0 0
Read Time:1 Minute, 36 Second



ደጉ የሰላሙ መሪ ንጉሳችን ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ሆይ የእንባ እርግማንዎን እባክዎ በዚህ አዲስ አመት ያንሱልን ?

43 አመት ካለምንም ምክንያት እርስ በርስ ተባላን ምድሪቱ የመጣ መሪ ቢመጣ አልረጋ አልገዛ ብላ አስቸገረች ህዝቡም እምነት ፍቅር ስምምነት አጣ ::
ንጉስ ሆይ ይማሩን ይቅርም ይበሉን

አመቱ የሰላም የጤና የፍቅር የብልፅግና እንዲሆንልን እባክዎ በእንባ የታጀበው እርግማንዎትን ከኛ ከህዝብዎ ላይ ያንሱልን በቃችሁ ልጆቸ ብለው ከልብ ይማሩን ::

እኛም ወጥተን እንግባበት አሽተን እንቃም ወልደን እንሳም ሰርተን እንግባ ዘመድ ከወገን በፍቅር በመተሳሰብ እንደ ድሮው እንደ ጥንቱ እንኑርበት ::
ግርማዊ ሆይ እንሆ አባቴ ይቅር ይበሉን :

በትራስ አፍነን ከሆን የገደልን እንሆ በተምች በሽታ መድኃኔት ባልተገኘለት አፍ እና አፍንጫችን አፍነን እኛም መተንፈሻ አተናል :: ቆሎ ባጣ ሆዳችን ለእግር ጫማ በለለው ኑሮአችን በቀን አስር ግዜ እጃችን ከውሃ ጋር ሲጫወት ይውላል :: ንጉስ ሆይ ይማሩን !

በግፍ ብጹእ ወቅዱስ ጳትሪያርካችንን እና ባለ ሥልጣኖችዎን ገለን ከሆን እኛም እርስ በእርስ ቀይ ሽብር ነጭ ሽብር እያልን የሞት ብልት እያወጣን እርስ በርስ ተላልቀናል ግርማዊ ሆይ በዚህም አላቆምንም በዚህ በሰለጠነው ዘመንም በምንጫ እየተፋለጥን ተዘቅዝቀን አየተሰቀልን በመቶ አስር አመት ታሪክ እየተናቆርን አንተ ትብስ አንች ቀርቶ የታባህ የታባሽ ነግሶ : ፍርድ እርትእ ጠፍቶብን ፍርድ ቤት ሲፈታ ፖሊስ እያሰረ እንሆ 43 አመት አስቆጠርን
እባክዎ ግርማዊ ሆይ በነበርዎት የድሮ የህዝብዎ ፍቅር ሲሉ ዘንድሮን ይማሩን !

አዲስ አመት ወንዱ ሴቱ ትልቁ ትንሹ ወጣት አዛውንቱ እንደየ እምነቱ ነጭ ለብሰን ደምቀን አምረን አሮጌ አመት አልፎ አዲስ አመት ሲተካ እግዚአብሔርን ሊያመሰግን በመንገድ ላይ ሲተራመስ ይታይ ነበር ::
በተለይ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ውበቱዋ ይህ ለት ነበር እንዲሁም አኑዋር መስጌድ

አሁንማ ንጉስ ሆይ እርግማንዊ እንሆ የእምነት አባቶቻችንን ወደውስጥ አስገብቶ እኛው ሃጤያተኛ ልጆችዎን ሌባ ሌባ ሌባ ባልንበት አፋችን ተለጉመን ቤተክርስትያ እንዳንደርስ ሁነናል
እሪሳችንም ለጥንብ አንሳ ከተሰጠን ሰነባበትን ፍትሃት አይታሰብም እናማ ! ደጉ መሪያችን ግርማዊ ሆይ እባክዎን ይማሩን !

መጭው አመት ቤተ መንግስትዎ እና ቤተእምነት ተረጋግቶ ሰላም ፍቅር እምነት አንድነት መዋደድ መከባበር ትህትና እና ብልፅግና በሀገራችን በኢትዮጵያ ሰፍኖ የምናይበት በአለም ዙሪያ ተበትኖ ያለው ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው መሬት የሚበቁበት የታሰሩ ተፈተው የታመሙ ድነው ተምች ከአለም ጠፍቶ ሀገረ ሰላም ኢትዮጵያን ለማየት ያበቃን ዘንድ ንጉስ ሆይ ይማሩን !!!

መልካም አዲስ ዘመን እንዲሆንልን ይቅርታን እናስቀድም :: ለሞላው የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም በጤና አደረሳችሁ::

አልማዝ ጣሰው መኩንን

ከአሜሪካ !

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *