“በሰው ደም የሚጫወቱ አረመኔ መሆነወትን ተረድቻለሁ!!” የቱለማው ጀግና ታዬ ደንዳ።

0
0 0
Read Time:1 Minute, 42 Second

አለባቸው ደሰአለኝ

ሰላም ሚኒስትሩ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ትእዛዝ ከስልጣናቸው ተባረሩ:

የሰሜን ሸዋ የኩዩ ወረዳ እና አካባቢ ሕዝብን በመወከል የኦሮሚያ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ታዬ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሚመራው ገዢው የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ናቸው።

ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሶስት መስመር ከሥልጣናቸው ተሰናበተዋል ::


በአገሪቱ ያለው ጦርነት እንዲቆም ጥሪ በማቅረባቸው እንጂ ሌላ ምክንያት እንደሌላቸው የሚናገሩት
የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ የነበሩት አቶ ታዬ ለቢቢሲ ጋዜጠኛ በዝርዝር ገልፅውለታል : : በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተፈረመ ደብዳቤ ከሥልጣን መነሳታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ይፋ ካደረጉ በኋላ ነው።

በፌስ ቡክ ገፃቸው ላይ
“ስለእርቅ ስለተናገርኩ ጦርነት ይቁም ስላልኩ “በጦርነቱ ጊዜ ጦርነቱን ስደግፍ፣ ሲያበረታቱኝ ነበር። ሕዝቡ ይታረቅ ስንል ነው ያመማቸው። ጠርተውም አላናገሩኝም። በአካል አልተገናኘንም” ሲሉ ቅርትቸውን አሰምተዋል ።

አቶ ታዬ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተጻፈላቸውን የስንበት ደብዳቤ አያይዘው እንዳሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩን አምነው እንደተከተሏቸው እና በቃላቸው አለመገኘታቸውን ጠንከር ያሉ ቃላትን ተጠቅመው ወቅሰዋቸዋል: :

ስንብታቸውን በተመለከተ በፌስቡክ ላይ ያሰፈሩትን ጠንካራ ትችት. እንዲህ ይላል “ይሄ እውነት ነው። ለሰው አያዝኑም። የሰው ልጅ ሞቶ አውሬ እየበላው ስለ ፓርክ ያወራሉ። ሰው የሚበላው አጥቶ እየሞተ በብዙ ገንዘብ ቤተ መንግሥት ያስገነባሉ” በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩን አብጠልጥለዋቸዋል ።


አያይዘውም
“የተናገሩትንና የፃፉትን የመደመር ዕሳቤ አምኜ ተከተልኩዎት። አሁን ግን በተናገሩት የማይኖሩ ብቻ ሳይሆን በሰው ደም የሚጫወቱ አረመኔ መሆነወትን ተረድቻለሁ” ሲሉ በገጻቸው ላይ አስፍረዋል።
በሕግ ሊያስጠይቃቸው የሚችል ነገር ይኖር እንደሆነ በቢቢሲ. ለጠይቅቸው ጥያቄ ሲመልሱ ” ዝግጁ መሆናቸውን ጠቅሰው ነገር ግን ይህ የሚሆንበት ዕድል እንደሌለ ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል።

“ይህ [በሕግ መጠየቅ] ምን ችግር አለው ታዲያ። ነገር ግን ሕግ የታለና በሕግ ይጠይቁኛል። ከጠየቁኝ ደግሞ ዝግጁ ነኝ።” በማለት ሐሳባቸውን ገልፀዋል::

የመንግሥት እና የገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ባለሥልጣን ሆነው በጠንካራ ትችታቸው የሚታወቁት አቶ ታዬ ሰሞኑን በተከታታይ የሰነዘሯቸው አስተያያቶች ለስንብታቸው ምክንያት ይሆናል ብለው አያምኑም።

“ከዚህ ጋር የሚገናኝ አይመስለኝም። ከፓርቲያችን መርሆች ውስጥ ነጻነት አንዱ ነው። ከዚህ መርህ በተቃራኒ መቆም ተገቢ አይደለም። እኔ ስናገር የነበረው ይህንን መርህ መሠረት በማድረግ ነው” ብለዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፊርማ ለአቶ ታዬ በተጻፈው ባለሦስት መስመር የስንብት ደብዳቤ ላይ የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው ላበረከቱት አስተዋጽኦ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመስግነው ከዛሬ ታኅሣሥ 1/2016 ዓ. ም. ጀምሮ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን አመልክቷል።

ከመስከረም 2014 ዓ. ም. ጀምሮ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ የነበሩት አቶ ታዬ የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ) አባል ሲሆኑ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እና በመገናኛ ብዙኃን ላይ በሚሰጡት አስተያየት የፌደራሉን መንግሥት እና የኦሮሚያ ክልልን በይፋ በመተቸት ይታወቃሉ ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *