በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ከ3 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ይፈልጋሉ

0
0 0
Read Time:37 Second

በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ 3 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ይፈልጋሉ።

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ደበበ ዘውዴ እንደገለጹት፥ በሶማሌ ክልል ከሚገኙ 11 ዞኖች ውስጥ በዘጠኙ ላይ የተከሰተው ድርቅ በሰዎች እና እንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡

አሁን ላይም ድርቁን ተከትሎ በሶማሌ ክልሉ አዲሱን ጥናት ሳይጨምር ከ3 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ዜጎች አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ነው ያሉት፡፡

በክልሉ እየተካሄደ ያለው አዲስ ጥናት ሲጠናቀቅ የተረጂዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል አስገንዝበዋል፡፡

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በክልሉ በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም አቶ ደበበ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

የተረጂዎች ቁጥር ከፍተኛ እና ከቀን ወደ ቀን እያሻቀበ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞም ተጨማሪ አስቸኳይ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ስለሆነም መንግስታዊ ተቋማት፣ የግል ድርጅቶች፣ አጋር አካላት፣ ታዋቂ ሰዎች እና ዳያስፖራዎች በክልሉ በድርቅ ለተጎዱ  ዜጎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *