በተራዘመ ድርቅ በቦረና ዞን በርካታ የቤት እንስሳት አልቀው የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ነዋሪዎችም እሞት አፋፍ ደርሰዋል።

0
0 0
Read Time:59 Second

የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ነዋሪዎች ከድርቁ ጋር በተያያዘ መሞት ጀምረዋል ” – የተልተሌ አርሶ አደር

” በርሃብ ምክንያት የሞተ ሰው የለም ” – ቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ

በቦረና ዞን በድርቁ ምክንያት ሰዎች በምግብ አጦት ሰውነታቸው እየተጎዳ ቢሆን ” በርሃብ ምክንያት የሞተ ሰው የለም ይህንን ቦታው ድረስ ተገኝተን አረጋግጠናል ” ሲል ቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ ገለፀ።

ቡሳ ጎኖፋ “የሰዎች ህይወት አላለፈም” ሲል ቃሉ የሰጠው ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ነው።

የቡሳ ጎኖፋ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ማሊቻ ሎጂ ፤ ” በድርቅ ወደ ተጎዳው ቦረና ዞን በማምራት ያለውን ሁኔታ ተመልክቻለሁ ” ያሉ ሲሆን ” በድርቁ ምክንያት ሰዎች በምግብ እጥረት ሰውነታቸን እንደተጎዳ ታዝቢያለሁ ” ብለዋል።

” ነገር ግን በረሃብ ምክንያት የሞተ ሰው እንደሌለ ቦታው ድረስ ተገኝቼ በአካባቢው ከሚገኙ ሰዎች አረጋግጫለሁ ” ሲሉ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያው ተናግረዋል።

ከሰሞኑን ቦረና ዞን በተራዘመ ድርቅ በርካታ የቤት እንስሳት አልቀው የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ነዋሪዎችም ከድርቁ ጋር በተያያዘ መሞት መጀመራቸውን ነዋሪዎችን ለዶቼ ቨለ ሬድዮ መናገራቸው ይታወሴ።

ለሬድዮ ጣቢያው ቃላቸውን ሰጥተው የነበረው በቦረና ዞን ተልተሌ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አርብቶ አደር ማሊቻ ሞሌ ከድርቁ ጋር በተያያዘ ሰዎች እየሞቱ ስለመሆኑ እንዲህ ሲሉ ነበር የተናገሩት ፦

” … በድርቁ ሰው የከፋ ችግር ውስጥ ነው ያለው ። ያላቸው ከብቶች በግ እና ፍየል እንኳ ሳይቀር አልቀዋል። ጠብ ያለ ዝናብ ባለመኖሩ የሚወጣ እህል የለም።

የሚሸጥ ከብት በሙሉ በድርቁ አልቀዋል። አሁን ሰው በችግሩ በሕይወት እስከማለፍ ደርሷል። የሚቀመስ በመጥፋቱ በዚሁ ዓመት ብቻ በዚህች ቀበሌያችን አራት ሰው የሚደርስ ተጎሳቅለው አልፈዋል

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *