የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስታወሻ። ስለ 60 ዎቹ ባለስልጣናት ግድያ ያልተነገሩ እውነታዎች።

0
1 0
Read Time:2 Minute, 33 Second

ጠቅላይ ሚኒስትር ጸሐፊ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተ ወልድ በግፍ ከተገደሉ 50 ዓመታት በኋላ የትነገሩ

የአዲስ አበባ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን ደብር አለቃ (ቄስ) ልጅ ናቸው። የተወለዱት የዛሬ 110 ዓመት በ1904 ዓ.ም. ነበር። የቄስ ትምህርታቸውን በራጉኤል ቤተ ክርስቲያን፣ ከዚያ ደግሞ አፄ ምኒልክ ትምህርት ቤት ለሁለት ወይም ለሦስት ዓመት ተምረው ነበር። ቀጥሎ ወደ ግብፅ ሄደው ለስድስት ዓመታት ዘመናዊ ትምህርት ተምረው ወደ ትልቁ የፈረንሣይ ሶቦን ዩንቨርስቲ (Sorbonne University) ገቡ። ሶቦን ዩኒቨርሲቲ ትልቅ ስም ያለውና ለብዙ መቶ ዓመት የቆየ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲ ነው። በስድስት ዓመታት ቆይታቸው የሕግ ዲግሪ ሲያገኙ፣ በማኅበራዊ ሕግ ላይ ደግሞ ዶክትሬት፣ በተጨማሪም በኢኮኖሚና በፋይናንስ ዲግሪና በፖለቲካል ሳይንስ ሰርቲፊኬት አግኝተዋል። ስናሰላው እስከ ዶክትሬት ትምህርትን የጨረሱት በ14 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ነበር። በአሁኑ ዘመን ቢያንስ 20 ዓመታት ይፈጃል።

ይህ የቀድሞ ኢትዮጵያውያን ምን ያህል የዕውቀት ጥማት እንዳላቸው፣ ዕድሉን ካገኙ ያለውን ሁሉ ነገር በአዕምሯቸው አጭቀው ወደ አገራቸው ለማምጣት ይጥሩ እንደነበረ ያሳያል።

ዛሬ ትምህርት “አንቱ” መባያ ወይም ጥሩ ብር ማግኛ እየሆነ ስለመጣ የዕውቀት ጥማቱ እንደ ጥንቱ አይደለም። የዶክትሬት ዲግሪ ቢኖራቸውም ዶ/ር ብለው ራሳቸውን አልጠሩም። አሁንም በሙያቸው ጸሐፊ ትዕዛዝ ተብለው ነው የሚጠሩት።

ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ የአገር አገልግሎት ገና ግብፅ ውስጥ ተማሪ ቤት እያሉ ነው የጀመሩት። ግብፅ አስተምራለሁ ብላ ያመጣቻቸው 60 የኢትዮጵያ ተማሪዎች ተቸግረው፣ ተርበውና ተራቁተው ሲያገኟቸው የኢትዮጵያዊያንን መብት ለማስከበር ከግብፅ የኮፕቲክ ፓትርያርክና ባለሥልጣናት ዘንድ ቀርበው በማመልከትና በመከራከር የልጆቹን ችግር ለጊዜው በማቃለል ችለው ነበር። ከዚያም ችግሩ ሲብስ ከአልጋ ወራሽ ራስ ተፈሪ መኮንን ጋር በመጻጻፍ ወጣቶቹ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አድርገው ነበር።

ፈረንሣይ ተማሪም እያሉ አገልግሎታቸው ቀጠለ። ሞሰሎኒ እ.ኤ.አ. በ1922 ሥልጣን ላይ ወጣ። ሞሶሎኒ ሥልጣን በያዘ በዓመቱ ኢትዮጵያ ለሊግ ኦፍ ኔሽን ለመመዝገብ የጠየቀችው ማመልከቻ ሲቀርብ ተቃዋሚ ጣሊያን ሆነች።

“ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ጅግራ ይሏታል” እንደሚባለው፣ ጣሊያኖች ኢትዮጵያ የሊግ ኦፍ ኔሽን አባል እንዳትሆን በሩን ዘግተው ያለ ታዛቢና ተሟጋች ቅኝ ለማድረግ ነበር ያቀዱት፡፡ የያኔው አልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን “ጣሊያን ምን አስባ ነው ነፃዋ አገር የዓለም አቀፉ ማኅበር እንዳትሆን ሞሶሎኒ እንቅፋት የሆነው?›› ሲሉ ጠየቁ። ሞሶሎኒ ተደናግጦ ተቃውሞውን አነሳ።

በዚህም የመጀመርያዋ የጥቁር ሕዝብ አገር ኢትዮጵያ በሊግ ኦፍ ኔሽን ወንበር አገኘች። በዚያን ዘመን የዓረብ ነፃ አገር አልነበረም፣ ህንድና እስያም ከጃፓን በስተቀር ነፃ አገር አልነበሩም፡፡ ከካሪቢያም ነፃ አገር አልነበረም። ዛሬ ወደ 193 አገሮች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ናቸው። ያኔ በ1923 ዓ.ም. ኢትዮጵያ በግድ አባል ልሁን ስትል 42 የነጭ አገሮች ብቻ ነበሩ። ኢትዮጵያ ብቻ ናት እንደ ጥቁር ፈርጥ በነጩ ዓለም ከመሀል የተቀመጠችው።

የሚገርመው ግን ወጣት አክሊሉ ሀብተ ወልድ ከ18 ዓመታቸው ጀምረው ነው ወደ ጄኔቭ እየሄዱ ኢትዮጵያን ወክለው መሟገት የጀመሩት።

ከዚያ በሊግ ኦፍ ኔሽን ብቻ ሳይሆን የጣሊያንን ፕሮፓጋንዳ መመከት በእሳቸው ላይ ወደቀ። ጣሊያን ያልሠለጠኑ አረመኔ ሕዝብ (Savage) ናቸው፣ እኛ የምንሄደው ልናሠለጥናቸው ነው ሲል፣ ከጣሊያን ያላነስን የሠለጠንን ሕዝብ ነን፣ የራሳችን ሥልጣኔ፣ ጽሑፍና እምነት ያለን ነን እያሉ ይጽፋሉ። ጨካኞች ናቸው ሰው ያቃጥላሉ፣ ይሰልባሉ፣ ባርያ ያደርጋሉ ሲል በመረጃ እየደረደሩ መታገልና መመከት በትከሻቸው ላይ ወደቀ።

ዓለም ግን ጥቁርን የምታዳምጥበት ጆሮዋ አልተከፈተም ነበርና የተፈራው አልቀረም፡፡ ኢትዮጵያ በ1928 ዓ.ም. ተወረረች። በዚህ ጊዜ የአክሊሉ ሀብተ ወልድ ለኢትዮጵያ መታገል ሕይወታቸው ሆነ።

የጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተ ወልድ ትውስታ አጭር ቢሆንም፣ የሚያሳዝነው ዕድል ተሰጥቷቸው ታሪካቸውን ለመጻፍ ሳይችሉ በእነ ኮሎኔል መንግሥቱ፣ በእነ ኮሎኔል ፍስሐ ደስታ፣ በእነ ሻለቃ ፍቅረ ማርያም ወግደረስ፣ በመንጋ ፖለቲካ ስም እየጠሩ ‹እንትና ይገደል› እያሉ ድምፅ ሰጥተው እንደ እነ አክሊሉ ያሉትን ታላላቅ አርበኞች ረሸኑ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *