በፓርላማው መደመጥ እንጅ ፓርላማውን የማያዳምጥ መንግሥት

0
1 0
Read Time:6 Minute, 49 Second

በፓርላማው መደመጥ እንጅ ፓርላማውን የማያዳምጥ መንግሥት፤

ፓርላማ ማለት በሕዝብ የተወከሉ ወይም የተመረጡ ሰዎች ስለ ሕዝብ እና ሀገር ጉዳይ የሚወያዩበት የመንግሥት ከፍተኛው ሥልጣን እና የሕግ አውጪ አካል ስብሰባ ማለት ነው።እንግሊዘኛ ትርጉሙ በዚህ መልኩ በአጭሩ ያስቀምጠዋል A formal conference for the discussion of public affairs፣ 

ቀደም ያለው የእንግሊዝ ፓርላማ ታሪክ የመሬት ከበርቴዎች፣ቤተ ከርስቲያን እና የሕዝብ ተወካዮች ወይም ተመራጮች በአንድነት የሚመክሩበት ጉባኤ በማለት ይገልጽዋል An Assemblage of the nobility, clergy, and commons called together by the British sovereign as the supreme legislative body. በሚል ጉባኤ ለረጀም ዘመናት ሲሠራበት ቆይቷል፤ በሀገራችን ኢትዮጵያ ይህ አወቃቀር እና አሠራር በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመን በጥሩ ሁኔታ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ነበር። 

በዘመናዊ የእንግሊዝ ሀገር ፓርላማ ከላይ የተጠቀሰውን ጥንታዊ የጉባኤ መሠረታዊ አወቃቀሩን ሳይለቅ በዘመናዊ ፓለቲካ nobility የመሬት ከበርቴው የሚለው አካል ቀርቶ የፓለቲካል ፓርቲ ውክልና ባላቸው major political unit ሰዎች ተተክቶ እየተሠራበት ይገኛል።

በዚህ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ምንስትሩ የመንግሥት ሥራ አስፈጻሚ የበላይ ኃላፊ እንደ መሆኑ መጠን በሥራ አፈጻጸም ይዘቶች ላይ መልስ ሸጭ ፓርላማው ጥያቄ በማቅረብ በጋዜጠኝነት ቃለ ምልልስ በሚመስል ትይንት ብቻ የሚወሰን አደለም።

እርግጥ ጠቅላይ ምንስትሩ አስፈላጊ በሆኑ መጠይቆች እንደ አስፈላጊነታቸው መልስ መስጠት የመንግሥት ተጠሪ ኃላፊነት ያለው አካል ሆኖ ሳለ፤ ዋናው በጣም ትልቁ ተግባር ግን ሀገር አቀፍ ሕዝባዊ ቀንደኛ እና ቀዳሚ ችግሮች ላይ ሙሉ ትኩረት ሰጥቶ በፍጥነት መወያየት እና መወሰን ሲሆን ውሳኔው በሕግ መልክ ተቀርጾለት የአፈጻጸም መመሪያ ወጥቶለት ወዲያውኑ ተግባር ላይ በማዋል ችግሮችን ብዙ ጥፋት እና ውደመት ከማድረሳቸው በፊት በአጭሩ መፍታት ነው። 

ፓርላመንቱ መወሰን እና ሕግ ማውጣት ብቻ ሳይሆን የሕዝብን ድምጽ እየሰማ አፈጻጸሙን እግር በእግር ይከታተላል። ለዚህም ጠቅላይ ምንሥትሩን በግንባር ቀደም በኃላፊነት፣ በተጠያቂነት እና በአስፈጻሚነት ይቆጣጠራል። የፓርላማውን ውሳኔ ለማስፈጸም የማይችል ወይም የሚተላለፍ እና የሚሸራርፍ ከሆነ በሚገባ ተተችቶ እና ተወቅሶ ወዲያውኑ ሥልጣኑን እንዲያስረክብ ይጠየቃል ወይም ይገደዳል። 

በእንግሊዝ ሀገር በዚህ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ሁለት ጠቅላይ ምንሥትር የተለወጡት የፓርላማ ውሳኔ ከሀገር እና ከሕዝብ ጥቅም ተቀዳሚ ተግባር አኳያ የማስፈጸም ደክመት እና ቸልተኝነት ወይም ዋዘኝነት ስለታየባቸው ነው።

በሀገራችን ኢትዮጵያ ይህ ዓይነት አሠራር በፍጹም ገና አልተለመደም። የፓርላመንት ተመራጮች በሙሉ የመንግሥት የበላይ አካል መሆናቸውን አያውቁም።ነገር ግን ተመርጠው የገቡት የጠቅላይ ምንስትሩ አዳማጭ፣አዳናቂ ተመልካች ታዳሚዎች ለመሆን ብቻ ስለሚመስላቸው ክምር እንደ ፈጀ ዝንጀሮ ተጎልተው ቁልጭ ቁልጭ ይላሉ አለዚያም አፍ ከፍቶ ማንቀላፋቱ የተለመደ ነው። 

ጠቅላይ ምንስትሩም አስቀደመው በሚያውቁት እና በተዘጋጁበት ጥያቄ ላይ ለቴለቭዥን ፍጆታ ይቀርባሉ።የፓርላመንቱ አባላት ጠያቂ፤ጠቅላይ ምንስትሩ መልስ ሰጭ ሆነው በጋዜጠኝነት ቃለ ምልልስ መልክ ስብሰባው ምንም ወጤታማ ሳይሆን፤ወቅታዊ ሀገር አቀፍ ችግሮችን ሳይመረምር፤ ውሳኔ ሳይሰጥ፤የውሳኔው ሕግ ሳይወጣ፤ ለአስፈጻሚው የአፈጻጸም መመሪያ ሳይሰጥ ጠቅላይ ምንስትሩ ተደማጭ ፓርላማው አዳማጭ ሆኖ ይጠናቀቃል። 

እርግጥ ነው፤ በመካከል አንዳንድ ሊደርስባቸው የሚችለውን ዛቻና ጡጫ ሁሉ እያውቁ በቁርጠኝነት ፈንቅለው ወጥተው የመንግሥትን የአፈጻጸም ደክመት የሕዝብን በመንግሥት ድጋፍ እጦት የሚደርሰበትን ችግር አፍርጠው የሚያጋልጡ የፓርላማ አባላት ፈጽሞ የሉም ማለት አይቻልም። 

ባለፉት ጊዜያት በተደጋጋሚ በተደረገው ስብሰባ፤ዶክተር አንጋሳ ኢብራሂም የወለጋውን ጭፍጨፋ አስመልክቶ ጊዜ የማይሰጠው ሀገር አቀፍ ችግር መሆኑን በመረዳት፤ የችግሩን ምንጭ በመጠቆም፣ ኃላፊነት ያላቸው ሰዎች ለችግሩ ቀንደኛ ተባባሪ መሆናቸውን በማውሳት፤ችግሩን በምን መንገድ መፍታት እንደሚገባ በማመላከት፣ጠቅላይ ምንስትሩም ሀገሪቱ ዘርፈ ብዙ ሕዝባዊ ከባድ ችግር ያለባት በመሆኑ ጊዜያቸውን በማይመለከታቸው የሥራ መስክ ከማሳለፍ ተቆጥበው ሀገር አቀፍ ሕዝባዊ የሕይዎት አድን ችሮችን በፍጥነት ለመፍታት እንዲታትሩ በግልጽ ጥሪ አድርገዋል።

በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ኦነግን እየረዱ የጎሳ መድሎ እያደረጉ ዜጎች በግፍ እንዲጨፈጨፉ የሚያደርጉ ባለሥልጣናት በተለይም የኦሮሚያ ክልል አንበል ሽመልስ አብዲሳ ከሕዝብ የማይበልጡ መሆናቸውን በስም እየጠቀሱ የያዙትን ሥልጣን እንዲለቁ በተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርበዋል።የኦሮሞ ክልል አስተዳደር በዚህ ግለሰብ አመራር ለዜጎች ሰላማዊ ኖሮ እጅግ በጣም አደገኛ ጠንቅ እየሆነ መምጣቱን በከፍተኛ ደረጃ አስጠንቅቀዋል፤ያዳመጣቸው ግን አልነበረም።

በወለጋ የሚከናወነው የዐማራን ዘር ለይቶ ማጥፋት፣በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ትጥቅና ስንቅ በጀት ተመድቦለት እየተረዳ የሚንቀሳቀሰው ኦነግ ከ390 በላይ የኦሮሚያ ክልል ቀበሌውችን ተቆጣጥሮ ባንኮችን እየዘረፈ፤ ዜጎችን በግፍ አሰቃቂ በሆነ ሆኔታ እየገደለ፤ ሕዝባዊና መንግሥታዊ ተቋማትን እያወደመ ኦነግ እራሱን ችሎ መንግሥት ሆኖ ግብር እስከ ማስከፈል ደርጃ መድረሱን ሲጠቁሙ የሰማቸው አካል የለም። 

ይህን እያዳመጠ የደገፋቸው የፓርላመንት አባል አልተገኘም። ለዐማራው ሕዝብ ተቆርቋሪ ነን የሚሉት ሁሉ እንደዚህ ያሉ ግለሰቦችን በመደገፍ ወደ ተሻለ የንቃተ ኅሊና ለውጥና አስተሳሰብ ማዝገም እና የሚጨፈጨፉትን ዜጎች መታደግ ሲቻል በማይጠቅሙ እና ውክልና በሌላቸው ዘላኖች እንደ ዘመነ ካሤ ላሉ የመንደር ወመኔ የውሸት ፋኖዎች የሽሮ ድንፋታ ሠክሮ እየዋዥቀ፣ያልዘመተበትንና የማይተኩሰውን ጠበንጃ ታጥቆ ላሞች በሚሰማሩበት ጓሳ ፎቶ እየተነሳ እየበተነ፣በባዶ እያቅራራ ለዐማራው መጨፍጨፍ አስተዋጾ አድርጓል።

የወለጋ ጭፍጨፋ በኦነግ አባላት ብቻ የሚፈጸም አደለም።ባለፉት 27 ዓመታት በትግራይ ቃለ አሚኖ በሚል ትምህርት ቤት ውስጥ በልዩ ሁኔታ ተመልምለው የተጣራ ኦሮምኛ እና የተጣራ አማርኛ የሚናገሩ ጥላቻን እና መከፋፈልን የተጋቱ ውሉደ ትግራዩች በኦነጉ መካከል ተሰማርተው መኖራቸውን መዘንጋት አይገባም።

የኦሮሞ ሕዝብ አንዱ ችግሩ በእነሱ ቋንቋ እንደነሱ አለባበስ ለጊዜውም ቢሆን የእነሱን ባህል ተቀብሎ ወደ ጥፋት የሚመራቸውን ሁሉ አንተ ማን ነህ ? ከየት ወዴት? ለምን ?የሚል ጥያቄ አያቀርቡም። ነገር ግን በውስጡ የተሸከመውን ለኦሮሞ ሕዝብ እንደ ሕዝብ የማይበጀውን መርዝ ሳያውቁ በጀምላ ወደ ጥፋት ጎዳና ሚያመራውን ሴረኛ ሁሉ በመንጋ የመከተል ባህሪ ጎልቶ ይታይበታል።ይህም ለወያኔ ዓይነት መሠሪ የጥፋት ተልዕኮ ማቆጥቆጥ እና ሥር መስደደ የተመቸ ለም መሬት ሆኖለታል።

በወለጋ የሚደረገው ጭፍጨፋ በሽመለስ አብዲሳ የሚመራው የክልሉ መንግሥት በትጥቅና ስንቅ በበጀት የተደገፈ ከመሆኑንም በተጨማሪ፤የሕወሀትን ተልዕኮ የሚያስፈጽሙ ኦሮምኛ ተናጋሪ ትግሬዎች በአሰልጣኝነት እና በአመራር ሰጭነት በውስጡ ተበትነው እንዳሉበት መረዳት መቻል ግዴታ ነው።

ጠቅላይ ምንስትሩ ፓርላማው ሊያዳምጣቸው ሳይሆን ሊያዳምጡት ይገባል። በወለጋው ድሃ ገበሬዎችን ጎሰቋላ ሕይዎት የሚገፉትን ሰዎች በማንነታቸው ተለይተው የሚጨፈጨፋትን መታደግና በአጭሩ መቅጨት ሲቻል፤የፓርላማው አባላት የሚናገሩትን የሚሰጡጥን ጠቃሚ ትችት ባለማዳመጥ፤ለሚታየው ሀገር አቅፍ ችግር የሥራ ክፍፍል አድርጎ አፋጣኝ የተጠናከረ ቀጣይነት ያለው እርምጃ አለመውሰድና ያለምድብ ሥራቸው ብዙ ጊዚያትን ማሳለፍ፤ሀገር አቀፍ ሕዝባዊ ጉዳዩችን በቸልታ በማየት ወይም ጊዜ በመስጠት ለጀምላ የሕዝብ እልቂት ምክንያት እንደሆኑ በመንግሥት ሥራ አስፈጻሚ የበላይ ኃላፊነት የመጀመሪያው ተጠያቂ መሆናቸውን መረዳት ይኖርባቸዋል።

የወገኖቻቸን ያለማቋረጥ የሚደረገው ጭፍጨፋም ሆነ ለሰሜኑ ክፍል ሚሊዮኖች ላለቁበት የማይጠቅም ጦርነት ትልቁ ችግር ሕገ መንግሥቱ አለመሻሻል እና የለውጥ ሂደቱ የስም ለውጥ እንጅ የአውቃቀር፣የአደረጃጀት እና የአፈጻጸም፣ከሕወሀታዊ ስነ-ልቡና የጸዳ የተሻለ ግንዛቤ እና ዕወቅት ያልቀሰሙ አመራሮች በአዲስ ሁለገብ ዘመናዊ አስተሳሰብ በአላቸው አለመተካት እና ችግሩ እንዳለ እንደነበረ መቀጠሉ ነው። 

የጠባብ ብሔርተኝነት እና የቋንቋ ክልል ማነቆ፤የመገንጠል ማስገንጠል የውሸት ፌደራሊዝም የተመሠረተው ትግራይ የምትባለውን ትንሽ ክፍለ ሀገር ነፃ ለማውጣት ወይም ቢቻል ለመገንጠል እንደ ነብር ዥንጉርጉር የሆነውን ወርቃማ ሕዝባችን ለመለያየት ሀገራችን ኢትዮጵያን ለማፈርስ ተሠራ እንጅ በፍጹም ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚጠቅም አለመሆኑ በዓለም አቀፍ ምሁራን ተነቅፏል፣በተሞክሮ ውጤታማ ሳይሆን ቀርቶ ወድቋል፣በሕዝብ ተቃውሞ ተጥሏል በየትኛውም የዓለም ክፍል የማይሠራበት ለሰው ልጆች ሰላማዊ ፣ማኀበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሕይዎት ትስሥር ጠንቅ መሆኑ ተመስክሯል።

ጠቅላይ ምንስትሩ ይህን እያዳመጡ የሕግ መሻሻልን፣የአደራጃጀት መዋቅርን በአዲስ መልክ በአዲስ አስተሳሰብ፣በአዲስ ስልት በአዲስ የበሰሉ ለሕዝብ እና ለሀገር ታማኝ ኃላፊነት መውሰድ የሚችሉ እና ተጠያቂነት የሚሰማቸው ሥራ አስፈጻሚዎች የተገራ መንግሥትን ባለማቋቋማቸው የዜጎቻችን በአሠቃቂ ሁኔታ መጨፍጨፍ ከፍተኛውን ሚና የተጫወተ እንደመሆኑ መጠን ሕዝብ በትግል እና በመስዋዕትነት ያመጣውን ለውጥ ሽባ፣ተንፏቃቂ እና ትርጉም አልባ ሆኗል። 

ለውጡን በኃላፊነት ሕዝብ በሚጠይቀው መሠረት ጠንካራ አቋም ወስደው ለሕግ መሻሻል ቅድሚያ ሰጥተው በሕግ እና በሕግ ብቻ ለውጡን ያልመሩት ጠቅላይ ምንስትሩና የእሳቸው ከዳሚዎች በሙሉ፤የመንግሥት ተቀዳሚ ተግባር የሕዝብን ደህንነት የሀገርን ሉዋሏዊነት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ከማስጠበቅ የመሪነት ዐቢይ ተልዕኮ አንጻር በዜጎች ላይ ለሚደርሰው ጭፍጨፋ ግንባር ቀደም ተጠያቂዎች ናቸው።

በግፍ እና በአድማ የተገደሉት የዐማራ ክልል ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት ዶክተር አባቸው መኮንን፤የመጀመሪያ ከፍተኛ ትኩረታቸው በሕግ መሻሻል ላይ ከብረት የጠነከረ አቋም ነበራቸው። ያለው የሕወሀታዊ ሕግ ለሕዝብ ይቅረብ፤ሕዝብ ይጠቅማል ያለው ይቀመጥ፤ሕዝብ ይሻሻል ያለው በሙሉ መሻሻል አለበት የሚል ተቀዳሚ የጠራ፣ የጎመራ፣ በሳል እና ንቁ አቋም ነበራቸው።

የሰውን ልጅ የሚመራው እና የሚገራው፣የሚጠብቀው እና የሚጠቅመው፤ የሚያስተዳድረው እና በእኩልነት በፍትሕ ርዕትሕ የሚዳኘው ከሁሉ በላይ ሕግ መሆኑን አንጥረው የተረዱ በሳል ምሁር በመሆናቸው ሕዝብን እና ሀገርን በሚመጥን መልኩ ከሁሉ በፊት ለሕግ መሻሻል ቅድሚያ ሰጥተው ነበር።ነገር ግን ይኽን ጠንካራ ሐሳብ “ለአንድ ክልል ስንል ሕግ አናሻሽልም” በሚሉ ልምሾ በሆኑ እሩቅ ማሰብ በማይችሉ ጨለምተኛ ደካሞች እና አጃቢዎቻቸው አድማና ሴራ በግፍ አስገደላቸው እንጅ በሕይዎት አላቆያቸውም። 

የዶክተር አንባቸው ሐሳብ ተግባራዊ አለመሆኑ የተነሳ፤”የዐማራን ሕዝብ ጥቅም በፍጹም አሳልፈን አንሰጥም” ብለው የማሉለት የዐማራ ሕዝብ ተቆርቋሪ አጥቶ በግዑዛን እና በዱልዱሞች አሽከላ ተተብትቦ እሳቸው ካለፉ በኋላ አውራ የሌለው ንብ ሆኖ እሳቸውን ተከትሎ በሚሊዮን የሚቆጠር ዐማራ ያለማቋረጥ የለማንም ከልካይ አስቃቂ በሆነ መልኩ ተጨፈጨፈ፤ ተፈናቀለ ይህም የሕዝብ ተወካዮችን እንዲያዳምጡ እንጅ እንዲደመጡ ካለማድረግ የመጣ ዋና ችግርና ጥፋት ነው።

ዶክተር አንባቸው መኮንን “የምንናገረው ነገር እና የምናደርገው እንቅስቃሴ ሁሉ ተጠንቅቀን በማስተዋል መሆን አለበት አለዚያ ግን ሳንዘጋጅ ከዐማራ ክልል ውጪ የሚኖሩትን ዐማራዎች ሕይዎት አስይዘን ስለሆነ፤የተነፈሰ ጎማ እረጅም አይጓዝም” ያሉት፤ሕገ መንግሥቱ ከክልላቸው ውጪ ለሚኖሩ ዜጎች በሚኖሩበት ክልል የሚሰጠው የሕገ መንግሥታዊ ጠንካራ ጥበቃ እና ከለላ አለመኖሩን ጠንቅቀው እና አበጥረው ስለተረዱ ነበር።

ነገር ግን የዐማራው ዘላቂ ሕይዎት ሳይሆን የሥልጣን ስስት ባላቸው አድመኞች እንደ ወንጀለኛ ተቆጥረው በሥራ ገበታቸው ላይ እንደ ተጠመዱ በግፍ አስገደላቸው እንጅ ያዳመጣቸው አካል የተረዳቸው እና የሚመጠናቸው እሩቅ ማሰብ የሚችል በሳል አዕምሮ አልነበረም።ከግል ሥላጣን የሕዝብን ችግር ማስቀደም፣ከሴራ ከሸፍጥ ይልቅ ሕዝባዊ ወገንተኝነትን በማስቀደም፣ከመደመጥ ይልቅ ማዳመጥ ቢቻል ኖሮ ከክልላቸው ውጪ በሌሎች ክልል ለሚኖሩ ዜጎች ቀዳሚ ሕግ ቢሠራና የክልሉ መንግሥት ለሚደርስባቸው ጥቃት በመጀምሪያ ደረጃ የሕግ ተጠያቂ የሚሆንበት መንግድ ቢቀየስ ቀይ መስመር ቢሠመር ኖሮ አሁን የሚደርሰው የወገኖቻችን አሰቃቂ ጭፍጨፋ በአሰቃቂ ሁኔታ በጀምላ ባልተፈጸመ ነበር።

ተጻፈ በ መንገሻ መልኬ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *