦታቢል
(Mensa Otabil) በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያሰራጨውን Buy the future የተሰኙትን ባለ ኹለት ክፍል የስብከት ሲዲዎቹን አዳምጫለሁ ብዙም ተምሬበታለሁ። ፓስተር ሜንሣ በስብከቱ በተለይም የይስሐቅ መንታ ልጆች የሆኑት ዔሣውና ያዕቆብን መንገድ በስፋት ይተነትናል። ዔሣው የያዕቆብ መንትያ ወንድም ቢሆንም ከእናቱ ማኅፀን ቀድሞ በመውጣቱ ብኩርናን የራሱ አድርጓል። ብኩርና የራሱ የሆኑ ኃይማኖታዊና ዓለማዊ ጠቀሜታዎች ( privileges) አሉት። ዔሣው ጊዜያዊ ብኩርናው የሚሰጠውን ወቅታዊ ጥቅማጥቅም እንጂ ብኩርናውን በማጣቱ ወደፊት የሚያጣቸውንና የሚቀሩበትን ኃይማኖታዊና ዓለማዊ ጥቅማጥቅሞች አርቆ አልተመለከታቸውም ይላል ፓስተር ሜንሣ በስብከቱ። የወደፊቱን መፃዒ ክስተቶችን ከግንዛቤ ያስገባው ታናሹ ያዕቆብ ግን ጊዜያዊ ረሀብና ጊዜያዊ የበታችነትን ወደፊት በሚያገኛቸው በረከቶች ለውጦ ብኩርናን ከታላቅ ወንድሙ በጊዜያዊ የምስር ወጥ ገዛ ይላል። ዔሣው ብኩርናውን ብቻ ሳይሆን ወፈፊት የሰው ልጆች በስሙ ዔሣው ተብለው እንኳን እንዳይጠሩ ስሙን አሳደፈ። ሜንሣ በመቀጠልም ያዕቆብ የምስር ወጥ ለወንድሙ ሽጦ ዮሴፍና ብንያምን ጨምሮ አሥራ ኹለት ልጆችን ወልዶ ለወደፊት የስሙ መጠሪያን የገድሉ መዘከሪያን ሸመተ። በኋለኛው ዘመንም ጌታ ከያዕቆብ ልጆች ተወልዶ ዓለምን ነፃ አወጣ። የያዕቆብ ስምም ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሻገረ ሲታዎስ ይኖራል ይላል። ከእስልምና አስተምሕሮዎች ቁርዐንና ሐዲሳትን በማንበብም ሰፋ ያለ ግንዛቤንና ዕውቀትን እንጂ ጠበኝነትን አልገበየሁም። እንደውም በቤተክርስቲያኔና በመስገድ ጫማ ማውለቅን፣ ጾምን አውጆ መጾምን፣ ዕለትን በሰዓታት ከፍሎ መጸለይና መስገድን፣ ምፅዋትንና ዘካትን፣ ፀበልና ዘምዘምን የሴቶች የራስ መከናነብንና ሂጃብን፣ መፃዒው ዓለምንና ውመል ቂያማን ተገንዝቤባቸዋለሁ።
የፓስተር ሜንሣ ስብከቶችን ከፓስተር ዮናታን ዘለፋዎች ጋር እያነፃፃረ ለሚከታተል ሰው ሜንሣ በተለያዩ ስብቶቹ ስለ መጪው ዓለምና የእግዚአብሔር መንግሥት ዮናታን ሰሙነኛ ፖለቲካን አጋዥ በማድረግ የወደፊት ጥልን ሲጠነስስ መረዳት ይቻላል። ለዚህ ነው በአንድ እምነት ውስጥ የሚገኙ ምዕመናንንና መጋቢዎቻቸውን በጅምላ መውቀጥ ተገቢ አለመሆኑንና ጠብ አጫሪና የሰሙነኛ መንግሥት ብረት ለባሽ የሆኑትን ለመለየትና የሜንሣና ዮናታንን አስተምሕሮዎች በማገናዘብ በምሳሌነት ማቅረቡ አስፈላጊ የሚሆነው።

በአንድ እምነት ዶግማዊና ቀኖናዊ ተአስተምሕሮዎች ለሚነሱ ጥያቄዎች ሕጋዊና ተገቢ ግብረ መልስ የሚሰጡ ተቋማት አሉ። በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዙሪያ ለሚነሱ ቅዱስ ሲኖዶስና በስሩ ያለው የሊቃውንት ጉባኤ፣ በእስልምና ለሚነሱ መጅሊስና የዑለማዎች ምክር ቤት፣ በካቶሊክና በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ዙሪያ ለሚሰነዘሩም ግብረ መላሽ ተቋማዊ አካላት አሏቸው። እነዚህ አካላት ሕጋዊ በመሆናቸው ተአማኒነታቸውና ውክልነታቸው ተቋማዊ በመሆኑ እንጂ ተራው ምዕመንም እንደ ግንዛቤውና የእውቀት መጠኑ ግብረ መልስ ለመስጠት ያንሳል ማለት አይደለም መልሱ ግን ተቋማዊ ውክልና ከሌለው ሌላ አተካሮ እንዳይፈጥር በሚል ነው እንጂ።
ፓስተር ዮናታን በተለይ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ አዋልድ መጻሕፍት ላይ የተጠቀሱ አንቀጾችን በመንቀስ የሰነዘራቸውን ጠብ አጫሪ ዘለፋዎች እንደማኝኛውን የማኅበራዊ ድረ ገጽ ተከታታይ ተመልክቻቸዋለሁ። ምንም ተቋማዊ ውክልና ባይኖረኝም ፓስተሩ በሰነዘራቸው ዘለፋዎች ዙሪያ እንደ አንድ ምዕመን በመረጠው ቋንቋ በአማርኛም ሆነ በእንግሊዝኛ፣ በመረጠው የመገናኛ ብዙኃን እንደ ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ ምዕመን በገባኝና በተረዳሁት ያህል ልወያየው ፈቃደኛ ነኝ። ልከራከረው ያላልኩት በኃይማኖት ውይይት እንጂ ክርክር ስለማያስፈልግ ነው። ለማንኛውም ወንድም ዮናታን ነቢየ እግዚአብሔር ሰሎሞን እንዳለው ኹሉም ጠፊና ኃላፊ በመሆኑ አሰላለፉንና መንገዱን ከሰማያዊው አምላክና ከማይሻር መንግሥቱ ጋር እንጂ ከኃላፊውና ተሻሪው ምድራዊ መንግሥት ጋር እንዳያደርግ፣ በሰው ልጆች ሰላም፣ አብሮነትና መቻቻል ዙሪያ እንዲያተኩር አንጋፋ የቤተ እምነቱ መምህራን ሊመክሩትና ሊገስፁት ይገባል።

በሥነ አዕምሮና (philosophy ) እና ሥነ አመክንዮ ( logics) ሥርዓተ ትምሕርት ለተዛባ ኢምክንያታዊነት የሚዳርጉና የሚሰነዘሩ 20 ፋላሲዎችን ወንድሜ የኔታ Betemariam Abebaw Bekele ዛሬ የቀዳሚት ሰንበት ማለዳ ላይ ዘርዝረዋቸው ተመለከትኩና ከዚህ ጽሑፍ ጋር ላያይዛቸው ወደድኩ።

The 20 Most Common Logical Fallacies

  1. Appeal to ignorance – Thinking a claim is true (or false) because it can’t be proven true (or false).
    _
  2. Ad hominem – Making a personal attack against the person saying the argument, rather than directly addressing the issue.
    _
  3. Strawman fallacy – Misrepresenting or exaggerating another person’s argument to make it easier to attack.
    _
  4. Bandwagon fallacy – Thinking an argument must be true because it’s popular.
    _
  5. Naturalistic fallacy – Believing something is good or beneficial just because it’s natural.
    _
  6. Cherry picking – Only choosing a few examples that support your argument,
    rather than looking at the full picture.
    _
  7. False dilemma – Thinking there are only two possibilities when there may be other alternatives you haven’t considered.
    _
  8. Begging the question – Making an argument that something is true by repeating the same thing in different words.
    _
  9. Appeal to tradition – Believing something is right just because it’s been done around for a really long time.
    _
  10. Appeal to emotions – Trying to persuade someone by manipulating their emotions – such as fear, anger, or ridicule – rather than making a rational case.
    _
  11. Shifting the burden of proof – Thinking instead of proving your claim is true, the other person has to prove it’s false.
    _
  12. Appeal to authority – Believing just because an authority or “expert” believes something than it must be true.
    _
  13. Red herring – When you change the subject to a topic that’s easier to attack.
    _
  14. Slippery slope – Taking an argument to an exaggerated extreme. “If we let A happen, then Z will happen.”
    _
  15. Correlation proves causation – Believing that just because two things happen at the same time, that one must have caused the other.
    _
  16. Anecdotal evidence – Thinking that just because something applies toyou that it must be true for most people.
    _
  17. Equivocation – Using two different meanings of a word to prove your argument.
    _
  18. Non sequitur – Implying a logical connection between two things that doesn’t exist. “It doesn’t follow…”
    _
  19. Ecological fallacy – Making an assumption about a specific person based on general tendencies within a group they belong to.
    _
  20. Fallacy fallacy – Thinking just because a claim follows a logical fallacy that it must be false.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *