ለእውነተኛው የየአማራ ፋኖ ታጋዮች የቀረበ ጥብቅና አስቸኳይ ግልፅ ጥሪ፦ የባርነት ካምፑን ሰብራችሁ ወጥታችሁ የሕዝባችሁን ክብርና ነፃነት አስከብሩ

0
img_6474
0 0
Read Time:3 Minute, 31 Second

አስተያየት · ግልፅ ደብዳቤ

ለእውነተኛው የአማራ ፋኖ ታጋዮች የቀረበ ጥብቅና አስቸኳይ ግልፅ ጥሪ፦ የባርነት ካምፑን ሰብራችሁ ወጥታችሁ የሕዝባችሁን ክብርና ነፃነት አስከብሩ!

ዶ/ር ሶስና ታደሰ ቀደም ሲል በ«ፅምዶ» ጥምረት ዙሪያ ካቀረቡት ትንታኔ በመቀጠል፣ በጎንደርና በመላው አማራ ለሚገኙ የፋኖ ታጋዮች ከአፋብን አመራርና ከፅምዶ አሰላለፍ ራሳቸውን እንዲለዩ ግልፅ ጥሪ ያቀርባሉ።

ዶ/ር ሶስና ታደሰ · መስከረም 2019 ዓ.ም.

የአዘጋጁ ማስታወሻ፦ ይህ ግልፅ ደብዳቤ በአስተያየት ዓምድ ስር የቀረበ ነው። በደብዳቤው የተገለጹት አቋሞችና የቀረቡት መረጃዎች ሙሉ ኃላፊነት የጸሐፊዋ ብቻ ሲሆን የኢትዮጵያ ትሪቡንን አቋም አይወክሉም። በደብዳቤው የተጠቀሱ ወገኖች ምላሽ ለመስጠት ቢፈልጉ ዓምዳችን ክፍት ነው።

ከ፦ የታሪካዊና የህልውና ትግሉ ተቆርቋሪ (ዶ/ር ሶስና ታደሰ)

ለ፦ በጎንደርና በመላው አማራ ምድር መሬት ላይ ላላችሁ እውነተኛ የፋኖ አበጋዞችና ታጋዮች

የተከበራችሁ የአማራ የሕልውናችን አጥርና በተለይም የጎንደር ወታደራዊ አቅም ማዕከል የሆናችሁ ታጋዮች፤

ከዚህ በፊት የ«ፅምዶ»ን አደገኛነት በተለይም «ፅምዶ ፋኖን ለሕወሓት ተራ እግረኛ ቅጥረኛ ወታደር ያደርገዋል፤ ከዚህ አሰላለፍ ወጥታችሁ የድርጅት ነፃነታችሁን አስከብሩ፤ ወይም ይህንን ማድረግ ካልቻላችሁ በአስቸኳይ ከዚህ አፋብን ከሚባል መዋቅር ራሳችሁን በማግለል በራሳችሁ ዕዝና ነፃ ድርጅት ቁሙና መልሳችሁ ያጣችሁትን የሕዝብ ተቀባይነት አግኙ» የሚል ተደጋጋሚ ጥሪ ማድረጋችን ይታወቃል።

ይሁን እንጂ እናንተ አንድም እርምጃ ሳትወስዱ፦

መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም. የድርጅታችሁ መሪ ተብዬው ዘመነ ካሴ መቀሌ ላይ ሆኖ የፅምዶን ፀረ-አማራ የትብብር ኃይሎች መግለጫ ሲያነብ በትግራይ ቴሌቪዥን ከእናንተ እኩል ተመልክተናል!

መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ.ም. የድርጅታችሁ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ሄኖክ ኪዳኔ በሰጠው የሚዲያ ማብራሪያ፣ በራያ ዘብና በተከዜ ዘብ ዙሪያ በተነሳለት ጥያቄ ላይ፦ «የራያ ዘብም ሆነ የወልቃይት ዘብ ከሥርዓቱ ጋር ትጥቅ ይፈታል፤ የሚያስጠይቀው ወንጀል ካለ በወንጀል ይጠየቃል» ብሎ የማንነታቸውን፣ የርስታቸውንና የሕልውናቸውን አስጠባቂ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆችን ትጥቅ አስፈትቶ በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ የተዘጋጁ መሆኑን በግልጽ ተናግሯል!

የዚህ ንግግርና የፖለቲካ አቅጣጫ ዋና ትርጉም

የሄኖክ ኪዳኔ ንግግር ዋና ዓላማ በግልጽ እንደወረደ ሲተረጎም፦ ሕወሓት በአማራ ሕዝብ ላይ በተለይም በሸዋ፣ በጎንደር (ወልቃይት/ጠገዴ/ጠለምት) እና በቤተ-አማራ ወሎ (ራያ) ሕዝብ ላይ የፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለማጠብና ከወንጀሉ ነፃ አድርጎ፣ የወልቃይትና የራያን አማራ ሕዝብ ትጥቅ አስፈትቶ ለጠላት አሳልፎ ለመስጠት የተዘጋጀ የፖለቲካ ወጥመድ ነው! ይህም በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ የተሰጠበት አሁን ግን በይፋ የተገለጠ አስነዋሪ ሴራ መሆኑን መላው ሕዝብ ተገንዝቦታል።

ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያ የይስሙላ የወሰን ውዝግብ ሳይሆኑ የአማራ ሕዝብ፣ የአማራ ህልውናና የጎንደርና የወሎ ቤተ-አማራ የፖለቲካና የወታደራዊ አቅም ማዕከላዊ ደም ስሮች ናቸው!

ጎንደር የታሪክ፣ የጀግንነትና የነፃነት አምባ እንጂ የጠላት ማስፈጸሚያና የባርነት ካምፕ ሆና አታውቅም!

ጎንደር የታሪክ፣ የጀግንነትና የነፃነት አምባ እንጂ የጠላት ማስፈጸሚያና የባርነት ካምፕ ሆና አታውቅም! ታዲያ እናንተ የዚህ ታሪካዊ ውርደትና የወልቃይት/ራያ ርስት አሳልፎ ለመስጠት የሴራ እቅድ አካል ሆናችሁ በዝምታ የምትቀጥሉት እስከመቼ ነው?

የሚቆረቆርላችሁን ማህበረሰብ ምክር ጆሮ ዳባ ልበስ ብላችሁ እንዳሳለፋችሁ ይታወቃል። ቢያንስ ግን አሁን የራሳችሁ የምትሏቸው መሪዎቻችሁ ከእናንተ ዓላማና የትግል ግብ ውጭ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን በተግባር እያያችሁ ነው! የሊሐቃኑን ምክር ለመስማት ቢከብዳችሁ እንኳ ያላችሁበትን ሁኔታ አይቶ የሚንቃችሁ የጠላት ስብስብ እንዳለ ካወቃችሁ ሊያነቃችሁ ይገባል።

ትብብር በሚል የዳቦ ስም የፅምዶ የባርነት ካምፕ ውስጥ ተደፍቃችሁ እስከመቼ ተራ ቅጥረኛ የሕወሓት ወታደር ሆናችሁ ታደፍጣላችሁ?

እስከመቼ ከወጣችሁበት የትግል ዓላማ፣ ከጎንደር የጀግንነት ሌጋሲና ከራያና ከወልቃይት የአማራነት ጥያቄ ጋር ተጣልታችሁ ታዘግማላችሁ?

እስከመቼ ደጀን ከሆናችሁ ማህበረሰብ ጋር ተራርቃችሁ ትዘልቃላችሁ?

ይህ አፋብን የሚባል ፀረ-አማራ ስብስብ ለተከዜ ዘብ የማይራራና ትጥቅ አስፈታለሁ እያለ ሲፎክር ማን ማለት እንደሆነ ልብ ማለት ይገባል፣ እናንተም በተከዜ ዘብ መነጸር የምትታዩ የአማራ ዘቦች ናችሁ! ስለዚህ እንደ ሄኖክ ኪዳኔ አገላለጽ በፀረ-ሕወሓት ትግል ላይ በመሳተፋችሁ ትጥቅ ትፈታላችሁ፣ ብሎም የወንጀል ተጠያቂ ትሆናላችሁ ማለት ነው! ምክንያቱም አብዛኞቻችሁ የምትታወቁት ሕዝባችሁን ለመታደግ በፀረ-ፋሽስት ሕወሓት ትግል ላይ በመሰለፋችሁ ነው። ስለሆነም የአፋብን የትግል መስመር ፀረ-አማራ ብሎም የሕወሓት የሴራ ወጥመድ አስፈጻሚ መሆኑን በግልጽ ካያችሁ፣ ያላችሁበት የትግል ማዕቀፍ የጠላቶቻችሁ ወጥመድ መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳያል።

ጥሪያችን

እውነታውን ተቀበሉ! የከፈላችሁትን ከባድ መስዕዋትና የመጣችሁበትን የትግል መስመር አስቡ! የወጣችሁለትን ታሪካዊ የትግል መስመር መሳቱን በድጋሚ መርምሩ፣ ከሐሰት ፕሮፕጋንዳ ራሳችሁን በማራቅ በዙሪያችሁ ያለውን የሕዝብ ትርታ አድምጡ! ተከዜ ዘብ በሕወሓት የሚመጣውን አውዳሚ ጦርነት ገድቦ የያዘ ለአማራ ሕዝብ ብሎም ለናንተ ቁጥር አንድ ጠባቂያችሁ ነው! ስለሆነም ከደጀኑና ከጠባቂው ማህበረሰባችሁ ጋር ተጣልታችሁ የጠላቶቻችሁን የፖለቲካ ቁማር መጫወቻ ካርድ ከመሆን በጊዜ እንድትቆጠቡ እና በጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ሐምሌ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ያወጣችሁትን መግለጫ መሠረት በማድረግ ግልጽ አማራዊ አቋማችሁን እንድታስፈጽሙ በጥብቅ እናሳስባለን! ከፋሽስት ወራሪ ሕወሓት ነፃ የሆኑ የአማራ ርስቶች በአማራነት በደምና በአጥንት የተገነባ የነፃነት ምድሮች እንጂ በፅምዶ ደላሎች ስምምነት የሚደራደሩበት የንግድ እቃ አይደሉም!

የአማራ ሕልውና፣ የፍትሕና የርስት ጥያቄ በፀረ-አማራና በፀረ-ኢትዮጵያ ደላሎች ቁማር አይሸጥም! ነፃነትን የሚያፃና ታጋይ ሁኑ!!

ድል ለአማራ ሕዝብ!

ፍትሕ፣ እኩልነትና ነፃነት ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

ዶ/ር ሶስና ታደሰ


የአዘጋጁ ማስታወሻ፦ ይህ ግልፅ ደብዳቤ በአስተያየት ዓምድ ስር የቀረበ ነው። በደብዳቤው የተገለጹት አቋሞችና የቀረቡት መረጃዎች ሙሉ ኃላፊነት የጸሐፊዋ ብቻ ሲሆን የኢትዮጵያ ትሪቡንን አቋም አይወክሉም። በደብዳቤው የተጠቀሱ ወገኖች ምላሽ ለመስጠት ቢፈልጉ ዓምዳችን ክፍት ነው።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *