የፖለቲካ ሥልጣን ቢኖረኝ

0
0 0
Read Time:1 Minute, 3 Second


(በቀለ ገሠሠ)

በህይወቴ የፖለቲካ ሥልጣን ተመኝቼ አላውቅም። ፍላጎቴ እግዚአብሔር ይመስገን ባገኘሁት ከፍተኛ ትምህርትና ዓለማቀፍ የሥራ ልምዴ ወገኔን ማገልገል ብቻ ነበር።

ዛሬ ግን በተለይ በአማራው ወገኖቻችን ላይ ያነጣጠረው የጅምላ ጭፍጨፋና መፈናቀል ስመለከት አንጀቴ ያራል፣ ልቤ ይቆስላል፣ በህይወት መሰንበቴን ያስጠላኛል። አማራ የትግሬ፣ የኦሮሞ፣ ወዘተ ህዝብ ጠላት ሆኖ አያውቅም። ያገኘውን ልክ ጥቅም አልነበረም። እንደ ሁሉም ዜጋ ጥሮ ግሮ ህይወትን አቸንፎ የኖረ ደግ ህዝብ ነው። ስለዚህ በምናብም ሆነ በተግባር ጭቁን ህዝባችንን ለመታደግና ውድ አገራችንን ከጥፋት ለማዳን ሥልጣን ቢኖረን የምንፈጽማቸው ተግባራት የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፣

ሀ) ሁሉ አቀፍ የሽግግር መንግሥት አናቋቁማለን፣ ዘረኝነትን፣ የወገን ጭፍጨፋ፣ መፈናቀልና ሰቆቃ እናቆማለን፣ በዘር ማጥፋት ወንጀል የሚሳተፉት በነፃ ፍርድ ቤት እንዲጠየቁ እናመቻቻለን። በመቀጠል የተለያዩ ፓርቲዎች ነፃና ፍትሐዊ በሆነ መልክ ተወዳድረው መንግሥት እንዲመሠርቱ እናመቻቻለን፣

ለ) ሕገመንግሥቱ እንዲለወጥ አናደርጋለን፣

ሐ) የተረጩት የውሸት ትርክቶች እንዲታረሙ አናደርጋለን፣

መ) ዕርቀ ሰላም እናወርዳለን፣ የማንም ዜጋ ህይወት በግፍ እንዳይጥፋ እንከላከላለን፣

ሠ) የተፈናቀሉትን ወገኖች መልሰን አነናቋቁማለን፣

ረ) ግፍ ለደረሰባቸው ወገኖች ካሣ እንከፍላለን፣

ሰ) ለገበሬው ሰላምና ድጋፍ አናመቻቻለን፣

ሸ) ነጋዴው በነፃ ተዟዙሮ መነገድ መቻሉን አናረጋግጣለን፣

ቀ) ወጣቶች ጥሩ ትምህርት እንዲያገኙ እናመቻቻለን፣ እንደግፋለን፣

በ) የሀገር ኢኮኖሚ እንዲያድግ የሚገባውን ሁሉ ድጋፍ እንሰጣለን፣ ለምሣሌ ጠፍ መሬቶች ማልማት፣ ወንዞቻችንን መገደብ፣ የመስኖ እርሻዎች ማስፋፋት ፣ የአካባቢ አየር ብክለት መከላከል፣ ወዘተ ።

ውድ ወገኖች፣
እላይ እንደጠቀስኩት ጥረቴ የመንግሥት ስልጣን ፍላጎት አይደለም፣ ሆኖም አያውቅም። ዋናው ምኞቴን ለመግለጽ ስለሆነ ተረድታችሁ ለዘላቂ ሰላምና ዕድገት የሚቻላችሁን ጥረት እንድታደርጉ በትህትና እጠይቃለሁ፣
ቸሩ አምላካችን ይጨመርበት።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *